በብራዚል የአሜሪካ አምባሳደር ከፕሬዝዳንት ቦልሳናሮ ጋር ግብዣ ላይ መገኘታቸውን ተከትሎ ኮሮና ሊመረመሩ ነው
በብራዚል የአሜሪካ አምባሳደር፣ በአሜሪካ የነጻነትን ቀንን አስመልክቶ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮን ጋብዘው ነበር።
በዚህም የተነሳ የፕሬዝዳንቱ በኮቪድ-19 መያዝን አስመልክቶ ምርመራ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
ቅዳሜ እለት ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጋር የአሜሪካውን አምባሳደር ቶድ ቻፕማንንን አቅፈው የአሜሪካ የነጻነት በዓልን ሲያከብሩ የተነሱት ምሰል በትዊትር ላይ ታይቷል።
ፕሬዝዳንቱ በቫይረሱ መያዛቸው እንደተሰማ ኤምባሲው በትዊትር ላይ አምባሳደሩ “ምልክት አልታየባቸውም ነገር ግን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ያደርጋሉ” የሚል መልእክት አስፍሯል።
የአሜሪካ ኤምባሲ መልእክት አክሎም ምርመራ እንደሚያደርጉ ገልጾ” የምርመራ አሰራሮችን ይከተላሉ” ብሏል።