ስደተኞች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ባይገቡ ኖሮ አሜሪካ ምን ትመስል ነበር?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
እየተካሄደ ባለው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፉክክር በአገሪቱ የሚገኙ ስደተኞች ዋነኛ ጉዳይ የምረጫ ቅስቀሳቸው ዋነኛው ርዕሰ ጉዳይ ነው።
የሪፐብሊካን እና የዴሞክራቲክ ፓርቲዎች ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወደ አሜሪካ በተለይም በሜክሲኮ ድንበር በኩል በሚገቡት ስደተኞቸ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ።
ዶናልድ ትራምፕ ስለ ስደተኞች ጉዳይ አሳሳቢነት ሲያወሱ ክስተቱን ከ“ወረራ” ጋር በማመሳሰል ነው ደጋግመው የሚያስጠነቀቁት። ተመርጠው ወደ ሥልጣን የሚመለሱ ከሆነም ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸውን ስደተኞች በጅምላ ለማባረርም አየዛቱ ነወ።
የዲሞክራቷ ተቀናቃኛቸው ካማላ ሃሪስ በበኩላቸው የቀድሞውን ፕሬዚዳንት በስደተኞች ዙሪያ “ፍርሃት እና መከፋፈል እያቀጣጠሉ ነው” ሲሉ ከሰዋቸዋል።Link














