የኤፍ ቢ አይን ቢሮ ‘ጥሶ’ ለመግባት የሞከረው ግለሰብ በተከፈተበት ተኩስ ተገደለ

የፖሊስ አባላት

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ታትሟል

በአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት አንድ የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ የኤፍቢአይ ጽህፈት ቤትን ‘ጥሶ’ ለመግባት ሲሞክር በተከፈተበት ጥቃት መገደሉን ባለስልጣናት አሳውቀዋለ።

ግለሰቡን በሲንሲናቲ ወደሚገኘው የኤፍ ቢ አይ ቢሮ ለመግባት ሙከራ ካደረገ በኃላ ያመለጠ ሲሆን ሰዓታት ከፈጀ ፍጥጫ በኃላ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ተገድሏል።

የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ሪኪ ሺፈር የተባለው የ42 ዓመት ሰው ከቀኝ ዘመም አክራሪ ቡደኖች ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ዘግበዋል።

የኤፍቢአይ ሃላፊ መስሪያ ቤታቸው ላይ የሚቃጣ ጥቃት እና ስጋት የሚፈጥር ተግባር “ሁሉንም አሜሪካዊ በእጅጉ ሊያሳስብ ይገባል” ብለዋል።

ትላንት ሃሙስ በተፈጠረው ክስተት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ፖሊስ የግለሰቡን ማንነት እና ድርጊቱን የፈጸመበትን ምክንያት ይፋ ከመግለጽ ተቆጥቧል።

የኤፍቢአይቢሮ ላይ የተቃጣው ጥቃት ከመሰማቱ አስቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣናት ባለፈው ሰኞ ፍሎሪዳ የሚገኘው የዶናለድ ትራምፕ ቤት ላይ ፍተሻ ከተደረገ በኃላ የህግ አስከባሪ ተቋማት ላይ ስጋት መጨመሩን አስታውቀው ነበር።

ታዲያ ተጠርጣሪው የኤፍቢአይ የሲንሲናቲን ቢሮ የእንግዶች የፍተሻ ስፍራ ጥሶ ለመግባት ያደረገው ሙከራ ከከሸፈ በኃላ ከአከባቢው ተሰውሯል።

ይሁን እንጂ ይህ ከሆነ ከሃያ ደቂቃ በኃላ ተጠርጣሪው ያለበት ቦታ መለየቱ ተነግሯል።

ግለሰቡ ፖሊሶች ላይ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ይህ ከመሆኑ በፊት ፖሊሰ ሲያሳድደው ነበር። በተኩስ ልውውጡ የተጎዳ ፖሊሰ እንደሌለወም ተገልጿል።