በህንድ አባት እና ልጅ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መሞታቸውን ተከትሎ ቁጣ ተቀሰቀሰ

ፖሊስ ተቃዋሚዎችን ሲደበድብ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 1 ደቂቃ

በህንድ ደቡባዊ ግዛት ታሚል ናዱ፤ አባት እና ልጅ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሳሉ መገደላቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጣ ተቀሰቀሰ፡፡

የ58 ዓመቱ ፒ ጀያራጅ እና የ38 ዓመቱ ወንድ ልጁ ፌኒክስ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለባት ታሚ ናዱ፤ ከተፈቀደው ሰዓት ውጭ የንግድ ሱቃችሁን ከፍታችኋል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡

ሁለቱ ግለሰቦች ምሽቱን በእስር ያሳለፉ ሲሆን ከሁለት ቀናት በኋላ በሰዓታት ልዩነት ሁለቱም ሕይወታቸው አልፏል፡፡

የሟች ቤተሰቦች በእስር ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል፡፡

የግለሰቦቹን ሞት ተከትሎም ማህበረሰቡ ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው፡፡ የከተማዋ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን እየተከታተለ ነው፡፡

ሁለቱን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ያዋሉት ፖሊሶች ወደ ሌላ ቦታ የተዛወሩ ሲሆን፤ የግዛቷ መንግሥት ለተጎጂ ቤተሰቦች 13 ሺህ 222 ዶላር ካሳ ሰጥቷል፡፡

ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡

በርካቶች በቅርቡ በአሜሪካ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ በግፍ ከተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ጋር በማያያዝ የፖሊስን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት አውግዘዋል፡፡

ድርጊቱን ፈጽመዋል ያሏቸው ፖሊሶችም በግድያ ወንጀል ባለመከሰሳቸው ከፍተኛ ቁጣ ተነስቷል፡፡

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

በህንድ በእስር ቤቶች የሚፈጸሙ ኢ ሰብዓዊ ድርጊቶች በተመለከተ ሪፖርት የሚያወጣ አንድ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጥምረት ባለፈው ዓመት ብቻ 1ሺህ 731 ሰዎች በእስር ቤት ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ይህ ማለትም በቀን ውስጥ 5 የሚሆኑ ሰዎች በአስር ላይ እያሉ ይሞታሉ ማለት ነው፡፡