ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የፅ/ቤት ኃላፊ ሾሙ

በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ 47ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ወደ ዋይት ሐውስ ከመመለሳቸው በፊት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቻቸውን ለመሾም ተዘጋጅተዋል። ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በበኩላቸው ያልተቋጩ ሥራዎችን ጨርሰው ሥልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ አስታውቀዋል። ትራምፕ የዋይት ሐውስ ፅ/ቤት ኃላፊ ሹመዋል። ቢቢሲ አማርኛ የአሜሪካ ምርጫ ሂደትን የተመለከቱ ዘገባዎች በዚህ ገጽ በቀጥታ ያቀርባል።

ጭምቅ ሃሳብ

  • ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
  • የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ለትራምፕ ‘የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት’ አስተላለፉ
  • ትራምፕ “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” አሉ
  • ትራምፕ ፕሬዝዳንት ለመሆን ሲቃረቡ፣ ሪፐብሊካኖች በሁለቱም ምክር ቤቶች የበላይነት እየያዙ ነው
  • ሪፐብሊካኖች የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን ይቆጣጠራሉ- ትንበያ
  • የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጉ፤ ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው
  • ትራምፕ ወሳኝ የምትባለውን የሰሜን ካሮላይና ግዛትን አሸነፉ
  • የአሜሪካዊ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ውጤት እንደ ሩሲያ እና ቻይና ላሉ ኃያላን ሀገራት ምን ይፈይዳል?
  • የፕሬዚዳንታዊ እጩዎቹ የምርጫ ዘመቻ በእምነት ላይ የተመሰረተ ነው?
  • የአይዋ ግዛት ለምን የትኩረት ማዕከል ሆነች?
  • “የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” ካማላ ሃሪስ
  • ከምርጫው ቀን በፊት ከ70 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምጽ ሰጥቷል
  • እስካሁን ባለው ሂደት ከ78 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ድምጻቸውን የሰጡ ሲሆን ይህም ከአራት ዓመት በፊት የነበረውን የመጀመሪያ መራጮች ተሳትፎ ክብረ ወሰን የሰበረ ነው

የቀጥታ ሽፋን

  1. የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጉ፤ ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው

    የካማላ ሃሪስ ደጋፊዎች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    በአሜሪካ የመጨረሻዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች በአላስካ እና ሃዋይ ሲዘጉ እስካሁን ባሉ የቆጠራ ውጤቶች ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው።

    እስካሁን ባሉ የቆጠራ ውጤቶችን መሰረት ባደረጉ ትንበያዎች መሰረት ዶናልድ ትራምፕ 246 ኢሌክቶራል ኮሌጅ ድምጾችን እንዳገኙ ሲገመት የዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ ደግሞ 194 ኢሌክቶራል ኮሌጅ እንዳገኙ ይታመናል።አንድእጩ ዋይትሃውስን ለማሸነፍ 270 ኢሌክቶራልኮሌጅ ማግኘትአለበት።

    እስካሁን ድረስ በአሜሪካ ምርጫ ወሳኝ ከሚባሉት ውስጥ የሰሜን ካሮላይና እና ጆርጂያ ግዛቶችን ትራምፕ ማሸነፍ ችለዋል። እስካሁን ድረስ የአምስት ተጨማሪ ወሳኝ ግዛቶች ውጤት ባይታወቅም ቀደምት ትንበያዎች ትራምፕ በሁሉም እየመሩ እንደሆነ አሳይተዋል።.እነዚህስፍራዎች ካማላሃሪስ ወይምትራምፕ ሊያሸንፉባቸው የሚችሉ ተለዋዋጭነት ያላቸው ሲሆን የምርጫ ውጤቱንም የሚወስኑ እንደሆነ ተነግሯል።

    የዲሞክራት ደጋፊዎች እና የምርጫው ስትራቴጂስቶች “ተስፋ የመቁረጥ ስሜት” እየተሰማቸው እንደሆነ ለቢቢሲው የምርጫ ዘጋቢ ተናግረዋል። በፍሎሪዳ የትራምፕ መቀመጫ ደግሞ ከፍተኛ ደስታ እየተገለጸ እንደሆነ ተዘግቧል።

    የካማላ ሃሪስ ደጋፊዎች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የካማላ ሃሪስ ደጋፊዎች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

  2. ድሉ ወደ ትራምፕ እያጋደለ ነው

    የትራምፕ ደጋፊዎች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ገና ቢሆንም እስካሁን ባሉ ቆጠራዎችን መሰረት ባደረጉ ትንበያዎች ድሉ ወደ ሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ እያጋደለ ነው።

    ትራምፕ ከወሳኝ ግዛቶች መካከል የተጠበቀውን የሰሜን ካሮላይና ግዛት ያሸነፉ ሲሆን ሌላኛዋን ወሳኟን ጆርጂያ ግዛትን ማሸነፍ እንደቻሉ ትንበያዎች አሳይተዋል።

