ጆ ባይደን ኡሁሩ ኬንያታን በዋይት ሐውስ ተቀብለው አነጋገሩ

ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ጆ ባይደን

የፎቶው ባለመብት, White House

የምስሉ መግለጫ, ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ጆ ባይደን
ታትሟል

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የኬንያውን ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታን በዋይት ሐውስ ተቀብለው አነጋገሩ።

ሁለቱ መሪዎች በአሜሪካ እና በኬንያ መካከል ባለው ጠንካራ የተባለ ወዳጅነት ዙሪያ ተወያይተዋል ሲል የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ዋይት ሐውስ በመግለጫው አስታውቋል።

ባይደን እና ኬንያታ በውይይታቸው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ውስጥ ላሉ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሄ መገኘት አለበት በሚለው ላይ አጽንኦት ሰጥተው መነጋገራቸውን መግለጫው ጠቅሷል።

ሁለቱ መሪዎች ዲሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እንዲሁም አህጉራዊ ሰላም እና ደኅንነት በማስጠበቅ ዙሪያ ሁለቱ አገራት በጋራ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ዙሪያ ተነጋግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝደንቶቹ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በጋራ ለመግታት የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ለማምረት ሊያደርጉ ስለሚችሉት ትብብሮች ተወያይተዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን ለአፍሪካ ሕብረት አገራት የጆንሰን ኤንድ ጆንስን ምርት የሆነው 17 ሚሊዮን ክትባት እንደሚሰጡ አስታውቋል።

ኬንያ እስካሁን 2.8 ሚሊዮን ክትባቶችን እስካሁን የተቀበለች ሲሆን፤ ተጨማሪ የፋይዘር ክትባቶችን በቀጣይ ወራት ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነች።