ኮሮና ቫይረስ: የትንሳኤ በአል በአለም ላይ እንዴት እየተከበረ ነው?

ታትሟል

ከተሞች በተዘጉበት ወቅት፣ ሰዎች ከበሮቻቸው ማለፍ በማይችሉበት በዚህ ወቅት የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በአልን አድርገውት በማያውቁት ሁኔታ እያከበሩ ነው።

አንዳንድ ካህናት ወና በሆኑ ቤተ ክርስቲያኖች ላይ ልክ እንደቀድሞው ለተሰበሰው ህዝብ በሚሰብኩበት ጉልበት ካሜራውን እየተመለከቱ ይሰብካሉ።

ብዙዎች ቤታቸው ተቀምጠውም በስልክ እንዲሁም በቴሌቪዥናቸው መስኮቶቸች በቀጥታ አገልግሎቱን ይከታተላሉ።

በአንዳንድ ሃገራት ግን የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ ስርጭትን ለመቆጣጠር የወጡትን አስገዳጅ ህጎች ችላ በማለት የትንሳኤ በአልን እንደ ቀድሞው ለማክበር እየሞከሩ ነው።

እሰቲ የተወሰኑትን አገራት የትንሳኤ በአል አከባበር በፎቶ እንቃኝ

በደቡብ ቡካሬስ ሄራሲቲ መንደር በምትገኝ ቤተክርስቲያን የሆሳዕና በአል አከባበር

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, በሮማንያ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አማኞች የሆሳዕና በአልን ሲያከብሩ
በፊሊፒንሷ ኬዎዞን ከተማ ልክ እንደ አብዛኛው አገራት የካቶሊክ ካህናት የቅዳሴ ስነስርአታቸውን በስልክ በመቅረፅ በቀጥታ ተላልፏል።

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በፊሊፒንሷ ኬዎዞን ከተማ ልክ እንደ አብዛኛው አገራት የካቶሊክ ካህናት የቅዳሴ ስነስርአታቸውን በስልክ በመቅረፅ በቀጥታ ተላልፏል።
በአውስትራሊያዋ ሜልቦርን የቤተክርስቲያን አገልግሎትን በቤታቸው ሆነው በቴሌቪዥን ሲከታተሉ

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በአውስትራሊያዋ ሜልቦርን የቤተክርስቲያን አገልግሎትን በቤታቸው ሆነው በቴሌቪዥን ሲከታተሉ
በደቡብ ኮሪያዋ መዲና ሲዎል ፓስተሮች የፊት ጭምብል አጥልቀው በመስበክ ላይ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በደቡብ ኮሪያዋ መዲና ሲዎል ፓስተሮች የፊት ጭምብል አጥልቀው በመስበክ ላይ
በቤላሩስ መንግሥት ቤት የመቀመጥ ውሳኔውን በማላላት የካቶሊክ አማኞች ቤተክርስቲያን ሄደው የትንሳኤ በአልን እንዲያከብሩ ፈቅዶላቸዋል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በቤላሩስ መንግሥት ቤት የመቀመጥ ውሳኔውን በማላላት የካቶሊክ አማኞች ቤተክርስቲያን ሄደው የትንሳኤ በአልን እንዲያከብሩ ፈቅዶላቸዋል።
አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ በሆነባት አለም የጀርመን ካህናት መገኘት የማይችሉትን አማኞች ፎቶ በመስቀል የትንሳኤ በአልን ዘክረዋል።

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ በሆነባት አለም የጀርመን ካህናት መገኘት የማይችሉትን አማኞች ፎቶ በመስቀል የትንሳኤ በአልን ዘክረዋል።
በፖላንዷ ከተማ ዛኮፔን ካህናት በሰረገላ ላይ ተጭነው ፀበል እየረጩ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በፖላንዷ ከተማ ዛኮፔን ካህናት በሰረገላ ላይ ተጭነው ፀበል እየረጩ ነበር።
በቺሊዋ መዲና ሳንቲያጎ አንድ ካህን በመኪና ተጭኖ ቡራኬ ላላፊው ላግዳሚው እየሰጠ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, በቺሊዋ መዲና ሳንቲያጎ አንድ ካህን በመኪና ተጭኖ ቡራኬ ላላፊው ላግዳሚው እየሰጠ ነበር።