    የኢሌክቶራል ውጤትን የሚያሳየው ካርታ ትራምፕ ከአራት ዓመት በፊት ከነበረው በተለየ በአውሮፓውያኑ 2016 ያሸነፉበትን መስሏል።

    በመላው አሜሪካ ውጤታቸውን ይፋ ባደረጉት ግዛቶች የቀድሞው ፕሬዚዳንት በሚታይ ልዩነት እየመሩ እንደሆነ አሳይቷል።

    ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በከተሞች እና በከፊል ከተሞች መካከል ያገኙት ድምጽ ከዚህ ቀደም ጆ ባይደን ካገኙት ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ከትራምፕ ጋር ያላቸውን ልዩነት ማጥበብ አልቻሉም።

    የትራምፕ ደጋፊዎች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የትራምፕ ደጋፊዎች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

  3. ትራምፕ ወሳኝ የምትባለውን የሰሜን ካሮላይና ግዛትን አሸነፉ

    የትራምፕ ደጋፊዎች

    የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ወሳኝ ከሚባሉት መካከል የሰሜን ካሮላይናን ግዛት በማሸነፍ 16 ኢሌክቶራል ድምጽ ማግኘት ችለዋል።

    ፕሬዚዳንታዊ ውድድሩን ለማሸነፍ 270 ኢሌክቶራልኮሌጅ ድምጽማግኘት ለሚያስፈልጋቸው ትራምፕ ይህ መልካም ዜና ነው።

    ነገር ግን አብዛኞቹ የወሳኝ ግዛቶች ውጤት ገና ያልታወቀ ሲሆን በተለይም የዊስኮንሰን፣ ፔንሲልቫንያ እና ሚቺጋንን የያዙት ‘ረስት ቤልት ሲት’ ግዛትን የሚያሸንፉ ከሆነ ድሉ ወደ ካማላ ሃሪስ ሊያጋድል ይችላል̄።

    የሰሜን ካሮላይና ድል ለሪፐብሊካኖች ትልቅ ቢሆንም ግዛቲቱ ከዚህ በፊት ድምጽ ከምትሰጥበት ጋር ተመሳሳይ ነው። በአውሮፓውያኑ 2016 በነበረው ምርጫ በ3.66 በመቶ ልዩነት ያሸነፉ ሲሆን በ2020 ደግሞ ባነሰ 1.34 ማሸነፋቸው ይታወሳል።

  4. በጆርጂያ በሐሰተኛ የቦምብ ዛቻዎች የተነሳ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ምርጫ ተቋረጠ

    በአትላንታ መራጮች የምርጫ ወረቀታቸውን ስካን ለማድረግ ሲዘጋጁ

    የፎቶው ባለመብት, EPA-EFE/REX/SHUTTERSTOCK

    የምስሉ መግለጫ, በአትላንታ መራጮች የምርጫ ወረቀታቸውን ስካን ለማድረግ ሲዘጋጁ

    በጆርጂያ አምስት ሐሰተኛ የቦምብ ዛቻዎች ነበሩ ሲል የቢቢሲ የአሜሪካ ሚዲያ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ዘግቧል።

    የአካባቢው የምርጫ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ናዳይን ዊሊያምስ በዛቻው የተነሳ በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በግምት ለ30 ደቂቃዎች ቦታውን ለቀው ወጥተው ነበር ብሏል።

    አካባቢው አትላንታ ከተማን የሚያካትት ሲሆን፣ በሁለቱ ስጋቱ ተከስቶባቸው በነበሩ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ሰዓትን ለማራዘም የፍርድ ቤት ይሁንታን ለማግኘት እየተሞከረ እንደሆነ አስታውቋል።

    በተመሳሳይ ዜና በፔንሴልቫንያ እንዲሁ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መራጮች የምርጫ ወረቀታቸውን ስካን ማድረግ ባለመቻላቸው የተነሳ ለባከኑ ሰዓታት የምርጫ ሰዓቱን ለማራዘም ለፍርድ ቤት ጥያቄ መቅረቡ ተሰምቷል።

  5. የአሜሪካን ምርጫ የሚወስነው ምንድን ነው?

    አንዲት መራጭ ድምጽ እየሰጠች

    የፎቶው ባለመብት, AFP

    በአሜሪካ የፖለቲካ ታሪክ እንደዘንድሮው ምርጫ ፉክክሩ ጦዞ አያውቅም።

    ከዚህ ቀደም የተደረጉ ምርጫዎችን መለስ ብሎ ለሚያይ እኤአ በ2000 ጆርጅ ደብሊው ቡሽ በአል ጎር ላይ የተቀዳጁት ድል በፍሎሪዳ ባገኙት በትንሽ መቶዎች የሚቆጠር የአብላጫ ድምጽ እንደነበር ይረዳል።

    በአሜሪካ ሁሌም ምርጫው ለማን ያዘነበለ እንደሆነ የሚታወቅበት ዕድል አለ።

    በአውሮፓውያኑ 2016 የተካሄደው ምርጫ ላይ ግን ይህ ግምት የተዛባ ሆኖ ተገኝቷል።

    በዚያ ዓመት የመራጮችን አስተያየት የሚገምቱ ሁሉ ዕድል ፊቷን ወደ ሒላሪ ክሊንተን ታዞራለች ሲሉ ተንብየው ነበር።

    በኋላ እንደታየው ግን ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊ ሆነው ወጥተዋል።

    በአሁኑ ምርጫ ግን የምርጫው ውጤት ለሁለቱም ያደላ መሆኑን የሚያሳዩ ትንበያዎች በርካታ ናቸው።

    ማንም ደፍሮ አንዱ ያሸንፋል ሊል አልቻለም። ሙሉውን ዘገባ እዚህ ያንብቡ የአሜሪካን ምርጫ የሚወስነው ምንድን ነው?

  6. አሜሪካውያን ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በተጨማሪ ለሌሎች ጉዳዮችም ድምጽ እንሚሰጡ ያውቃሉ?

    መራጮች ለተለያዩ ጉዳዮች ድምጽ እንዲሰጡ የሚቀሰቅሱ ፖስተሮች

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, መራጮች ለተለያዩ ጉዳዮች ድምጽ እንዲሰጡ የሚቀሰቅሱ ፖስተሮች

    ባለፉት ወራት ስለ አሜሪካ ምርጫ ሲወራ ዋነኛው እና ብቸኛው ጉዳይ በካማላ ሃሪስ እና በዶናልድ ትራምፕ መካከል ስለሚደረገው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ነው። በእርግጥም ፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ለአሜሪካውያን መራጮች ዋነኛው ጉዳይ ነው። ነገር ግን መራጮች ለተጨማሪ ጉዳዮች ድምጽ ይሰጣሉ።

    በዛሬው ዕለት በሚጠናቀቀው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት አሜሪካውያን መራጮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣሉ። በዚህም መሠረት ግዛቶች በሚከተሉት ሕጎች እና የምክር ቤት መቀመጫዎች ላይ ድምጽ ይሰጣሉ።

    • ጽንስን የማቋረጥ መብትን በተመለከተ ከባድ ፉክክር የሚደረግባቸውን አሪዞና እና ኔቫዳን ጨምሮ በአስር ግዛቶች ውስጥ ድምጽ ይሰጣል።
    • ለአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አንድ ሦስተኛ መቀመጫዎች ማለትም ካሉት 100 መቀመጫዎች ለ34ቱ አባላትን ይመርጣሉ። በአሁኑ ወቅት ዲሞክራቶች በአንድ ድምጽ የበላይነት ሴኔቱን ይቆጣጠሩታል።
    • በየሁለት ዓመቱ ለሚመረጡት 435 የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ኮንግረስ) አባላት ምርጫ ይደረጋል። በአሁኑ ወቅት ሪፐብሊካን ጠባብ የበላይነት አላቸው።
    • ለመዝናኛነት እና ለህክምና አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውል የማሪዋና ዕጽ አጠቃቀምን በተመለከተ የፍሎሪዳ፣ ኔብራስካ፣ ሰሜን ካሮላይና እና ደቡብ ካሮላይና ነዋሪዎች ድምጽ ይሰጣሉ።
    • ምርጫን እና ድምጽ አሰጣጥን በተመለከተ ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል፤ በዚህም በአንዳንድ ግዛቶች መራጮች ምርጫዎች እንዴት መካሄድ እንዳለባቸው ውሳኔ ይሰጣሉ።

    ስለዚህም ምርጫው ከፕሬዝዳንት በተጨማሪ የሴኔት እና የኮንግረስ አባላትን ለመምረጥ እንዲሁም በአንዳንድ ግዛቶች ውስጥ ደግሞ ጽንስ ማቋረጥን፣ የዕጽ ሕጋዊ አጠቃቀምን እና ምርጫን በተመለከተ ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል።

  7. በአሜሪካ የድምጽ መስጫ ጣብያዎች ተከፍተዋል

    በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች መራጮች ድምጻቸውን መስጠት ጀምረዋል።

    ሰሜን ካሮላይና፣ ኢንዲያና፣ ኬንታኪ፣ ኒው ጀርሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ፍላዴልፊያ፣ ፔንሴልቫኒያ፣ ቨርጂኒያ፣ ጆርጂያ መራጮች ድምጻቸውን መስጠት ከጀመሩባቸው ግዛቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

    መራጮች በፔንሴልቫኒያ ሰልፍ ይዘው ይታያሉ
    የምስሉ መግለጫ, መራጮች በፔንሴልቫኒያ ድምጻቸውን ለመስጠት ሰልፍ ይዘው ይታያሉ
    በአትላንታ ጆርጂያ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ሲገቡ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, በአትላንታ ጆርጂያ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ሲገቡ
    በኒውዮርክ የመጀመሪያዎቹ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ተሰልፈው

