በሙስና ሲከሰሱ የነበሩት ሲሪል ራማፎሳ በኤኤንሲ መሪነታቸው እንዲቀጥሉ ተመረጡ

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ
ታትሟል

በሙስና ክስ ሲብጠለጠሉ የነበሩት እና በፓርቲያቸው መሪነት ላይ ጥያቄ የተነሳባቸው የደብብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲን) መሪነታቸው እንዲቀጥሉ የመተማመኛ ድምጽ አገኙ።

ራማፎሳ ተፎካካሪያቸው የሆኑትን የቀድሞ የጤና ሚኒስትራቸው የነበሩትን ዝዌሊ ምኺዜን ያሸነፉት 2,476 ለ 1,897 በሆነ ድምጽ ነው።

ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የፓርቲው መሪነትን ያሸነፉት ባለፉት ሳምንታት ስማቸው በሙስና ሲነሳ ከሰነበተ በኋላ ነው። ተቀናቃኛቸውም በተመሳሳይ በሙስና የሚከሰሱ ቢሆንም ለመሪነት ቦታው ሲወዳደሩ ቀላል ያማይባል ድጋፍን አግኝተዋል። ሁለቱም ፖለቲከኞች ግን የሚቀርብባቸውን ክስ አይቀበሉትም።

ሲሪል ራማፎሳ በኤኤንሲ የመሪነት መንበር ላይ ለመቀጠል መመረጣቸው ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር ቀዳሚ ቦታ ላይ ያስቀምጣቸዋል።

ነገር ግን ራማፎሳ አሁንም ከቤታቸው ሶፋ ውስጥ በሌቦች ተዘርፏል ስለተባለው 580,000 ዶላር ምንጭ ጋር በተያያዘ በፖሊስ ምርመራ ይደረግባቸዋል እየተባለ ነው።

በአገሪቱ ፓርላማ አፈጉባኤ የተቋቋመው የሕግ ባለሙያዎች ቡድን ራማፎሳ ሕገ መንግሥቱን እና የፀረ ሙስና ሕግን በመጣስ ከሥልጣን የሚያስነሳ ክስ እንዲመሰረትባቸው ሃሳብ አቅርቦ ነበር።

ነገር ግን ኤኤንሲ በፓርላማው ያለውን የበላይነት በመጠቀም የሕግ ባለሙያዎች ያቀረቡትን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ በማድረጉ ነው ለፓርቲው መሪነት የተወዳደሩት።

ፕሬዝዳንት ሲርል እራማፎዛና የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስትር ