ከዩክሬን የተገኙ የቅርብ ጊዜ ፎቶዎች
በመላው ዩክሬን ጦርነቱ እንደቀጠለ ሲሆን የሩሲያ ኃይሎች ወደ መዲናዋ ኪዬቭ መግባታቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች እየሸሹ ነው።
መሬት ላይ ተገኝተው ይህንን ቀውስ ከሚዘግቡ ጋዜጠኞች ካገኘናቸው ፎቶዎች መካከል የተወሰኑት እነሆ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአገራቸው ሠራዊት የኑክሌር ኃይል ‘በተለየ ሁኔታ በተጠንቀቅ’ እንዲቆም አዘዙ። ፕሬዝዳንት ፑቲን የአገራቸውን መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሹይጉን ጨምሮ ለከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፣ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ “ተገቢ ያልሆነ” እርምጃ እና “ሕገ ወጥ ማዕቀብ” መጣላቸውን ተናግረዋል።
በመላው ዩክሬን ጦርነቱ እንደቀጠለ ሲሆን የሩሲያ ኃይሎች ወደ መዲናዋ ኪዬቭ መግባታቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች እየሸሹ ነው።
መሬት ላይ ተገኝተው ይህንን ቀውስ ከሚዘግቡ ጋዜጠኞች ካገኘናቸው ፎቶዎች መካከል የተወሰኑት እነሆ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, AFP via Getty Images
በዩክሬን ውስጥ በርካታ ነገሮች እየተከሰቱ ሲሆን በቅርብ ጊዜ የተከሰቱትን በጥቂቱ እንመልከት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ 450 የሩስያ ወታደሮች እና 194 ዩክሬናውያን መገደላቸውን የዩናይትድ ኪንግደም የጦር ሃይሎች ሚኒስትር ጀምስ ሄፔ በፓርላማ ቀርበው አብራርተዋል።
በዩክሬን በኩል ከተገደሉት መካከል 57ቱ ሰላማዊ ዜጎች መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ረፋድ ላይ ከጠቀሰው የ25 ሲቪሊያን ሞት ሪፖርት ጋር ሲነፃፀር የሰላማዊ ዜጎች ሞት ከፍ ያለ መሆኑ ተነግሯል።
ጀምስ ሄፔ በተጨማሪም የዩናይትድ ኪንግደም ወታደሮች ወደ ኔቶ አጋር ኢስቶኒያ ከታቀደው ቀደም ብለው እንደተላኩና ከዩክሬን ወደ አጎራባች ሃገራት የሚፈናቀሉ ዜጎችንም ለመርዳት 1 ሺህ ወታደሮች በተጠባባቂ ላይ ይገኛሉ ብለዋል ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የዩክሬን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መዲናቸውን ከሩሲያ ኃይሎች ለመከላከል ወደ ኪዬቭ እየገቡ መሆናቸውን የዩክሬን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኪዬቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ቀደም ሲል ከተማዋ "በመከላከል ላይ ናት " ሲሉ ተደምጠዋል።
ተቀጣጣዮችን ማዘጋጀትን ጨምሮ የጦር መሳሪያ በመታጠቅ የኪዬቭ ነዋሪዎች የሩስያ ወታደሮችን ለመቋቋም የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ መንግሥት እየጠየቀ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ በዛሬው ዕለት፣ አርብ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት የሩሲያ አቻቸው በዩክሬን ላይ ያደረጉትን ወረራ "ታሪክን ማረም" ሲሉ ማድነቃቸውን የሶሪያ ፕሬዝዳንት መግለጫ አስታውቋል።
አሳድ አክለውም "በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ሁኔታ ወደ ከባድ ውድቅት የመራው የአሜሪካ እና የኔቶ የማበጣበጥ ፖሊሲ ነው" ሲሉም መናገራቸውን በክሬምሊን ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ የተለጠፈው መግለጫ አትቷል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የአሳድ ደጋፊ የሆኑ የመንግሥት ሃይሎችን በእጅጉ ይደግፉ እንደነበር ይታወሳል።
የሩሲያ ሚሳኤል በዩክሬን መዲና ኪዬቭ ሰሜናዊ ምዕራብ አካባቢ የሚገኙ የመኖሪያ ሰፈሮችን ሲመታ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቷል።
ቢቢሲ ያረጋገጠው ይህ ቪዲዮ የሩሲያ ሚሳኤል ከኪዬቭ ሰሜናዊ ምዕራብ በሚገኘው ቡቻ የመኖሪያ ሰፈሮችን ሲመታ ያሳያል።