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, በኒውዮርክ የመጀመሪያዎቹ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ተሰልፈው
    በኒውዮርክ የመጀመሪያዎቹ መራጮች ድምጻቸውን ሰጥተዋል

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    የምስሉ መግለጫ, በኒውዮርክ የመጀመሪያዎቹ መራጮች ድምጻቸውን ሰጥተዋል
  8. ሩሲያ በምርጫው እምነት እንዲጠፋ ጥረት እያደረገች ነው - የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች

    መጭበርበሩ ይቁም የሚል ፅሑፍ የያዘ አሜሪካዊ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በርካታ ታዋቂ አሜሪካዊያን ድምፃቸውን ለማን እንደሚሰጡ ይፋ እያደረጉ ነው። ታዋቂዋ ሙዚቀኛ ሌዲ ጋጋ ድምጿን ለካማላ ሃሪስ እንደምትሰጥ ይፋ ስታደርግ ጆ ሮጋን የተባለው ታዋቂ የፖድካስት ጋዜጠኛ ደግሞ ድጋፉን ለትራምፕ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

    ከዚህ ዜና ወጣ ስንል የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች “የውጭ ኃይሎች” የአሜሪካ ምርጫ እምነት እንዲያጣ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲል ወቅሰዋል።

    መሥሪያ ቤቶቹ ሩሲያን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ኃይሎች “ሕዝቡ በአሜሪካ ምርጫ ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር እና ክፍፍል እንዲሰፍን” ሙከራ እያደረጉ ነው ብለዋል።

    የብሔራዊ ደኅንነት ዳይሬክተር ቢሮ፣ ኤፍቢአይ እና የሳይበርሴኪዩሪቲ ኤጀንሲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች የምርጫ አስተባባሪዎች ላይ አመፅ እንዲነሳ እያደረጉ ነው እንዲሁም ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል ሐሰተኛ ዜና እያሰራጩ ነው ብለዋል።

    “በሩሲያ ተፅዕኖ ሥር ያሉ ቡድኖች” በቅርቡ የምርጫ አስተባባሪዎች በተለይ በቁልፍ ግዛቶች የምርጫ ሳጥኑን በመሙላት ምርጫውን ለማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል የሚል ሐሰተኛ ዜና መለጠፋቸውን መግለጫው ጠቅሷል።

    መግለጫው አክሎ በሚቀጥሉት ቀናት መሰል ዜናዎች የበለጠ ሊሰራጩ ይችላሉ የሚል ግምት እንዳለ አስታውቋል።

    መሥሪያ ቤቶቹ በጋራ ያወጡት መግለጫ ኢራን ለአሜሪካ “ከፍተኛ የውጭ ስጋት ናት” ይላል።

    ቴህራንም ሆነች ሞስኮው በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ ነው የሚለውን ዜና ያስተባብላሉ።

  9. ምርጫውን ካማላ ሃሪስ ወይም ዶናልድ ትራምፕ ሊያሸንፉ የሚችሉባቸው 10 ነጥቦች

    ሃሪስ እና ትራምፕ

    ሁለቱም ዕጩዎች ወሳኝ በሚባሉ ቦታዎች ደጋፊዎቻቸው በነቂስ ወጥተው እንዲደግፏቸው የተለያዩ የምርጫ ቅስቀሳዎች ሲያካሂዱ ቆይተዋል።

    ከሁለቱ ዕጩዎች አንዱ ይህን ታሪካዊ የተባለ ምርጫ ሊያሸንፉባቸው የሚችሉ 10 ነጥቦችን እነሆ።

  10. ሃሪስ ወይስ ትራምፕ? አሜሪካዊያን ድምፃቸውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል

    ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሃሪስ

    የአሜሪካ ምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን ቀርቧል። በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት አሜሪካዊያን ከእንቅልፋቸው ነቅተው ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ያመራሉ። ቀጣይ መሪያቸውንም ይመርጣሉ።

    ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት 82 ሚሊዮን ዜጎች መርጠዋል። በ2022 በዩናይትድ ስቴትስ 161 ሚሊዮን ሰዎች ድምፃቸውን ለመስጠት ተመዝግበው ነበር።

    የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳቸውን በሚሺጋን ግዛት አጠናቀዋል። ሚሺጋን ወሳኝ ከሚባሉት ሰባት ግዛቶች አንዷ ናት። በመጨረሻው የምርጫ ንግግራቸው ተቀናቃኛቸው ካማላ ሃሪስን “ጤና የሌላቸው ግራ ዘመም አክራሪ” ሲሉ ወርፈዋቸዋል።

    ትራምፕ ከንግግራቸው በኋላ ልጆቻቸውን ወደ መድረክ ጋብዘው ሲጨባበጡ፤ ለደጋፊዎቻቸው ሰላምታ ሲሰጡ ታይተዋል።

    የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩዋ ካማላ ሃሪስ በበኩላቸው የመጨረሻ የቅስቀሳ ንግግራቸውን ያደረጉት እጅግ ቁልፍ በምትባለው ፔንሲልቬኒያ ግዛት ነው። ሃሪስ የተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕን ስም ከመጥቀስ ተቆጥበው፤ ወጣት መራጮች ላይ ትኩረት ያደረገ ንግግር አሰምተዋል።

