ኮሮናቫይረስ፡ በቀን ግማሽ ሚሊዮን ሰው የምትመረምረው ሃገር

ታትሟል

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፤ ሃገራቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በሚቀጥሉ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በቀን አንደ ሚሊዮን ሰው መመርመር እንደምትጀምር አሳውቀዋል።

ነገር ግን የሞዲ አገር ሕንድ ይህን ማድረግ ይቻላት ይሆን? ምርመራውስ አስተማማኝ ነው?

ሕንድ አሁን በቀን ስንት ሰው ትመረምራለች?

ወርሃ ነሐሴ ሲጠባ ሕንድ በአንድ ቀን ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች እየመረመረች እንዳለ 'አወር ዎርልድ ኢን ዳታ' የተሰኘው ድርጅት ይፋ ቢያደርግም ቁጥሩ ግን ከዚያም በላይ እንደሆነ ከመንግሥት ቤት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ይህ በጣም ከፍተኛ አሃዝ ነው። ነግር ግን ከሕንድ ሕዝብ ቁጥር አንፃር ሲታይ እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆን መረዳት ይቻላል።

ሕንድ በቀን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ መረመረች ማለት ከ100 ሺህ ሕዝብ 36 ሰዎች ብቻ ተመርምረዋል ማለት ነው። ደቡብ አፍሪካ በተመሳሳይ ቀመር 69 ሰዎች ትመረምራለች፣ ፓኪስታን 8 ሰው፤ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ስንመጣ ደግሞ 192 ሰው ይሆናል።

1.3 ቢሊዮን ሰው የሚያስተዳድሩት ሞዲ ይህን በማሰብ ነው በቀን ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ሰው መመርመር አለብን ያሉት።

መመርመሪያ መንገድ

በርከታ የዓለማችን ሃገራት የሚጠቀሙት መመርመሪያ መንገድ በሕክምና ቋንቋ ፒሲአር ተብሎ የሚታወቀው ነው። ይህ መመርመሪያ ጥጥ በመጠቀም የዘረ መል ቅንጣት በመወሰድ ቫይረሱ መኖር አለመኖሩን የሚያጣራ ነው።

ምንም እንኳ ይህ የመመርመሪያ መንገድ አሁን ላይ በስፋት እየዋለ ያለና አዋጭ ቢሆንም፤ ለሕንድ ግን በጣም ውድ ከመሆኑም ባለፈ ውጤት ለማወቅ 24 ሰዓታት ሊፈጅ ይችላል።

የሕንድ ባለሥልጣናት በአጭር ጊዜ በርከታ ሰዎች መመርመር ያስችላቸው ዘንድ ፈጠን ወዳለ መንገድ ፊታቸውን አዙረዋል። ይህ መንገድ ዳያግኖስቲክ ወይም ራፒድ ቴስት በመባል ይታወቃል።

ይህ መንገድ ሰውነት ውስጥ ያለ ለቫይረሱ ቅርበት ያለው ፕሮቲንን ከለየ በኋላ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውጤት ማሳወቅ ይችላል።

ነገር ግን ይህ ዘዴ ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር አስተማማኝነቱ ዝቅ ያለ ነው። በመቶኛ ሲሰላ የዚህ መመርመሪያ መንገድ አስተማማኝነት 50 በመቶ ያክል ነው።

እዚህ ላይ መርሳት የሌለብን ነገር እኒህ መመርመሪያዎች በቫይረሱ መያዝ አለመያዝዎን እንጂ ከዚህ በፊት ተይዘው እንደነበር ከሚለየው መንገድ የሚለዩ መሆናቸውን ነው።

'ራፒድ ቴስት' ተመራጭ ነው?

ይህ መመርመሪያ መንገድ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ጥቅም ላይ ውሎ 20 በመቶ ውጤት ትክክለኛ ያለሆነ ሆኖ ተገኝቷል።

ነገር ግን ኦክስፎርድ ናኖፕር የተሰኘው ተቋም ያመረታቸው መመርመሪያዎች 98 በመቶ ትክክለኛ ውጤት አሳይተዋል። ነገር ግን ተጨማሪ ምርመራዎች ያሻዋል ተብሏል።

ነገር ግን ራፒድ ቴስቲንግ የሚባለውም አሁን በርከታ ሃገራት የሚጠቀመሙት የዘረ-መል ቅንጣት ምርመራ ከሞላ ጎደል አስተማማኝ ናቸው።

የዓለም ጤና ድርጅት ራፒድ ቴስት በተሰኘው ተመርምረው ቫይረሱ የለብዎትም ከተባለ በፒሲአር ምርመራ እንዲያረጋግጡ ይመክራል።

አሜሪካ፤ ልክ እንደ እርግዝና ማሳወቂያ ያለ በየትኛውም መድኃኒት ቤት ሊገኝ የሚችልና የኮሮናቫይረስ ውጤትን በጥቂት ደቂቃዎች የሚያሳውቅ አነስተኛ መሣሪያ አምርታ ለገበያ ለማቅረብ እየጣረች ነው።

አሜሪካ የምትጠቀማቸው የመመርመሪያ መንገዶች ከሕንድ ጋር ሲነፃፀሩ 81 በመቶ ትክክለኛ የሆነ ውጤት ያትማሉ።

ሕንድ፤ ከሁለት ሳምነታት በፊት በፈጣን ምርመራ ተመርምረው ቫይረሱ የለባችሁም ተብለው ነገር ግን የኮሮናቫይረስ ምልክት የሚታይባቸውን ሰዎች ድጋሚ የፒሲአር ምርመራ እንዲያደርጉ አድርጋ 38 በመቶው ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ፈጣን ምርመራ በርካቶች በአጭር ጊዜ ለመመርመር ይርዳ እንጂ የወረርሽኙን ትክክለኛ ባሕሪ ሊደብቅ ይችላል ሲሉ የጤና ባለሙያዎች ይሞግታሉ።