ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የማክሰኞ ምሽት አጫጭር ዜናዎች
ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ የማክሰኞ ምሽት አጫጭር ዜናዎች።
ታይላንድ
አንድ ሚሊየነር እንግሊዛዊ እና ባለቤታቸው በታይላንድ ተገድለው ተገኙ።
አለን ሆግ እና ኖደ ሱዳይን በቅጥር ነፍሰ ገዳይ እጅ ሳይገደሉ እንዳልቀረ ፖሊስ ተናግሯል።
ሕንድ
በህንድ ጉጅራት 11 አንበሶች በጥቂት ቀናት ውስጥ መሞታቸውን ተከትሎ ምርመራ ተጀምሯል።
ባለስልጣናት አንበሶቹ ከሌላ ቦታ በመጣ ሌላ የአንበሳ መንጋ በግዛት ማስፋፋት ጠብ ሳይገድሏቸው እንዳልቀረ ጠርጥረዋል።
ስዊዲን
ግራዘመሙ የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር የእንደራሴዎች ምክር ቤት ድጋፍን በመጣታቸው ከስልጣን ሊለቁ ነው።
ፀረ ስደተኛ የሆነው የስዊድን ዲሞክራት ህብረት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማወረድ ለተደረገውን ዘመቻ ድጋፍ ሰጥቷኣል።
ደቡብ አፍሪካ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንታ ታቦ ኤምቤኬ የሀገሪቱን ገዢ የፖለቲካ ፓርቲ ተቹ።
ኤምቤኬ አፍሪካ ብሄራዊ ሸንጎ በምህፃሩ ኤ ኤን ሲ ወደ ለየለት ጥቁር ፓርቲ እየተለወጠ ነው፣ዘር አግላይ ያልነበረውን እንቅስቃሴውን እየተወ መሆኑን ጠቅሰው ተችተውታል።
እንግሊዝ
የእንግሊዝ የባንክ ስርዓት በአጭበርባሪዎች እየተፈተነ እንደሆነ አንድ ተቋም ተናገረ።
Industry group UK የተሰኘው ተቋም ይፋ እንዳደረገው በ2018 የጎረጎሳዊያኑ ዘመን ግማሽ ዓመት ብቻ የበይነ መረብ ኪስ አውላቂዎች ግማሽ ቢሊየን ዶላር ከደንበኞች መንትፈዋል።
ፖርቹጋል
400 ዓመት ያስቆጠረ የመርከብ ፍርስራሽ በፖርቹጋል የባህር ዳርቻ ተገኘ።
የፖርቹጋል መንግስት፣የባህር ሃይል እና ኖቫ ዩኒቨርሰቲ ያቋቋሙት ተመራማሪ ግብረ ሃይል ሃላፊ ዮርግ ፌርየር ግኝቱን «የ10 ዓመቱ ግሩም ግኝት» ሲሉ አሞካሽተውታል።
ሳዑዲ አረቢያ
ሳውዲ ሁለቱን ቅዱስ ከተሞች የሚያገኛኝ እጅግ ፈጣን ባቡር አስመረቀች።
መካ እና መዲናን የሚያገናኘው ባቡር በሰዓት 300 ኪሜትር የሚምዘገዘግ ሲሆን በቀጣይ ሰኞ ስራ ይጀምራል ተብሏል።