    ቀጥሎ ምን ይሆናል? አብዛኛው የአሜሪካ ግዛት በተለይ ምስራቁ ክፍል አሁን እንቅልፍ ላይ ነው። ይህ ማለት በሚቀጥሉት ሰዓታት ምን ዓይነት ዜና ላይመጣ ይችላል ማለት ነው።

  11. ስድስት መራጮች ባሏት ከተማ ትራምፕ እና ሃሪስ እኩል ድምፅ አገኙ

    በዲክስቪል ኖች የተካሄደው ምርጫ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የምስሉ መግለጫ, በአነስተኛዋ ከተማ በተካሄደው ምርጫ ትራምፕ እና ሃሪስ እኩል ድምፅ አግኝተዋል

    ዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ እና ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳቸውን አጠናቀዋል።

    የምርጫ ኮሮጆ ለድምፅ ሰጭዎች ክፍት ያደረገችው የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ከተማ ኒው ሀምፕሸር ግዛት የምትገኘው ዲክስቪል ኖች ናት።

    በከተማዋ የምርጫ ጣቢያዎች የተከፈቱት በአካካቢው ሰዓት አቆጣጠር ሰኞ እኩለ ለሊት ነው። ከተማዋ ሁሌም የምርጫ ጣቢያዎቿን የምትከፍተው እኩለ ለሊት ነው። የምርጫ ጣቢያው ሁሉም መራጮች ድምፃቸውን እስኪሰጡ ክፍት ሆኖ ቆይቷል።

    ባለፈው ጥር በከተማዋ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሲካሄድ ድምፅ ለመስጠት የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር 6 ነበር።

    የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ኒው ሀምፕሸር ግዛት የአሜሪካ ምርጫ ምን ሊመስል እንደሚችል ፍንጭ የምትሰጥ ግዛት ናት ይሏታል።

    ስድስቱም የአካባቢው ነዋሪዎች ድምፅ ከሰጡ በኋላ ቆጠራ የተደረገ ሲሆን ሃሪስ 3 ትራምፕ 3 ድምፅ አግኝተዋል።

  12. ትራምፕ በመጨረሻው የቅስቀሳ ንግግራቸው ሃሪስን ወረፉ

    ዕጩው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ

    የፎቶው ባለመብት, EPA-EFE/REX/SHUTTERSTOCK

    ዶናልድ ትራምፕ በሚሺጋን ግዛት የመጨረሻ የቅስቀሳ ንግግራቸውን አድርገዋል። መድረክ ላይ መገኘት ከነበረባቸው ጊዜ ሁለት ሰዓት አርፍደው የመጡት ትራምፕ ከደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

    ካማላ ሃሪስ በመጨረሻዎቹ ቀናት የምርጫ ቅስቀሳቸው የዶናልድ ትራምፕን ስም ከማንሳት ተቆጥበው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ በተቃራኒው ተቀናቃኛቸውን “አክራሪ ግራ ዘመም” ሲሉ ወርፈዋቸዋል።

    የማክሰኞውን ምርጫ እንደሚያሸንፉ ለደጋፊዎቻቸው የተናገሩት ትራምፕ “ይህ በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ትልቁ ድል ይሆናል” ብለዋል።

    ዶናልድት ትራምፕ በ2016 እና በ2020 ያደረጓቸውን የምርጫ ቅስቀሳቸዎች ያጠናቀቁት እዚሁ ሚሺጋን ግዛት ግራንዳ ራፒድስ በተባለው ሥፍራ ነው።

    “በአንድ ቀን አራት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ እጅግ ከባድ ነው” ብለው ነገር ግን የደጋፊዎቻቸው አቀባበል ልዩ እንደሆነ ተናግረዋል።

    የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 4፡30 ይመጣሉ ቢባልም ለሰዓታት አርፍደው ደርሰው እስከ ለሊቱ 8፡00 ገደማ ቆይተዋል።

    ትራምፕ ምጣኔ ሀብት እና የስደተኞች ጉዳይ ላይ ንግግር አድርገዋል።

    አሁን ያላችሁበት ሁኔታ እና ከአራት ዓመታት በፊት የነበረው ጊዜ እንዴት ነው? የሚል ጥያቄ ለደጋፊዎቻቸው አቅርበዋል።

    “ለእናንተ እና ለተቀረው የአሜሪካ ሕዝብ የማስተላልፈው አንድ ነገር ቢኖር እንዲህ እየኖራችሁ መቀጠል የለባችሁም የሚል ነው” ብለዋል።

  13. “ቀጣይዋ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ተዘጋጅቻለሁ” - ካማላ ሃሪስ

    ዕጩ ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስ

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    ዲሞክራቷ ዕጩ ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስ የመጨረሻ የምርጫ ቅስቀሳቸውን በፊላደልፊያ አድርገዋል።

    ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ንግግር ያደረጉት ሃሪስ “አሜሪካ ምን ማለት እንደሆነች፤ አንድ ላይ እንደሆንን” ስላሳያችሁኝ አመሰግናለሁ ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ምስጋና ችረዋል።

    “የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻችን ምን ማሳካት እንደምንፈልግ፤ ሕልማችን ምን እንደሆነ እና የአሜሪካ ሕዝብ ፍላጎትን ያሳየ ነው። ትልቅ ተስፋ አለን፤ አንድ ላይ ሆነን ምን ማድረግ እንደምንችል ለማሳየት ጓጉተናል” ብለዋል።

    ሃሪስ አክለው መራጮች “ለዓመታት በፍርሀት እና በክፍፍል የታመሰውን ፖለቲካ ለመቀየር ዕድሉ አላቸው” ሲሉ ተደምጠዋል።

    የወቅቱ ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ ነው ወደፊት ብቅ ያሉት።

    ካማላ ፓርቲያቸውን ወክለው ዕጩ ፕሬዝደንት ሆነው ከመጡ ጥቂት ወራት ቢሆናቸውም ከዶናልድ ትራምፕ ጋር መፎካከር ችለዋል።

    አሜሪካዊያን ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ ድምፅ መስጠት ይጀምራሉ።

  14. ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ድምፃቸውን ሰጥተዋል

    የድምፅ መስጫ ኮሮጆ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የአሜሪካ ምርጫ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ይደረጋል። ከኦፊሴላዊው የድምፅ መስጫ ቀን በፊት ባሉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መምረጣቸው ተሰምቷል።

    በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ከዚህ ቀደም አይተውት በማያውቁት ሁኔታ በርካታ ሰዎች ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት እየመረጡ እንደሆ አሳውቀዋል።

    ከሰባቱ ቁልፍ ግዛቶች አንዷ በሆነችው ኖርዝ ካሮላይና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

    አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ዊስኮንሲን፣ ፔንስሊቪኒያ እና ሚሸጋን የምርጫውን ውጤት ሊወስኑ የሚችሉ ቁልፍ ግዛቶች ናቸው።

    ከእነዚህ መካከል በሚሺጋን፣ ዊስኮንሲን እና ፔንሲልቬኒያ ከማክሰኞ በፊት ድምፅ የሚሰጡ ሰዎች ቁጥር ከቀደመው ጊዜ እጅግ ልቋል።

    ታር ሒል ስቴት ተብላ በምትታወቀው ኖርዝ ካሮላይና ከ4.4 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ድምፃቸውን ሰጥተዋል። በዚህች ግዛት በ2020 ምርጫ በተመሳሳይ ወቅት ከምርጫው በፊት ድምፃቸውን የሰጡ ሰዎች ቁጥር 3.6 ሚሊዮን ነበር።

    ምንም እንኳ በርካታ ሰዎች ከማክሰኞ በፊት ድምፃቸውን ቢሰጡም ካለፈው ምርጫ ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ ዝቅ ያለ ነው።

    በአውሮፓውያኑ 2020 በተደረገው የአሜሪካ ምርጫ ከድምፅ መስጫው ቀን አስቀድሞ 101.5 ሚለዮን ሰዎች መርጠው ነበር። ነገር ግን ቁጥሩ እንዲህ ከፍ እንዲል ያደረገው ምርጫው የተካሄደው በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በመሆኑ ሰዎች መጨናነቁን ፈርተው አስቀድመው በመምረጣቸው ነው።

    በ2016 የአሜሪካ ምርጫ 47 ሚሊዮን በ2012 ደግሞ 46 ሚሊዮን ሰዎች ነበሩ ከምርጫው ቀን በፊት ድምፃቸውን የሰጡት።

  15. የአሜሪካ ምርጫ ውጤት ለሩሲያ ምን ይፈይድላታል?

    የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን

    የፎቶው ባለመብት, EPA

    የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከምክትል ፕሬዝደንቷ ካማላ ሀሪስ ይልቅ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ተመልሰው ሥልጣን ቢጨብጡ እንደሚመርጡ ለማወቅ የፖለቲካ ተንታኝ መሆን አይጠይቅም።

    ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የምታደርገውን የጦር መሣሪያ ድጋፍ በግልፅ ይነቅፋሉ። ሩሲያ ዩክሬን ላይ ለምታደርገው ጦርነት ፕሬዝደንት ፑቲንን ተወቃሽ ላለማድረግ ጥንቃቄ ሲያደርጉም ይስተዋላሉ።

    ዪክሬን ይህን ጦርነት እንድታሸንፍ ይሻሉ ወይ ተብለው ተጠይቀው ምላሽ ከመስጠት መቆጠባቸውም ይታወሳል።

    በተቃራኒው ምክትል ፕሬዝደንቷ ካማላ ሀሪስ ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ “የአሜሪካን ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው” ይላሉ። አልፎም ፕሬዝደንት ፑቲን “አምባገነን እና ገዳይ” መሪ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

