ፈረንሳዊው የ69 ዓመት የቀዶ ህክምና ሃኪም ህፃናትን በመድፈር ተከሰሱ

የአዛውንቱ የፍርድ ቤት ውሎ በስዕል

የፎቶው ባለመብት, AFP/Getty Images

ታትሟል

የ69 ዓመቱ ጡረተኛ የፈረንሳይ ቀዶ ጥገና ሃኪም ጆዬል ሶራንስ ሁለት የቅርብ ዘመዶቻቸውን ህፃናት፣ የጎረቤት ልጅ እንዲሁም አንድ ህሙም ላይ ፆታዊ ጥቃት በማድረስ ነው የተከሰሱት።

አቃብያነ ህጎች አዛውንቱ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1989-2017 ዓመታት ውስጥ ምናልባትም 349 ህፃናት ላይ ፆታዊ ጥቃት አድርሰዋል ብለው ጠርጥረዋል።

አዛውንቱ የተወሰኑ ዓይነት ጥቃቶችን ህፃናቱ ላይ መፈፀማቸውን ቢያምኑም የአስገድዶ መድፈር ግን እንዳልፈፀሙ ቃላቸውን ለፍርድ ቤት ሰጥተዋል።

አዛውንቱ ህፃናት ላይ ፆታዊ ጥቃት ፈፃሚ የፍርድ ሂደት እየተሰማ ሲሄድ ብዙ ሌሎች ተጎጅዎችም ሊመጡ እንደሚችሉ ግምት አለ።

የ69 ዓመቱ አዛውንቱ በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ የ20 ዓመት እስራት ሊጠብቃቸው ይችላል ተብሏል።

ጡረተኛው የቀዶ ጥገና ሃኪም የታሰሩት ከሶስት ዓመታ በፊት ጥቃት ያደረሱባት የጎረቤታቸው ህፃን ለወላጆቿ መናገሯን ተከትሎ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ ነበር።