የፕሪጎዥን ደጋፊዎች ሐዘን እና የፑቲን ንግግር
ታትሟል
ቫግነር የተባለው የግል ተዋጊ ቡድን መሪ የነበረው የቭጌኒ ፕሪጎዥን በአውሮፕላን አደጋ መሞቱ ከተነገረ በኋላ ጉዳዩ በዓለም ዙሪያ ዋነኛ ርዕስ ሆኗል።
የፕሪጎዢን ደጋፊዎች እና አድናቂዎች በሩሲያ የተለያዩ ከተሞች ውስጥ ሐዘናቸውን በአደባባይ እየገለጹ ነው። አመጽ ቀስቅሶባቸው በእጅጉ አስቆጥቷቸው የነበሩት ፑቲንም ስለ ፕሪጎዢን ሞት ሐሙስ ምሽት ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።









