የኤርትራ መንግሥት ግብጽ በኤርትራ ደሴት ላይ የባህር ኃይል ልታሰፍር ነው መባሉን ሐሰት ነው አለ

ጎግል ማፕ

የፎቶው ባለመብት, Google Map

የምስሉ መግለጫ, ኖራህ ደሴት ከዳህላክ በሰሜን አቅጣጫ በቃይ ባሕር ላይ ትገናለች።
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 1 ደቂቃ

በኤርትራዋ ኖራህ ደሴት ላይ ግብጽ የባህር ኃይሏን ለማስፈር ከኤርትራ ጋር ተስማምታለች መባሉን የኤርትራ መንግሥት ሐሰተኛ ወሬ ነው ሲል አጣጣለው።

'ዘ አረብ ዊኪሊ' የተባለው ድረ-ገጽ ከ10 ቀናት በፊት ግብጽ በኤርትራዋ ኖራህ ደሴት ላይ የባህር ኃይሏን ለማስፈር ከኤርትራ ጋር ከስምምነት ለመድረስ ተቃርባለች ሲል ዘግቦ ነበር።

የኤርትራ መንግሥት ግን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይህን "መሠረተ ቢስ ሐሰተኛ ወሬ ነው" ብሎታል።

መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ድረ-ገጽ ኤርትራን የተመለከቱ መሠረተ ቢስ የሆኑ መረጃዎች ያስራጫል ብሏል የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚንስቴር።

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ጨምሮም "የኤርትራ መንግሥት ይህን መሠረት ቢስ የሆነና እውነታውን ያማያመላክት ግላዊ አስተያያትን አይቀበልም" ብሏል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

ኖራህ ደሴት ከዳህላክ በሰሜን አቅጣጫ በቀይ ባሕር ላይ ትገኛለች።

በደሴቷ ላይ የራሻይዳ፣ አፋር እና ትግረ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ኤርትራውያን ይኖሩባታል።