ዶናልድ ትራምፕ፡ "አሜሪካ የዓለም ጤና ድርጅትን ጥላ የምትወጣበት በቂ ምክንያት የላትም" ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ታትሟል
አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት መውጣቷን በማስመልከት፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ጥሎ ለመውጣት በቂ ምክንያት የላቸውም" ሲሉ የድርጅቱ የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ተናገሩ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነቷ መውጣቷን ያስታወቁት በግንቦት ወር ሲሆን፣ ድርጅቱን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቻይናን ተጠያቂ ማድረግ ተስኖታል የሚል ስሞታ ያሰሙ ነበር።
ከታይም መጽሔት ጋር በነበራቸው ቆይታ " እውነቱን ለመናገር በመጀመሪያ አላመንኩም ነበር" ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም " አሁንም ቢሆን የአሜሪካ አስተዳደር ከዓለም ጤና ድርጅት ጥሎ ለመውጣት በቂ ምክንያት የለውም ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
በ2019 አሜሪካ የዓለም ጤና ድርጅትን አጠቃላይ በጀት 15.18% በመቶ ትሸፍን ነበር። ይህም ከፍተኛ መዋጮ ከሚያዋጡ አገሮች መካከል ብቸኛው ያደርጋታል።
ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴድሮስ የኮቪድ-19 ክትባት ተገኝቶ ክፍፍል ሲጀመር ዳግም አሜሪካ ያላት ትብብር ይሻሻላል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።
"ክትባትን ማከፋፈል ላይ አሁን የምንከተለው መሰረታዊው መርሆ፣ በተወሰኑ አገራት ለሁሉም ሰዎች ሳይሆን፣ በሁሉም አገራት ለተወሰኑ ሰዎች ክትባቱን መስጠት ነው።" ብለዋል።









