ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ማክሮን እስራኤል ሕጻናት እና ሴቶችን በቦምብ ከመደብደብ ትቆጠብ አሉ
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እስራኤል በጋዛ ያሉ ሕጻናት እና ሴቶችን በቦምብ ከመደብደብ መቆጠብ አለባት አሉ። ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በሐማስ የሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር በጦርነቱ አስካሁን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 11,078 ከፍ ማለቱን ይፋ ካደረገ በኋላ ነው። በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉት ፍልስጤማውያን መካከል አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕጻናት እና ሴቶች ናቸው።
የቀጥታ ሽፋን
ከ4 ሳምንታት የእስራኤል-ጋዛ ጦርነት በኋላ በግልጽ የሚታዩ 5 እውነታዎች
ዶክተር፣ ልብስ ሰፊ፣ ጨቅላ ሕጻን...- በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደሉት መካከል የጥቂቶቹ አሳዛኝ ታሪክ