    የምርጫው ወጤት እጅግ ጠባብ እና ክርክር የሚያስነሳ የሚሆን ከሆነም ይህ ለክሬምሊን መልካም ዜና ነው።

    የምርጫው ውጤት አከራካሪ ሆነ ማለት አሜሪካ ቀጣይ መሪዋን ለመወሰን በምታደርገው ውጣ ውረድ ውስጥ የውጭ ጉዳዮችን ትዘነጋለች ማለት ነው።

  16. ትራምፕ እና ሃሪስ በምርጫው ዋዜማ ምን እየሰሩ ነው?

    ትራምፕ እና ሃሪስ

    የዲሞክራቷ እጩ ካማላ ሃሪስ እና የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ የመጨረሻ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን እያካሄዱ ነው። ምርጫው ሊካሄድ ሰዓታት በቀሩት በዚህ ወቅትም ለማን እንደሚመርጡ ያልወሰኑ ሰዎችን ድምጽ ለማግኘት ተጽእኖ ለመፍጠር እየሞከሩ ነው።

    ካማላ ሃሪስ በምርጫ ወሳኝ በምትባለው ፔንስልቫንያ ግዛት በሚገኙት አሌንታውን፣ ፒትስበርግ እና ፊላደልፊያ ከተሞች የድጋፍ ሰልፎችን ያካሂዳሉ። እሳቸውም ሆነ ተቀናቃኛቸው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በግዛቲቱ ረዘም ላለ ጊዜ አሳልፈው ነበር።

    ትራምፕ በበኩላቸው በምርጫው ዋዜማ በሰሜን ካሮላይና፣ ፔንስልቫንያ እና ሚቺጋን በተሰኙት ወሳኝ ግዛቶች ጉብኝት ያደርጋሉ።

  17. የፕሬዚዳንታዊ እጩዎቹ የምርጫ ዘመቻ በእምነት ላይ የተመሰረተ ነው

    ካማላ ሃሪስ

    የፎቶው ባለመብት, AP

    ቶኒ ብሌይር የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የኮሙዩኒኬሽንዳይሬክተራቸው “አምላክን ጣልቃ አናስገባም” ሲሉ ተናግረው ነበር።

    በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ፖለቲከኞች እምነትን ለፖለቲካ መሳሪያነት ሲጠቀሙበት አይታዩም።

    በተጻራሪው የአሜሪካ ፖለቲከኞች በየትኛውም ቅስቀሳቸውም ሆነ ተግባራቸው አምላካቸውን በተደጋጋሚ በማንሳት እና መጽሐፍ ቅዱስን በመጥቀስ ይታወቃሉ።

    እሁድ ዕለት የዲሞክራት ዕጩ የሆኑት ካማላ ሃሪስ ጥቁሮች በሚያመልኩበት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ነበር። ፖለቲከኛዋ በንግግራቸው መጨረሻ ላይ መጽሃፍ ቅዱስን ሲጠቅሱ ሰባኪመስለው የታዩሲሆን ምዕመኑም በአድናቆት ተነስቶ በጭብጨባ እና በጩኸት ድጋፉን ለግሷቸዋል።

    የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕም ቢሆኑ ሃይማኖተኛ የሆኑ መራጮችን ድምጽ በመሰረታዊነትተረድተውታል።

    ሶስት ጊዜ አግብተው የፈቱት ትራምፕ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ላይ ጽንስ የማስወረድ ጥበቃን የገረሰሱ ዳኞችን በመሾም በበርካታ ክርስቲያኖች ዘንድ ድጋፍን አግኝተዋል። ትራምፕ በምርጫ ላይ መጽሃፍ ቅዱስ ሲሰጡም ታይተዋል።

    “ሁሉም አሜሪካውያን በቤታቸው መጽሃፍ ቅዱስ ያስፈልጋቸዋል፤ እኔ በርካታ መጽሃፍ ቅዱስ አለኝ። ተመራጭ መጽሃፌ ነው። መጽሃፍ ቅዱስ እንዲኖራችሁ ማበረታት እፈልጋለሁ። አሜሪካ እንደገና እንድትጸልይ ማድረግ አለብን” ሲሉ ተደምጠዋል።

  18. ትራምፕ ከሰባቱ ወሳኝ ግዛቶች በስድስቱ ያሸንፋሉ- የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናቸው

    የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ምርጫ ወሳኝ ሚና አላቸው ከሚባሉት ከሰባቱ ግዛቶች በስድስቱ እንደሚያሸንፉ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናቸው አስታወቀ።

    በወሳኝ ግዛቶች እናሸንፋለን በሚል እሳቤም የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን ትራምፕ ላያሸንፉ በሚችሉባቸው ግዛቶች አተኩረው ቆይተዋል።

