በመንጃ ፈቃድ ፍተና ላይ እናቱን መስሎ የተፈተነው ብራዚላዊ ታሰረ

ታትሟል

በሰሜን ብራዚል እናቱን እናቱ ለመምሰል አለባበሱን ቀይሮ የመንጃ ፍቃድ ፈተና የተፈተነው የ43 ዓመቱ ብራዚላዊ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

የሄትሮ ስኪያቮ እናት የሆኑት የ60 ዓመቷ ማሪያ፤ የመንጃ ፍቃድ ፈተናቸውን ሦስት ጊዜ ያህል ወድቀዋል። በዚህም ምክንያት ነው መካኒኩ ልጃቸው ሊፈተንላቸው የወሰነው።

እቅዱ እንዲሰምርለትም በአበባ ባጌጠ አልባሳት ተውቦ፣ ጥፍሮቹን በጥፍር ቀለም አስጊጦ፣ ሜካፕ እና አርቲፊሻል ፀጉር በማድረግ በተባለው ስፍራ መኪናውን በማሽከርከር ፈተናውን ወሰደ።

ይሁን እንጅ በተሽከርካሪው መቀመጫ ላይ ያለችው ሴት፤ በመታወቂያዋ ላይ ያለችው ሴት እንዳልሆነች ጥርጣሬዎች ነገሱ።

መርማሪ አሊን ሜንዶነካ "ግለሰቡ እናቱን ለመምሰል የሚችለውን ሁል አድርጓል፤ ጥፍሮቹ በጥፍር ቀለም ተውበዋል፣ በሜካፕ ፊቱን አሰማምሯል፣ የሴቶች ጌጣጌጥ አድርጓል" ብለዋል።

በዚህም የተነሳ ሌላን ሰው በመምሰል በሠራው የማጭበርበር ወንጀል ፖሊስ ተጠርቶ በቁጥጥር ሥር አውሎታል።

በቁጥጥር ሥር የሚገኘው ስኪያቮ እናቱ ይህንን እቅዱን ቀድመው እንደማያውቁ ተናግሯል።