ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አፕል ሆም አይፖደ፣ አማዞን ኤኮ፣ ጉግል ሆም እና ሌሎችንም ወስደን 7 ስፒከሮችን ፈተንን
ላለፉት አራት ሳምንታት የአምባገነኖች ቅዠት ውስጥ ነው የኖርኩት። የምናገረውን ነገር በአጠቃላይ መጠንቀቅ አለብኝ ምክንያቱም 'እነርሱ' ሁሌም ይሰሙኛል። እነርሱ ስል ደግሞ አሌክሳና ሲሪንና ጉግል ናቸው።
7 የተለያዩ ስማርተ ስፒከሮችን በአንድ ቤት ውስጥ አስቀምጠን የዕለተለት ኑሮዋችንንና የምናዳምጥበትን መንገድ እንዴት እንደሚቀይሩት ማወቁ ጥሩ ሃሳብ ሆኖ ታየን።
በወቅቱ በጣም ረዱኝ። ብስኩት ከጨረስን አንዳችን ጮክ ብለን "ሲሪ የሆብ ኖብን ሱቆች አድራሻ" ስንል በስልካችን ላይ መልእክት ይመጣልናል።
በስቶርም ኤማ ወቅት ልጆቻችን አሌክሳን ድመት የምታሰማው ድምፅ እንዴት ያለ ነው እያሉ ሲጫወቱ ጉግል የተሰረዙ የባቡር ጉዞዎቼን በወቅቱ በማሳወቅ ረድቶኛል።
ጥሩው ነገር የትኞቹም መሳሪያዎች በድንገት በደረቅ ለሊት መሳቅ አልጀመሩም ነገር ግን ሁሉም ያልተለመደ ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይሉም።
አንድ ጊዜ አሌክሳን "የመን የአየር ሁኔታው እንዴት ያለ ነው ስል ጠየኳት" ዳስ ቬተር በጀርመንኛ የአየር ሁኔታ ማለት ነው የሚል ምላሽ አገኘሁ።
ጉግልን "በማዕድ ቤቱ ውስጥ ሙዚቃ እንዲያጫውትልኝ " ስጠይቅ፣ ምላሹን የሰጠኝ የሊ ብሪስን ዘፈኞች በመክፈት ነበር።
የትኛው ስማርት ረዳት ምርጥ እንደሆነ ለማወቅ እያንዳንዱን ስፒከር 50 ጥያቄዎች ስለሙዚቃ፣ ስለ ስፖርት እና ጠቅላላ ዕውቀት ጥያቄ በማዘጋጀት ለፈተና አስቀመጥኳቸው። ልክ እንደ ጥሩ የጥያቄና መልስ ውድድር የመጀመሪያ መልሳቸውን ብቻ ነው የምቀበለው።
አሌክሳ 37 ጥያቄዎችን በትክክል በመመለስ ቀዳሚ ሆነች ጎግል 32 ሲሪ 27 በመመለስ ይከተላሉ።
የአፕል ረዳት ከሌሎች አፖች ጋር መጠዓመር አቅቶት ተቸግሮ ነበር። ያ ማለት ደግሞ ቀን መቁጠሪየዓዬን ማንበብም ሆነ የምግብ አበሳሰል ዝርዝር መሚያዎችን ማንበብ አይችልም ማለት ነው።
ከሙዚቃ አንፃር ካየነው ሲሪን የሚያክላት የለም።
ለምሳሌ ሆምፓድ ብቻ ነው ቀጣዩን የጀምስ ቦንድ ሙዚቃን እንዲያጫውት ተጠይቆ ማጫወት የቻለው። ሌሎቹ ግን የጀምስ ቦንድ ፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ ሲፈልጉ ሳይሳካላቸው ቀርቷል
የትኞችም ቢሆኑ ያለችግር የተጠየቁትን ባጠቃላይ ማከናወን አልሆነላቸውም። ቢሆንም ግን ቀጥሎ ከእርስዎ የሕእወት ዘይቤ ጋር አብሮ የሚሄድ ስፒከር መምረጥ እንዲችሉ ዝርዝሩን አቅርበናል።
