በ12 ቀናት 1000 ኪሎ ሜትር ሮጣ አገር ያቆራረጠች የ52 ዓመት ሴት

ታትሟል

የ52 ዓመቷ ናታሊ ዳው በ12 ቀናት አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በመሮጥ ከታይላንድ ተነስታ ሲናጋፖር ደረሰች።

ናታሊ በአንድ ቀን እስከ 84 ኪሎሜትር (ሁለት ማራቶን ያክላል) ለመሮጥ የቻለችባቸው ቀናትም ነበሩ ተብሏል።

ናታሊ የእጅግ ረዥም ርቀት ሯጭ ስትሆን በውድድር ፈጻሜዋ ላይ ናታሊ የእጅግ ረዥም ርቀት ሯጭ ስትሆን በውድድር ፈጻሜዋ ላይ፤ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ መግባት ምንም ለውጥ አያመጣም። ከዓለማችን ህዝብ 99.95 በመቶ ሊያከናውነው የማይችለውን ነገር ማድረግ ችያለሁ ብላለች።

በሩጫው ወቅት ከነበረው ከባድ ጸሐይ በተጨማሪ በመጀመሪያው ቀን ዳሌዋ ላይ እና በሦስተኛው ቀን ደግሞ ያጋጠማት የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሩጫውን ከባድ አድርጎባት ነበር።

ከዚህ በፊት ሮጣ የምታውቀው 200 ኪሎ ሜትር ብቻ መሆን የገለጸችው ናታሊ፤ ራሴን በተለያየ መንገድ ለመፈተን ሁሌም ዝግጁ ነኝ ስትል ለቢቢሲ ገልጻለች።

በታይላንድ ድንበር ተጀምሮ በማሌዥያ በኩል ወደ ሲንጋፖር እንዲያቀና የታቀደው ሩጫ ፕሮጀክት 1000 የሚል ስያሜም አግኝቷል።

ናታሊ በሮጥችባቸው 12 ቀናት ምሽት ላይ በየዕለቱ ያሳለፈቻቸውን ውጣ ውረዶች ለቢቢሲ በደምጽ መልዕክት ስትልክ ቆይታለች።

በአምስተኛው ቀን ላይ “ከመንገድ ዳር ቁርስ ለመብላት ትንሽ ጊዜ አግኝተናል። እንደገና ከመነሳታችን በፊት ለአምስት ደቂቃዎች አካባቢውን ጎብኝተን ደስ ብሎን ነበር። ዛሬ ጥሩ ቀን ነበር፣ ግን ሁሉም ቀናት ጥሩ ይሆናሉ ብዬ አልጠብቅም። ገና ብዙ ይቀረናል” ስትል መልዕክት ልካ ነበር።

ምሽት ላይ ከሁለት እስከ ሦስት ሰዓታት ብቻ ለመተኛት የተገደደው የናታሊ ቡድን ከሦስተኛው ቀን ሠምሮ ደግሞ ጠንካራውን የጸሐይ ሃሩር ለማምለጥ በለሊት መሮጥም የግድ ሆኖ ነበር።

ለበርካታ ቀናትም “ጠዋት ስነሳ መሮጥ ያቅተኝ ይሆን?” የሚል አስፈሪ ጥያቄ በተደጋጋሚ እንደተሰማትም ተናግራለች።

ወደ መዳረሻ ሲትቃረብ ሰውነቷ “በጣም የመዛል ስሜት” እንደነበረው ገልጻለች።

እጅግ በጣም ረዥም ርቀት ሯጮች “የተለየ ስብዕና ያላቸው ናቸው” ስትል ናታሊ ተናግራለች።

ከግል ስኬት በተጨማሪ ፕሮጀክት 1000 ሴቶችን እንደሚያበረታታ ተስፋ አድርጋ እንደነበርም ናታሊ አስታውቃለች። ብዙ ወጣት ሴቶች በስፖርት ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያበረታታ የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ለሆነው ለጂአርኤልኤስ 37 ሺህ ዶላር ያህል በሩጫው ተሰብስቧል።

"ሰዎች ቢለግሱም ባይለግሱም መልእክት የሚያስተላልፉበት መድረክ ነበር" ስትል ናታሊ ትናገራለች።

ናታሊ ሩጫውን ማጠናቀቅ ያለው ደስታ ህመሙን ሁሉ የሚያስረሳ እንደሆነ ስትጠየቅ “ገድሉ እና ልምዱ... ጥሩ ዋጋ አለው” ብላለች።

እንደገና ትሮጥ እንደሆነ ለቀረበላት ጥያቄም በመገረም ሳቅ ብቻ ምላሽ ሰተጥታለች።