የአምስት ዓመቱ ታዳጊ በማደጎ ሲሰጥ እንዲታዘቡ የክፍል ጓደኞቹን በሙሉ ጋበዘ

የፎቶው ባለመብት, Kent County court
ታትሟል
ነዋሪነቱ አሜሪካ ሚቺጋን የሆነው የአምስት ዓመቱ ታዳጊ ማይክል በማደጎ ሲሰጥ እንዲታዘቡ መላው የክፍል ጓደኞቹን ጋበዘ።
ማይክል ሐሙስ ጠዋት ላይ አዲሱን የቤተሰብ አባላቱን ተቀላቅሏል።
ማይክል በማደጎ ከሚወስዱት አዲስ ወላጆቹ ጋር ፍርድ ቤት ውስጥ ዘና ብሎ ተቀምጦ የሚያሳየው ምስል በርካቶች ተጋርተውታል።
ከማይክል ጀርባ ተቀምጠው ሥነ-ሥርዓቱን ሲከታተሉ የነበሩት የክፍል ጓደኞቹ ከወረቀት የተሰሩ የልብ ቀርጾችን ይዘው ለማይክል አጋርነታቸውን እና ፍቅራቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከተገኙት ህጻናት መካከል አንድ ስቲቨን የተባለ ታዳጊ "ማይክል የልብ ጓደኛዬ ነው" በማለት ለምን በሥፍራው እንደተገኘ ተናግሯል። ሊሊይ የተባለች ሌላ የክፍል ጓደኛው ደግሞ "ስሜ ሊሊ ነው ማይክልን እወደዋለሁ" ብላለች።
አዲሶቹ የማይክል ወላጆች ማይክልን ለማሳደግ ሥነ-ሥርዓቱን እንዳጠናቀቁ፤ ዳኛው ማይክል ለማደጎ እንዲሰጥ በመዶሻቸው ሲያረጋግጡ በፍርድ ቤቱ ክፍል ውስጥ የነበሩት የማይይክል የክልፍ ጓደኞች እና መምህራን በደስታ አጨብጭበዋል።








