ለዛሃ ዘረኛ መልዕክት የላከው የ12 ዓመት ልጅ በቁጥጥር ሥር ዋለ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የአይቮሪ ኮስት ብሔራዊ ቡድንና በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የክርስታል ፓላስ ተጫዋች ለዊልፍሬድ ዛሃ የዘረኝነት መልዕክት የላከው የ12 ዓመት ልጅ በፖሊስ መያዙ ተነገረ።
ዛሃ ከዚህ በተጨማሪም በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት መሰል መልዕክቶች እንደሚደርሱት አስታውቋል።
የክርስታል ፓላስ አሰልጣን ሮይ ሆድሰን የዘረኝነት ምልዕክቶቹን "የፈሪ ድርጊትና አሳፋሪ" ተግባር ሲሉ ገልጸውታል። ፕሪሚየር ሊጉም በ27 ዓመቱ አጥቂ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት "በምንም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው" ሲል አውግዞታል።
ፖሊስ የዛሃ የቆዳ ቀለም ላይ ያነጣጠሩ ዘረኛ መልዕክቶችን እየመረመርኩ ነው ካለ ከሰዓታት በኋላ አንድ የ12 ዓመት ታዳጊን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል።
የዌስት ሚድላንድስ ፖሊስ ትናንት በትዊተር ገጹ ላይ "ለእግር ኳስ ተጫዋቹ በርካታ ዘረኝነት የተሞላባቸው መልዕክቶች እንደደረሱት ሪፖርት ደርሶናል። ባደረግነው ማጣራትም ከሶሊሁል ከተማ የ12 ዓመት ልጅ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ዘረኝነትን አንታገስም" ብሏል።
ዛሃ በትዊተር ገጹ ላይ የደረሱትን ዘረኛ መልዕክቶች አስፈሯል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
"በግጥሚያ ቀን እንዲህ አይነት መልዕክት ሲደርስ በጣም ያሳዝናል። መልካም ነገሩ ዛሃ የደረሰውን መልዕክት ሰዎች እንዲያውቁት አድርጓል። በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም ሰው ዝምታን መምረጥ የለበትም" ብለዋል የክሪስታል ፓላስ አሰልጣኑ ሮይ ሆድሰን።
ፕሪሚየር ሊጉ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ ከተመለሰ በኋላ ተጨዋቾች ዘረኝነትን በመቃወምና በጥቁሮች ላይ የሚፈጸሙ በደሎችን ለመቃወም ጨዋታዎች ከመጀመራቸው በፊት የ'ብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴን በመደገፍ ተንበርክከው አጋርነታቸው ይገልጻሉ።












