የአሜሪካ ፖለቲከኞች የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ላይ ከስምምነት ደረሱ

ጠንካራ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ሕግ እንዲወጣ በመጠየቅ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ሰልፎች ተደርገዋል

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ጠንካራ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ሕግ እንዲወጣ በመጠየቅ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ሰልፎች ተደርገዋል
ታትሟል

በአሜሪካ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን በተመለከተ ልዩነት ያላቸው ሪፐብሊካን እና ዲሞክራቶች በአዲሱ መመሪያ ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ተገለጸ።

ሆኖም የምክረ ሃሳባቸው ሂደት የሚጠበቅበትን ያህል አልተጓዘም ተብሏል።

ፍሎሪዳ ውስጥ በአንድ ትምህር ቤት ላይ ከተከፈተ ተኩስ የተረፉት ዴቪድ ሆግ “ምንም እንኳን ይህ ስምምነት ትንሽ ቢሆንም ጠቃሚ እርምጃ ነው” ብለዋል።

ሌላዋ የቀድሞ ሕግ አውጪ እና እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 በአሪዞና ግዛት ውስጥ ከተፈጸመ ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው የተረፉት ጋብሬል ጊፎርድስ ስምምነቱን “ጠቃሚ እርምጃ ነው” ብለውታል።

ተቀናቃኞቹ ከስምምነት የደረሱበት አዲሱ እቅድ የጦር መሳሪያ ገዢዎች ጠንካራ ምርመራ የሚደረግባቸው ሲሆን ከ 21 ዓመት በላይ መሆን እና ከሕገ ወጥ የመሳሪያ ግዢ ጋር በተያያዘ ምረመራ ይደረገባቸዋል።

ይህ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ምክረ ሀሳብ ትላንት ዕሁድ ነበር ይፋ የተደረገው።

10 የሪፐብሊካን አባላት ሕጉን የደገፉ ሲሆን ይህ ማለት ወደ ሕግ ለመቀየር የሚስፈልገው ቁጥር ተሟልቷል ማለት ነው።

ፕሬዝዳነት ጆ ባይደን ዕቅዱ በትክክለኛ መንገድ ላይ እየሄደ ነበር ያሉ ሲሆን፣ ሆኖም እሳቸውም ይሁን ሌሎች ዲሞክራቶች እንዲሆን ከሚፈልጉት እጅግ የራቀ ነው።

ከየትኛውም የበለጸገ አገር በላይ በጦር መሳሪያ በርካታ ሰዎች የሚገደሉባት አሜሪካ፣ ጠበቅ ያለ የጦር መሳሪያ ሕግ ለማውጣት ያደረገችው ተደጋጋሚ ሙከራ ከሽፏል።

ምክንያቱ ደግሞ በኮንግረስ የሚጠበቀው ድምጽ በለመገኘቱ ነው።  

በአሜሪካ በቅርቡ በሁለት አከባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ትላንት ዕሁድ በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶች ጠንካራ የጦር መሳሪያ ሕግ እንዲጸድቅ የሚጠይቁ ሰልፎች ተካሄደዋል።

“እንደ መጀመሪያ ትልቅ እርምጃ ነው ነገር ግን የሆነው ሆኗል” ያሉት ሆግ “አንድ ፖሊስ ብቻውን ሁሉንም የጅምላ ግድያን አያስቆምም። ነገር ግን ቀጣዩን የፓርክላንድ አይነት [ፍሎሪዳ እሳችው የተረፉበት ጥቃት ነው] የጅምላ ግድያን ያስቆማል። ያ ደግሞ መልካም ነው” ብለዋል።

ጭንቅላታቸው ላይ ሰባት ቦታ ጉዳት የደረሰባቸው ጊፎርድስም አሁን ዲሞክራቶች እና ሪፐብሊካን የደረሱበትን ስምምነት አድንቀዋል።  

ይህ ስምምነት “ኮንግረሱ በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ዙሪያ እርምጃ ሲወስድ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሆን ይቸላል” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሰፈሩ ሲሆን “ስምምነቱ ጉዳዩን በፖለቲካ መንገድ መፍትሄ መስጠት እንደሚቻል እና የአሜሪካውያንን ደኅንነት መጠበቅ እንደሚቻል ያሳየ ነው” ብለዋል።

የአሜሪካ ሴኔት ወይም የላኛው ምክር ቤት አሁን ላይ በ50 ዴሞክራቶች እና በ 50 ሪፐብሊካኖች የተያዘ ነው ነው። ሕጎች እንዲጽድቁ ደግሞ 60 ድምጽ ያስፈልጋል።

 የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ሕጉን 10 ሪብሊካን ሴናተሮች የደገፉት ሲሆን ይህም ሕጉን ለመደገፍ የሚያስችል ድምጽ አስገኝቷል።