በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ250 ሺህ በላይ ናሙናዎች ላይ ምርመራ ተደርጓል
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቻይናዋ ዉሃን ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በመላው ዓለም በቫይረሱ የተያዙ የዓለማችን ሕዝቦች 10 ሚሊየን መሻገሩን የጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ያሳያል። ይህ ወረርሽኝ በብዛት በአሜሪካና አውሮጳ ተስፋፍቶ ቢገኝም በአሁኑ ሰዓት ግን በአሜሪካ ከምን ግዜውም በላይ ስርጭቱ ጨምሯል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ስድስት ቀናት ብቻ አንድ ሚሊየን ገደማ ሲሆን፣ በአፍሪካና በምዕራብ እስያ ይህ ቁጥር መጨመር እያሳየ ነው ተብሏል። በኢትዮጵያም ቢሆን የኮቪድ-19 በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር በአግባቡ መከተል ራስንም ሆነ ሌሎችን ለመከላከል ሁለኛ መላ መሆኑን ባለሙያዎችና መንግሥት ዘወትር ይመክራሉ።
የቀጥታ ሽፋን
አስራ አንድ አባላቱ በኮሮናቫይረስ የተያዙበት ቤተሰብ ጭንቀትና ደስታ
እንደምን አደራችሁ የቢቢሲ አማርኛ ቤተሰቦች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቻይናዋ ዉሃን ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በመላው ዓለም በቫይረሱ የተያዙ የዓለማችን ሕዝቦች 10 ሚሊየን መሻገሩን የጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ያሳያል።
ይህ ወረርሽኝ በብዛት በአሜሪካና አውሮጳ ተስፋፍቶ ቢገኝም በአሁኑ ሰዓት ግን በአሜሪካ ከምን ግዜውም በላይ ስርጭቱ ጨምሯል።
በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2.5 ሚሊየን በላይ የደረሰ ሲሆን በፍሎሪዳና ቴክሳስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ተመዝግቧል፡፡በአገሪቷ ደቡባዊ ክፍል በሚገኙት ግዛቶች የወረርሽኙ ሥርጭት የጨመረው በቅርብ ሳምንታት የንግድ ተቋማት እንዲከፈቱ ከተፈቀደ በኋላ ነው ተብሏል፡፡
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ስድስት ቀናት ብቻ አንድ ሚሊየን ገደማ ሲሆን፣ በአፍሪካና በምዕራብ እስያ ይህ ቁጥር መጨመር እያሳየ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያም ቢሆን የኮቪድ-19 በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክር በአግባቡ መከተል ራስንም ሆነ ሌሎችን ለመከላከል ሁነኛ መላ መሆኑን ባለሙያዎችና መንግሥት ዘወትር ይመክራሉ።
እናንተም የቢቢሲ አማርኛ ቤተሰቦች ራሳችሁም ሆነ ወዳጆቻችሁ በጤና ያለስጋት እንድትኖሩ እጃችሁን በየጊዜው መታጠብ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንዲሁም አካላዊ ርቀትን መጠበቅ አትርሱ።
ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከመላው ዓለም የምንመራርጣቸውን የኮሮናቫይረስ አበይት ዜናዎች እናቀርባለን። ተከታተሉን። መልካም ቀን!

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
