የሰባት ዓመት ህፃን የቤት ሠራተኛቸውን አሰቃይተው ገድለዋል የተባሉት ፓኪስታናውያኑ ባልና ሚስት ዘብጥያ ወረዱ

ሃሰን ሲዲቄ በፖሊስ ቁጥጥር ስር
የምስሉ መግለጫ, አሰሪዋ ሃሰን ሲዲቄ ህፃኗ እንደሞተች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

የሰባት ዓመት ህፃን ሠራተኛቸውን አሰቃይተው ገድለዋል የተባሉት ፓኪስታናውያኑ ባልና ሚስት የ'ፖሊግራፍ' (እውነትና ሐሰት መናገራቸውን የሚያጣራ መሳሪያ) ምርመራ ፖሊስ እስኪያደርግ ለሁለት ሳምንት ያህል በእስር እንደሚቆዩ ተገልጿል።

ጉዳት የደረሰባት ዛህራ ወደ በራዋልፒንዲ ወደሚገኝ ሆስፒታል አሰሪዎቿ ያመጧት ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር። ከአንድ ቀንም በኋላ ህይወቷ አለፈ።

የሆስፒታሉ ሠራተኞች ለፖሊስ ደውለው ሁኔታውን አሳውቀዋል።

በፓኪስታን ከአስራ አምስት አመት በታች የሚገኙ ህፃናትን መቅጠር ሕገ ወጥ ቢሆንም በከፍተኛ ሁኔታም የተስፋፋ ነው።

የህፃኗ ህይወት መጥፋትሎ ከፍተኛ ንዴትና ቁጣ በአገሪቱ ያስከተለ ሲሆን መገናኛ ብዙሃንም የፊት ገፃቸው ላይ የግድያውን ዜናወ ይዘውት ወጥተዋል።

በግድያው ወንጀል የተጠረጠሩት ባልና ሚስት ምንም ከማለት ተቆጥበዋል።

የፓኪስታን የሰብዓዊ መብቶች ሚኒስትር ሕጎቹን በማሻሻል ህፃናት ልጆችን ከመቀጠር ለማዳን እንደሚሰሩ ቃል ቢገቡም፤ ተችዎች ግን ያሉትን ሕጎች በአግባቡ እንኳን ማስፈፀም አልቻሉም ብለዋል።

የሟቿ ህፃን ዛህራ አያት ሰይድ ፋዛል ሁሴን ሻህ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለባልና ሚስቱ በምግብ አብሳይነት የሚሰራ የሩቅ ዘመዳቸው ከአምስት ወራት በፊት እንዳስቀጠራት ነው።

"ግለሰቡ ያስተምሯታል አለን። እኛ ለማስተማርም አቅሙ ስለሌለን የተሻለ ነገር ታገኛለች ብለን ሰደድናት" ብለዋል።

ፖሊስ ስለ ዛህራ አሟሟት ምን ይላል?

በፖሊስ ሪፖርት መሰረት ዛህራ ባህሪያ ከተማ ወደምትገኘው ራዋልፒንዲ ሆስፒታል በፀና ተጎድታ በአሰሪዋ ሃሰን ሲዲቄ የመጣችው ግንቦት 23፣ 2012 ዓ.ም ነበር።

ያለማቋረጥ ደም ይፈሳት ነበር። ፊቷ፣ ደረቷ፣ እጆቿና እግሮቿ ላይ ከፍተኛ የድብደባ ምልክቶች ነበሩባት። ወዲያው ነበር ወደ የፅኑ ህሙማን ክፍል የገባችው፤ ቬንትሌተርም ተገጠመላት። ነገር ግን በሕይወት ብዙም አልቆየችም፤ ሞተች።

የሆስፒታሉ ሠራተኞች ለፖሊስ ደውለው ሁኔታውን ማሳወቃቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል። ፖሊስ በደረሰበት ወቅት ህፃኗ በህይወት ብትኖርም ራሷን አታውቅም ነበር

