ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በይፋ አቋረጠች

የፎቶው ባለመብት, EPA
የሩሲያን ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ ኪዬቭ ከሞስኮ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በይፋ ማቋረጧን አስታወቀች።
ይህ የተገለጸው የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎደሚየር ዜሌኒስኪ በሰጡት መግለጫ ነው።
ፕሬዝደንቱ በዚህ መግለጫቸው ፍላጎት ያላቸውን የዩክሬን ዜጎች በሙሉ መንግሥታቸው እንደሚያስታጥቅ ተናግረዋል።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ለሲቪል ዜጎቿ መሠረታዊ ወታደራዊ ስልጠና ስትሰጥ ቆይታለች።














