ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የዘንድሮው የአዲስ ዓመት ገበያ በምስል
ታትሟል
በጦርነት፣ በረሃብ፣ በመፈናቀል በሌሎች ችግሮች የተሞላው አሮጌው ዓመት 2014 ዓመት ተጠናቆ አዲሱን ዓመት ተቀብለናል። የዛሬዋ መስከረም 01/2015 ዘመን መለወጫ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረች ትገኛለች።
ኢትዮጵያውያን በእንቁጣጣሽ እንደ አቅማቸው ዶሮ፣ በግ ወይም በቅርጫም ቢሆን የበሬ ሥጋቸውን በመጫረት ክብረ በዓሉን ያደምቁታል።
የሽንኩርቱ ቁሌት፣ የቅቤው ሽታ፣ የቡናው መዓዛና የእጣኑ ሽታ በየቤቱ ያውዳል፣ የእርዱ ሁካታ፣ የዘመድ አዝማዱ ሳቅ፣ የአገር ባህል ልብሱ፣ ሙዚቃው የአውደ ዓመቱ መገለጫዎች ናቸው።
ቢቢሲ አማርኛም በአዲስ አበባ የተወሰኑ ስፍራዎች ተዘዋውሮ የገበያውን ሁኔታ ቃኝቷል።