ሰባት መኮንኖች ገድለው የተሰወሩት ናይጄሪያዊያን ታጣቂዎች በፖሊስ እየተፈለጉ ነው

ታትሟል

በናይጄሪያ የታጠቁ ሰዎች በድንገት ባደረሱት ጥቃት ሰባት ፖሊሶ መገደላቸውን ተከትሎ ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመያዝ ፍለጋ እየተደረገ ነው።

በአገሪቱ ደቡባዊ ግዛት በሚገኝ አንድ የፍተሻ ጣቢያ ላይ ታጣቂዎቹ ተኩስ የከፈቱ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ ወደ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች በመሄድ ፖሊሶችን ገድለዋል፤ የፖሊስ መኪናዎችንም አቃጥለዋል ብሏል ፖሊስ።

ፖሊስ በአጸፋው በወሰደው እርምጃ ሁለት ጥቃት ፈጻሚዎች በቦታው የተገደሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ አምልጠዋል። አሁን ላይ ቀሪዎቹን ጥቃት ፈጻሚዎች ለመያዝ ከፍተኛ ፍለጋ እየተደረገ ነው።

እስካሁን ድረስ ጥቃቱ ለምን እንደፈጸመ ያልታወቀ ቢሆንም አካባቢው ግን ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ጥቃቶችንማስተናገዱ የሚታወስ ነው።

ማንነታቸው ያልታወቀው ግለሰቦች ‘ቾባ በሚባለው ድልድል ላይ በሚገኘው የፍተሻ ጣቢያ ላይ ድንገተኛ ጥቃትየሰነዘሩት በአገሪቱ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ መሆኑን የፖሊስ ቃል አቀባዩ ናምዲ ኦሞኒ ገልጸዋል።

‘’በፍተሻ ጣቢያው ውስጥ የነበሩ ሁለት ፖሊሶችን ተኩሰው ከገደሉ በኋላ በመንገዳቸው ያገኟቸውን ሌሎች ሁለትፖሊሶችም ገድለዋል። በመቀጠል ደግሞ ‘ሩሙጂ’ የሚባለው የፖሊስ ጣቢያ ንብረት የሆነ ተሽከርካሪ በእሳትአያይዘዋል’’ ብለዋል ቃል አቀባዩ።

አክለውም ‘’ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ደግሞ ሁለት ታጣቂዎች ተገድለዋል’’ ብለዋል።

ያመለጡት ጥቃት ፈጻሚዎች ደግሞ ‘ኤሊምቡ’ ወደተባለ ሌላ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ተጨማሪ ሶስት ፖሊሶች ላይ ተኩስበመክፈት ገድለዋለቸዋል።

በአዚህ አከባቢ ከቅርብ ጊዜኣት ወዲህ ፖሊሶችና ወታደሮች እየተገደሉ መሆናቸውን ተከትሎ በምሽት ተግባራዊየሚሆን አዲስ የሰአት እላፊ ተጥሏል።

ባሳለፍነው ሐሙስ አህን ጥቃት ከተፈጸመበት አካባቢ ብዙም ሳይርቅ ‘አናምብራ’ ግዛት ውስጥ የታጠቁ ግለሰቦችበከፈቱት ተኩስ የሁለት ፖሊሶች ሕይወት አልፏል።

ነይጄሪያ ከመሰል ጥቃቶች በተጨማሪ `በሰሜን ምስራቃዊ የአገሪቱ ክፍል ኢስላማዊ አክራሪዎች በሚያደርሷቸውጥቃቶች እየተፈተነች ነው። እንዲሁም በሰሜን ምዕራባዊ ክፍል ደግሞ ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 700 ህጻናትከትምህርት ቤት ታፍነው ተወስደዋል።