ዩክሬን የሩስያ ወታደሮች በዋና ከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ኪዬቭ ገብተዋል ማለቷንም ተከትሎ ነው ይህ ቪዲዮ የወጣው።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪዬቭን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የዩክሬን መከላከያ ኃይል ማንኛውም ዜጋ እንዲዋጋ በትዊተር ገጹ ጥሪ አቅርቧል።
የወታደሮቹ አዛዥ መግለጫ በዚህ ውጊያ "የእድሜ ገደቦች የሉም" ብሏል- ይህም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችም ትግሉን እንዲቀላቀሉ ሊፈቀድ እንደሚችል ያሳያል ተብሏል።
ነገር ገን የመከላከያ ሚኒስትሩ አሌክሲ ሬዝኒኮቭ ባወጡት አዲስ መግለጫ የዕድሜ ገደብ የለውም ሲባል ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ የዕድሜ ባለጸጎችን እንደሆነም ጠቁሟል። በዚህ መግለጫ ላይ ዕድሜያቸው ያልደረሰ ታዳጊዎችን አይጠቅስም።
"ከዩክሬን ጦር ኃይሎች ጦር አዛዥ ጋር በመስማማት ከ60 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች በአርበኞች ሰራዊት እንዲሳተፉ ወስነናል። ይህ ጥሪ በአካልም ሆነ በሞራል ዝግጁ የሆኑትንና ጠላትን ለማሸነፍ የተነሳሱትን ሁሉ የዕድሜ ባለጸጎች ይመለከታል" በማለት የመከላከያ ሚኒስትሩ አስፍረዋል።

የፎቶው ባለመብት, fmprc.gov.cn
ቻይና የረዥም ጊዜ አጋሯ ሩሲያ፤ በዩክሬን ላይ ወረራን ብትፈጽምም የሞስኮን እርምጃ መቃወምን አልመረጠችም።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን “ወረራ” ብሎ ከመጥራት ተቆጥቧል።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ምንም እንኳ ቻይና የሁሉንም አገራት ሉዓላዊ የግዛት አንድነትን ብታከብርም “ምክንያታዊ የሆነውን የሩሲያን የደኅንነት ስጋት” ትገነዘባለች ብለዋል።
ቃል አቀባዩ አሁም የዩክሬን ቀውስን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት እድሉ አለ ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ቀውሱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ንግግር እንዴት ሊደረግ እንደሚችል ምንም አላሉም።
በተጨማሪም ሩሲያ እውቅና ስለሰጠቻቸው ስለ ሁለቱ የዩክሬን ግዛቶች በተመለከተ የቻይና አቋም ምን እንደሆነ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ፖላንድ ድንበር እንዲሻገሩ በጀርመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
ኤምባሲው ዜጎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ፖላንድ አቋርጠው መግባት እንዲችሉ ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሁንታ ማግኘቱን አስታውቋል።
በዚህም መሠረት በዩክሬን ያሉት ዜጎች በፍጥነት ወደ ፖላንድ እንዲሻገሩ፣ ቀጥሎም ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ ኤምባሲው ጠይቋል።
በአሁኑ ወቅት ዩክሬን ውስጥ ስላሉበት ሁኔታ ቢቢሲ ያናገራት በኪዬቭ ያለችው ተማሪ እሌኒ አብሮም እንደገለጸችው፣ ሁሉም ወዴት እንደሚሄዱ ግራ መጋባታቸውንና በጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ጠቁማ፤ የተወሰኑት ወደ ፖላንድ ድንበር መጓዛቸውን ተናግራለች።
ኤምባሲው ቀደም ሲል ዜጎች ከነበሩበት ቦታ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ ለደኅንነታቸው ሲባል በማንኛውም ጊዜ ለኤምባሲው በስልክ ቁጥር +491767269094 እናኢሜይል፡berlin.embassy@mfa.gov.etእንዲያሳውቁ ጥሪ አስተላልፎ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ሩሲያ የ2022 የቻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታን እንዳታስተናግድ ተከለከለች።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ሊካሄደ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የፍጻሜ ውድድር ወደ ሌላ ከተማ ተዘዋውሯል።
የእግር ኳስ ማኅበሩ የፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ ውድድሩን እንደምታስተናግድ አስታውቋል።
የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጨምሮ እንደገለጸው ወደፊት ዩክሬን እና ሩሲያ የሚያደርጉት የእግር ኳስ ግጥሚያዎች በገለልተኛ ስታዲየሞች የሚካሄዱ ይሆናል ብሏል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የሩሲያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የዩናይትድ ኪንግደም አየር መንገዶች አውሮፕላኖች በሩሲያ አየር ማረፊያዎች እንዳያርፉ እና የአገሪቱን የአየር ክልል እንዳይጠቀሙ ከለከለ።
ሩሲያ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው የዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናትን ውሳኔ ተከትሎ መሆኑን አስታውቃለች።
ትናንት ዩናይትድ ኪንግደም የሩሲያው ኤሮፍሎት አየር መንገድ በብሪታኒያ እንዳያርፍ ከልክላ ነበር።
በዚህ የሩሰያ መንግሥት ውሳኔ በረራዎችን ለመሰረዝ የተገደደው ብሪቲሽ አየር መንገድ፤ ለመንገደኞቹ የተሰረዙ በረራዎችን እንደሚያሳውቅ እና ለቲኬት የተከፈለ ገንዘብ እንደሚመልስ ገልጿል።
“ይህ በግልጽ ከቁጥጥራችን ውጪ ቢሆንም ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን” ብሏል አየር መንገዱ።
አየር መንገዱ በሳምንት ሦስት ጊዜ ከለንደን ወደ ሞስኮ በረራ ያደርግ ነበር።
በተመሳሳይ የሩሲያን ወረራ ተከትሎ የዩክሬን አየር ክልል ከትናንት ጀምሮ ለሲቪል በረራዎች ዝግ መደረጉ ይታወሳል።

የሩሲያ ኃይሎች ዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ መግባታቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አረጋገጡ።
የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር እንዳለው "የጠላት ኃይል" በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ ከሚገኘው የአገሪቱ ፓርላማ 9 ኪሎ ሜትር ብቻ ርቃ በምትገኘው የኪዬቭ ክፍል በሆነችው ኦቦሎን ወረዳ ውስጥ እንዳሉ አመልክቷል።
ባለሥልጣናት ነዋሪው የሩሲያ ኃይሎችን በቤት ውስጥ በሚሰራ ተቀጣጣይ ፈንጂ ጭምር እንዲጋፈጣቸው፣ ያልቻለ ደግሞ ወደ መጠለያዎች እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በከተማዋ ውስጥ ቀደም ሲል የጠመንጃ ተኩስ አሁን ደግሞ ከባድ ፍንዳታ ድምጽ እየተሰማ መሆኑን የቢቢሲ ዘጋቢ ከኪዬቭ ገልጿል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ ቪዲዮዎች ደግሞ የሩሲያ ታንኮች በኦቦሎን በኩል አቋርጠው ወደ ኪዬቭ ከተማ ማዕከላዊ ክፍል ሲያልፉ አሳይተዋል።
የአገሪቱ የመከላከያ ባለሥልጣናት እንዳረጋገጡት የሩሲያ ኃይሎች ወደ ከተማዋ የመኖሪያ አካባቢዎች ዘልቀው ገብተዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የሩሲያን ጥቃት ተከትሎ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዩክሬናውያን ጎረቤት አገር ፖላንድ ደርሰዋል።
ከ1ሺህ በላይ የዩክሬን ዜጎች በድንበር አቅራቢያ ከምትገኝ የፖላንድ ከተማ በባቡር መድረሳቸውን የፖላንድ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
አብዛኞቹ ስደተኞች በባቡር ጣቢያዎች እና በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሊቱን አሳልፈዋል ተብሏል።
በፖላንድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዩክሬን ማኅብረሰብ ይኖራል። አሃዞች ቢለያዩም በፖላንድ ከ1 አስከ 2 ሚሊዮን ዩክሬናውያን ይኖራሉ ይባላል።
በፖላንድ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ዩክሬናውያን ዘመዶቻቸውን ለመቀበል ወደ ድንበር ከተሞች በግል ተሸከርካሪዎቻቸው እየጎረፉ ስለመሆኑ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው።
የዩክሬን ጎረቤት አገራት በተፈናቃዮች ሊጥለቀለቁ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ትናንት አሳስቦ ነበር።
ሃንጋሪ እና ስሎቫኪያ ስደተኞችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ ለማስተናገድ ጦራቸውን ወደ ድንበር እንደሚልኩ አስታውቀዋል።