አፕል ሆምፓድ (319 ፓውንድ)
አፕል የስማርት ስፒከርን ገበያውን ዘግይቶ ነው የተቀላቀለው። ይህ ግን ከስንፍና አልነበረም። ሆም ፖድ ከ 2012 ጀምሮ እየተሠራ ነበር።
በተለይ ደግሞ ይህ ስፒከር አኩስቲክ ሙዚቃዎችን ጥርት አድርጎ ነው የሚያሰማው። የረጂና ስፔክተርን ሳምሰን የተሰኘውን ሙዚቃ በሆም ፖድ ስሰማው እያንዳንዱን የሙዚቃ መሳሪያ ለመለየት በሚያስችል መልኩ ነበር የሚያሰማው።
በተለይ ደግሞ የፒያኖውን ድምጽ አስገራሚ አድርጎ ነበር የሚያወጣው። እንደ ሰቲቪ ወንደር ላሉ ፈጠን ላሉ ዘፈኖች ደግሞ የድራሙንና አንዳንድ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በትክክል ለማሰማት ሲቸገር ተመልክቼዋለው።
አንድ መረሳት የሌለበት ጠቃሚ ነጥብ ሆምፖድን በቀላሉ ከአይፎን አልያም ከአይፓድ ጋር ለማገናኘት ካልሆነ በሌሎች መገልጌኣዎች መጠቀም አይቻልም።
አማዞን ኤኮ ፕላስ (139 ፓውንድ )
ምናልባት ብርሃን ማውጣት የሚችል ስፒክር መጠቀም የሚፈልጉ ከሆነ የአማዞን ኤኮ ፕላስ ምርጫዎ መሆን አለበት።
ስፒከሩ በቤትዎ ውስጥ የሚገኙ ማንኛውም አይነት መገልገያዎችን በመጠቀም ቤትዎን አስደሳችና ተወዳጅ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ ነው። ሌላው ቢቀር በርቀት መቆጣጠሪያ የሚሰራ መጋረጃዎን ችምር በዚህ ስፒከር ማዘዝ ይችላሉ።
ሙዚቃን በማጫወት ረገድ ደግሞ አማዞን ኤኮ ፕላስ ከሌሎቹ ስፒከሮች ጋር ተወዳዳሪ ግን እጅግ ላያስገርም የሚችል አይነት ነው። ምናልባት በማብሴኣ ክፍል ውስጥ ያለውን ስፒከር ተክቶ ሊሰራ ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን የምንወዳቸውን ሙዚቃዎች በተመስጦ ለመስማት ተመራጭ የሚሆን ስፒከር አይደለም።
አልቲሜት ኢርስ ሜጋብላስት (199 ፓውንድ)
አልቲሜት ኢርስ ሜጋብላስት ረጅም እና አስደሳች የሆነ ስፒከር ነው። በተለያዩ ቀለም አማራጮችም መገኘቱ ደግሞ ይበልጥ ተወዳጅ የደርገዋል።
ለጆሮ የሚስማማና ሙዚቃዎችን በደንብ ለማጣጣም የሚያስችል ስፒከር ሆኖ አግኝቼዋለው። ይህንን ስፒከር በመጠቀም ከአሌክሳ ጋር በማገናኘት ከአማዞን ሙዚቃ ማጫወትም ያስችላል።
አልይም ደግሞ ከስልክዎ በቀትታ በብሉቱዝ በማገናኘት የሚወዷቸውን ሙዚቃዎች ማጫወት ይችላሉ።
በቤትዎ ውስጥ ጥሩ የሆነ የድምጽ መገልገያዎች ካለዎት ከሌሎቹ አንጻር ረከስ የሚለውን (በአሁኑ ሰአት 39 ፓውንድ )አማዞን ኤኮ ዶት ገዝተው ከበፊቶቹ ሰፒከሮችና ኤሌክሮኒክ መሳሪያዎች ጋር ማገናኘት ይችላሉ።