ኮሮናቫይረስ : አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ

ታትሟል

አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በመላው ዓለም ሊሰራጭ ይችላል ተባለ።

ኬንት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዓለም ላይ በስርጭቱ ቀዳሚው ሊሆን ይችላል ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደም የዘረ መል ክትትል መርሃ ግብር ኃላፊ ገልጸዋል።

ኃላፊው ፕሮፌሰር ሻሮን ፒኮክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዲሱ ዝርያ "በአገሪቱ የተሰራጨ" ሲሆን "በመላው ዓለም የመሰራጭ ዕድሎችም" አሉት ብለዋል፡፡

በኬንት የተገኘው ዝርያ ከ50 በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ ተሰራጭቶ ይገኛል።

የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ በጎርጎሮሳዊያኑ መስከረም 2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ሲሆን፤ በቀጣይ ወራት በፍጥነት ተስፋፍቶ በጥር ወር በመላው ዩናይትድ ኪንግደም አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል ምክንያት ሆኗል።

ፕሮፌሰር ፒኮክ "በእውነቱ ከሆነ እኛን በመጉዳት ላይ የሚገኘው በከፍተኛ ፍጥነት መተላለፉ ነው" ብለዋል።

ለኮሮናቫይረስ የተሠሩ ክትባቶች ቀደም ሲል ለነበረው የቫይረሱ ዙሪያ የተመረቱ ቢሆንም ሳይንቲስቶች አሁንም ቢሆን በአዲሱም ዝርያ ላይ ይሠራሉ ብለው ያምናሉ። ውጤታማነታቸውን ግን ጥሩ ላይሆን ይችላል።

በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ክትባቶች በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የቫይረስ ዓይነቶች ላይ በጥሩ ሁኔታ የሚሠሩ ይመስላሉ ብለዋል ፕሮፌሰር ፒኮክ።