    ባለፈው ኣምንት አርብ በአውሮፓውያኑ 2016 እና 2020 በሰፊ ልዩነትበተሸነፉበት ቨርጂኒያ ትራምፕ የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል።

    እሁድ ዕለት ደግሞ ዕጩ ምክትል ፕሬዚዳንት ቫንስ በኒው ሃምፕሻየር ማህበረሰብ ጋር ተገናኝተው ነበር። ሆኖምበዚህች ግዛትየዲሞክራት ዕጩዋካማላ ሃሪስበሰፋ ልዩነትእየመሩ እንደሆነ የህዝብ አስተያየቶች በግልጽ እንዳሳዩ አንደኛው የትራምፕ አማካሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

    የቅርብ ጊዜ የኒውዮርክ ታይምስ የሲየና የህዝብ አስተያየት እንደሚያሳየው ምርጫው የማይገመት ውጤት ሊታይበት እንደሚችል ነው።

    ከዚህ ቀደም የሪፐብሊካኑ መሰረት በነበረችው የአይዋ ግዛት ካማላ ሃሪስ የበለጠ ድጋፍ እያገኙ እንደሆነ የህዝብ አስተያየት ጠቁሟል። የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ቡድን ይህንን አስተያየት እንግዳ እና ግራ የሚያጋባ ብሎታል።

  19. የአይዋ ግዛት ለምን የትኩረት ማዕከል ሆነች?

    ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሃሪስ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    ከአራት ዓመታት በፊት በነበረው ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ በአይዋ ግዛት በስምንት ነጥቦች ማሸነፍ ችለው ነበር።

    በዚህ ሳምንት መጨረሻ የተደረገው የህዝብ አስተያየት ግን ትራምፕ በሶስት ነጥብ ዝቅ ያሉበት እንደሆነ ያሳየ ነው።

    ነጥቡ ዝቅ ማለቱ አስተያየት ከመሆኑ አንጻር ትክክለኛውን ገጽታ ላያሳይ ቢችልም በተቃራኒው ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል።

    ለምን? የተወሰኑ ምክንያቶች አሉ።

    • የአይዋ ግዛት ከአውሮፓውያኑ 2012 በኋላየሪፐብሊካን ጠንካራመሰረት ሆናቆይታለች ለዚያምነው አስተያየቱ ሪፐብሊካንን ያስደነገጠው
    • የህዝብ አስተያየቱ የተሰበሰበው በአሜሪካ በተለይም በአይዋ ግዛት ትክክለኛ መረጃዎችን በመሰብሰብ በሚታወቁት አን ሴልዘር ነው።
    • የሕዝብ አስተያየቱ እንደሚያሳየው ሴቶች እና ከፓርቲ ውጭ ያሉ መራጮች ድጋፋቸውን ለሃሪስ ድጋፋቸውን እየሰጡ በመሆናቸው ነው ይሄ የተከሰተው

    አን ሴልዘር ለቢቢሲ እንደተናገሩትከ65 ዓመትበላይ የሆኑእና ከዚያበላይ ሴቶችሃሪስን እየደገፉ በመሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑ ነው።

    “አስተማማኝ መራጭ ስለሆኑ በዕድሜ የገፉ አረጋውያንን ትኩረት ለማግኘት መሞከር አለብህ ካማላ ሃሪስ ይህንን እያደረጉ ይገኛሉ” ብለዋል።

    ከዚህም ጋር ተያይዞ እየተነሳው ያለው ጥያቄ “ ሃሪስ በሴቶች እና ፓርቲ ደጋፊ ባልሆኑ መራጮች ዘንድ በአይዋ ግዛት ድጋፍ ካገኙ በሌሎች ሚድዌስት በተሰኙት ግዛቶች ያንኑ ማሳካት ይችሉ ይሆን?

  20. “የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” ካማላ ሃሪስ

    ካማላ ሃሪስ

    የዲሞክራቷ እጩ ካማላ ሐሪስ “የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አሉ።

    ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26/ 2015 ዓ.ም ከሚደረገው የአሜሪካ ምርጫ በፊት የመጨረሻ ቅስቀሳቸውን እያደረጉ ያሉት ካማላ ሃሪስ በሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ ተገኝተው ነው ይህንን ያሉት።

    የአረብ አሜሪካውያን ከፍተኛው ህዝብ በሚገኝበት ሚቺጋን ግዛት ውስጥ ተገኝተው ነው ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት።

    የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከፍተኛ የአረብ ህዝብ በሚኖርባት የዲርቦርን ከተማ በሳምንቱ መጨረሻ ተገኝተው ቅስቀሳ አድርገዋል።

    ዲሞክራቶች ጦርነቱን የያዙበት መንገድ እንዲሁም እስራኤል በጋዛ ላይ በምታደርገው የተቀናጀ እና የማያባራ ጥቃት የባይደን አስተዳደር የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ላይ አረብ አሜሪካውያንን ያለባቸውን ቁጣ ለዚህ ቅስቀሳ ተጠቅመውበታል።