ህፃኗ ዛህራ በአምስት አመቷ

የፎቶው ባለመብት, Family handout

የምስሉ መግለጫ, ህፃኗ ዛህራ በአምስት አመቷ

የሆስፒታሉ ሠራተኞችም ሃሰን ሲዲቄ ዛህራን ያመጣት ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል መሆኑን አስረድተዋል።

ህፃኗ ዛህራ የቤት ሠራተኛቸው እንደሆነችና ቤት ውስጥ ያሉትን በቀቀኖች ከማደሪያቸው በማስመለጧ እሱም ሆነ ባለቤቱ ተናድደው እንደበደቧትና እንዳቆሰሏት ሃሰን ለጤና ባለሙያዎቹ ተናግሯል።

ለህፃኗም የድንገተኛ ህክምና እያደረጉ በነበረበት ወቅትም ሃሰን ከአካባቢው ተሰወረ። በሆስፒታሉ ግቢ ቢፈልጉትም ሊያገኙት ባለመቻላቸው ለፖሊስ ደወሉ።

ህፃኗን ለህክምና ባመጣት ወቅት ባስያዘው መታወቂያ በመጠቀምም ባልና ሚስቱ ሊገኙ ችለዋል፤ በፖሊስም ቁጥጥር ስር ዋሉ።

ዝቡ ቁጣ

በርካቶች በፓኪስታን ውስጥ ስር የሰደደው የማኅበረሰቡ ልምዶች እንዴት ህፃናትን ለጥቃትና ለሞት እየዳረገ እንደሆነ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል።

የሰብዓዊ መብት ታጋዮችም ግድያውን የፈፀሙት ወደ ፍርድ እንዲቀርቡ ጥሪ እያደረጉም ይገኛሉ።

እንዴት ተጋላጭ ከሆነ ማኅበረሰብ ለሚመጡ ህፃናት ሕጋዊ ከለላ አለመኖሩም በብዙዎች ዘንድ እየተተቸ ነው።

ግራ ዘመመሙ የሴቶች ዲሞክራቲክ ፎረም አባልና የሰብዓዊ መብት ታጋይ ለአሰሪዎቿ ጥያቄን አቅርባለች።

"ወፎችን ከጎጇቸው ነፃ ስላወጣቻቸው እንዴት ነው የምትገድሏት? እንዴት?" በማለት በትዊተር ገጿ ላይ አስፍራለች።

በላሆር ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነችው ኒዳ ኪርማኒም ህፃናትን በቤት ሠራተኝነት መቅጠር "የከፋ ብዝበዛ ነው" ብላለች።

በባለፈው ዓመት የፑንጃብ አስተዳደር ከአስራ አምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት በቤት ሠራተኝነት እንዳይቀጠሩ የሚከለክል ሕግ ቢያፀድቅም ብዙዎች ይጥሱታል።

ሕግ በማስከበሩም ላይ ክፍተት መኖሩንም በርካቶች ይናገራሉ።

በህፃናት የቤት ራተኞች ላይ ስለሚደርስ ጥቃት ምን መረጃ አለ?

በፓኪስታን በምን ያህል ህፃናት የቤት ሠራተኞች ላይ ጥቃት እንደደረሰ የተሰባሰበ መረጃ ባይኖርም የተወሰኑ ሪፖርቶች ግን አሉ።

ሦስት በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች ባወጡት ሪፖርት ባለፉት አስር ዓመታት 140 የሚሆኑ ህፃናት የቤት ሠራተኞች ተሰቃይተዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተደፍረዋል፣ ወይም ተገድለዋል።

እነዚህ ሪፖርቶች ማጣቀሻ ያደረጉት የጋዜጣ ፅሁፎችን ከመሆኑ አንፃር ግምቶችን የያዙ ናቸው። በርካታ አቅማቸው ደካማ የሆኑ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ጥቃት በሚደርስባቸው ሰዓት በፍራቻ፣ አንዳንድ ጊዜም በጉቦ በመደለል ሪፖርት እንደማያደርጉ መረጃዎች ያሳያሉ።

