ኡጋንዳ፡ አሜሪካ በምርጫ ጉዳይ ኡጋንዳን ‹‹የማስተማር›› መብት የላትም

ታትሟል

አሜሪካ ለኡጋንዳ ስለምርጫ ‹‹ትምህርት›› ከመስጠት ይልቅ በቅድሚያ የራሷን ምርጫዎች ማስተካል ይገባታል ማለታቸወን ተዘገበ።

የኡጋንዳ መንግሥት ቃል አባይ ኦፍዎኖ ኦፖንዶ፤ የአሜሪካ መንግሥት ስለ ኡጋንዳ ምርጫ አስተያየት ከመስጠቱ በፊት 'የራሱን ምርጫ ቢያስተካከል ይሻላል' ስለማለታቸው ቪዥን የተሰኘው ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያለው መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

አሜሪካ በኡጋዳን ከተካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ በፀጥታ ኃይሎች የተፈፀሙ ‹‹ሕገ ወጥነቶችን›› እና ‹‹በደሎችን›› ተከትሎ በዩጋንዳ ላይ ‹‹የታለሙ አማራጮችን›› እያጤነች እንደሆነ መግለጿን ተክተሎ ነው ቃል አቀባዩ ይህንን ያሉት።

ኦፔንዶ በሰጡት አስተያየት መንግሥታቸው ከአሜሪካ መንግሥት በጉዳዩ ላይ በይፋ መልክት እንዳልደረሰው ገልፀው ያንን እየተጠባበቀ ነው ብለዋል።

‹‹እስከዛው ግን የአሜሪካ መንግሥት የራሱን ምርጫ ቢያስተካከል ይሻላል፣ እንደ ፕሬዘዳንት ትራምፕ ከሆነ በህይወት የሌሉ ሰዎችም ምርጫ ላይ ተሳትፈዋል እንዲሁም ጆ ባይደን ስልጣን ላይ የወጡት በተጭበረበረ ምርጫ ነው። ስለዚህ እኛን ለማስተማር የመጨረሻዎቹ ነው መሆን ያለባቸው›› ብለዋል ቃል አቀባዩ።

ላለፉት 34 ዓመታት ኡጋንዳን እየመሩ ያሉት ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በጥር ወር ተካሂዶ የነበረውን ምርጫ አሸንፊያለሁ ማለታቸው ይታወሳል።

የሙሴቬኒ ዋነኛ ተፎካካሪያቸው የነበረው ቦቢ ዋይንም ምርጫው ተጭበርብሯል ሲል ቅሬታውን ቢያሰማም የምርጫውን ውጤት በፍርድ ቤት የመሞገት እቅዳቸውን መተውን ገልጿል።

የምርጫው ይፋዊ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ ሙሴቬኒ 59 በመቶ ድምፅ ያገኙ ሲሆን ቦቢ ዋይን 35 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ መሰብሰብ ችሏል።