የጤና ጥበቃ
ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው የምርመራ ውጤት መሰረት የቫይረሱ ምርመራከተደረገላቸው 659 ሰዎች መካከል ዘጠኙ በሽታው
እንደተገኘባቸው አመልክቷል።
ይህም እስካሁን ድረስ
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ቫይረስ የተገኘባቸውን ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር ከአንድ መቶ በላይ እንዲሻገር በማድረግ 105
አድርሶታል።
በበሽታው ከተያዙት መካከል አንድ የ13 ዓመት ታዳጊ ያለበት ሲሆን ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
በሽታው የተገኘባቸው ሰዎች እድሜያቸው ከ13 እስከ 73 ውስጥ ያለ ሲሆን ሦስት ሴቶችና 6 ወንዶች ናቸው። በየዕለቱ የሚወጣው የበሽታው ሁኔታ መግለጫ እንዳለው የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 8 ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ አንዱ የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜጋ ነው።
ከዘጠኙ ሰዎች ሦስቱ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው፣ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው። አምስቱ ደግሞ በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን ተገልጿል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው
አንዷ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባች ስትሆን፤ ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከጅቡቲ የመጡ ናቸው። ሌላኛው ግለሰብ የኢኳቶሪያል ጊኒ ተወላጅ ሲሆኑ ከእንግሊዝ መምጣታቸው ተጠቅሷል።
ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን
6890 የኮሮናቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል። በሽታው የተገኘባቸው 84 ሰዎች ደግሞ ህክምና ላይ ሲሆኑ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች አሃዝ በአንድ ጨምሮ 16 ደርሷል። አንድ ግለሰብ በፅኑ ህሙማን ክፍል
ናቸው።
እስካሁን ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጡት መካከል ሦስት ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸው ማለፉን የሚኒስቴሩ መግለጫ ያመለክታል።