የአውሮፓ ኅብረት ለጋዛ የሚያደርውን ድጋፍ በድጋሚ ጨመረ
የአውሮፓ ኅብረት ለጋዛ የሚላከውን ሰብአዊ እርዳታ በ25 ሚሊዮን ዩሮ ለመጨመር ቃል ገባ።
ዘንድሮ የሚደረገው ድጋፍ በድጋሚ እንዲጨምር ነው የተወሰነው።
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኧርሴላ ቮን ደር ሌይን፣ ከሦስት ሳምንታ በፊት እርዳታ በሦስት እጥፍ ለመጨመር መወሰናቸውን ተናግረዋል።
አሁን ድጋፍ እንዲጨመር ከተወሰነ በኋላ ለጋዛ የሚሰጠው አጠቃላይ እርዳታ 100 ሚሊዮን ዮሮ ይሆናል።
ድጋፉ ለሰብአዊ ተቋማት የሚሰጥ ሲሆን፣ በዋናነት ምግብ፣ የመጠጥ ውሃ፣ የጤና እና ሌሎችም መሠረታዊ አገልግሎቶች ላይ በማተኮር ነፍስ አድን እርዳታ እንደሚደረግበት ተገልጿል።
የአውሮፓ ኅብረት የፍልስጥኤም ትልቁ የውጭ እርዳታ ሰጭ ሲሆን፣ ተጨማሪ የሚሰጠው እርዳታ የጋዛ ነዋሪዎችን ስለመድረሱ ግን ግልጽ አይደለም።
በጋዛ እና ግብፅ መካከል ያለው ራፋ ድንበር የእርዳታ መተላለፊያ ቢሆንም እየገባ ያለው እርዳታ በቂ እንዳልሆነ ሰብአዊ ተቋማት ገልጸዋል።