ጀርመን በበኩሏ ስደተኞችን ለሚቀበሉ አገራት የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እንደምታደርግ ትናንት ገልጻለች።

ዩክሬን ውስጥ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ በአገሪቱ በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ካሉበት ቦታ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ጀርመን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁ ተጠየቁ።
ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት ዩክሬን ውስጥ ስላሉበት ሁኔታ ቢቢሲ ያናገራት ተማሪ እሌኒ አብሮም እንደገለጸችው፣ ሁሉም ወዴት እንደሚሄዱ ግራ መጋባታቸውንና በጭንቀት ላይ መሆናቸውን ጠቁማ፤ የተወሰኑት ወደ ፖላንድ ድንበር መጓዛቸውን ተናግራለች።
ኤምባሲው እንዳለው ኢትዮጵያውያኑ ዩክሬን ውስጥ ባጋጠመው ችግር ምክንያት በመደበኛነት ከነበሩበት ቦታ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ ለደኅንነታቸው ሲሉ በማንኛውም ጊዜ ጀርመን በርሊን ውስጥ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁና ምክር እንዲያገኙ ጠይቋል።
ለዚህም የሚከተሉትን የሞባይል ስልክ ቁጥር እና የኢሜል አድራሻ ሰጥቷል ስልክ፡ +491767269094 ኢሜይል፡ berlin.embassy@mfa.gov.et

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በሶቪየት ሕብረት ውስጥ አንድ አካል ነበረች።
የሶቪየት ሕብረት መፍረስን ተከትሎ እአአ 1991 ላይ ዩክሬን ነጻ አገር ሆነች።
በምሥራቅ አውሮፓ የምትገኘው ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ትዋሰናለች።
44 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ዩክሬን በቆዳ ስፋቷ ከአውሮፓ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ሩሲያ ደግሞ 144 ሚሊዮን ሕዝብ በመያዝ በቆዳ ስፋት በዓለም ቀዳሚዋ አገር ነች።
እአአ 2014 መጀመሪያ ላይ አፍቃሪ ሩሲያ የነበሩት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ከሥልጣን መነሳትን ተከትሎ ሞስኮ የዩክሬንን ግዛት በኃይል ይዛ ቆይታለች።
ከሞስኮ ጫና የበዛባት ኪዬቭ ጠንካራ ወዳጅ አገራትን ለማፍራት ፊቷን ወደ ምዕራባውያኑ አዙራለች።
ዩክሬን አሜሪካንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ አገራትን በአባልነት የያዘው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት አባል የመሆን ጽኑ ፍላጎት አላት።
ሞስኮ ግን ይህ እንዲሆን አትሻም።
የሩሲያን ወረራ ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት “ጠንካራ ነን። ለየትኛውም ነገር ዝግጁ ነን” በማለት አገራቸውን እንደሚከላከሉ ገልጸዋል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በዩናይትድ ኪንግድም የዩከሬን አምባሳደር ቫድያም ፕሬሰታኢኮ የሩሲያን ወረራ ‘ለመቀልበስ’ ምዕራባውያን እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል።
አምባሳደሩ "ኪዬቭ ለሞስኮ አንተንበረከከም" ካሉ በኋላ፤ የተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት ለአገራቸው አስቸኳይ ድጋፍ መስጠት አለባቸው ብለዋል።
“ዩናይትድ ኪንግደም እና ምዕራባውያኑ ቃል የገቡት አስቸኳይ፣ ወሳኝ እና ጠንካራ ማዕቀብ ሩሲያ ላይ እንዲጣል እንጠብቃለን። ሩሲያን ከስዊፍት የገንዝበ መላላኪያ ሥርዓት ማገድ በቂ አይደለም። ይህን ወረራ ለማስቆም ተጨማሪ እርምጃ ይጠይቃል” ብለዋል።
ምዕራባውያን ሞስኮን 'ስዊፍት' ከተባለው የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት አግደዋል።
ስዊፍት ከ200 በላይ በሆኑ አገራት፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ኩባንያዎች የፋይናንስ መልዕክቶችን ለመለዋወጥ የሚጠቀሙት የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ነው።
ሩሲያ ከስዊፍት መታገዷ፤ ባንኮቿ ከአገር ውጪ ካሉ ባንኮች ጋር የገንዘብ ዝውውር ማድረግን በእጅጉ አዳጋች ያደርግባቸዋል።