ነገር ግን አንዳንድ ጥቃቶች ከዚህ ሁሉ አምልጠው ወደ ሕዝቡ ጆሮ ይደርሳሉ። በጎርጎሳውያኑ 2016 ጣይባ የተባለች የአስር ዓመት ህፃን የቤት ሠራተኛ ፊቷ በደም ተለውሶ እንዲሁም አይኖቿ አብጠው የሚያሳይ ፎቶ መውጣቱን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ቁጣን አስከትሏል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

በአስር አመቷ ጣይባ ድብደባና እንግልት በመፈፀም ለእስር የተዳረጉት ዳኛና ባለቤቱ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, በዓስር አመቷ ጣይባ ድብደባና እንግልት በመፈፀም ለእስር የተዳረጉት ዳኛና ባለቤቱ

ህፃኗ ጣይባ በፑንጃብ ግዛት ከሚገኝ መንደር ሲሆን የመጣችው በአንድ የፍርድ ቤት ዳኛም ቤት በቤት ሠራተኝነት ታገለግል ነበር።

በዳኛው ባለቤት ጥቃቅን በሆኑ ምክንያቶች ለምሳሌ መጥረጊያ በመጥፋቱ ሰበብ ከፍተኛ ድብደባና ስቃይም በተደጋጋሚም ይደርስባት ነበር።

የዳኛው ጎረቤቶች በህፃኗ ላይ የሚታዩ ቁስለቶችን በማየት ለባለስልጣናቱ አሳወቁ።

ዳኛውና ባለቤቱ ለእስር ብትዳረግም ይግባኝ በመጠየቃቸው የእስር ጊዜው ተቀንሶላታል።

በፓኪስታን ምን ያህል ህፃናት የቤት ራተኞች ይገኛሉ?

በፓኪስታን የሚገኙ ህፃናት የቤት ሠራተኞች ቁጥር በመቶ ሺህዎች እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በአገሪቱም በርካታ የቤት ሠራተኛ አስቀጣሪ ድርጅቶች በገጠሪቱ ፓኪስታን የሚገኙ ሲሆን በከተሞች ላሉ ሃብታሞችም ህፃናት የቤት ሠራተኞችን ይልካሉ።

በጎርጎሳውያኑ 2004 የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መሰረት 264 ሺህ የሚሆኑ ህፃናት የቤት ሠራተኞች ተቀጥረው እንደሚገኙ 'ዶን' የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።

ይህ አሃዝ ከአስራ ስድስት ዓመታት በፊት ከመሆኑ አንፃር የአገሪቱ የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የድህነት ማሻቀብ፣ በግጭቶችና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ምክንያት የተከሰተው መፈናቀል ያስከተለው ጫና ቁጥሩን በበርካታ እጥፍ እንዳሳደገው እየተነገረ ነው።

ከፓኪስታን አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር ውስጥ 50 ሚሊዮን የሚሆኑት ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ናቸው።

ከእነዚህም ውስጥ አምስት ሚሊዮን የሚሆኑት መንግሥት የሚደጉማቸው ሲሆን፤ ከሦስት እስከ ስድስት ሚሊዮን የሚገመቱት ደግሞ ጎዳና ላይ የሚኖሩ ወይም ቋሚ አድራሻ የሌላቸውና በህዝብ ቁጥር ውስጥም ያልተካተቱ ናቸው።

ከዚህም በተጨማሪ አስር ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በቀን ሥራ የሚተዳደሩ ናቸው።

በቅርቡም መንግሥት ባወጣው መረጃ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በርካታ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ከመቆማቸው በተጨማሪ አስር ሚሊዮን ፓኪስታናውያንን ከድህነት ወለል በታች አድርጓቸዋል።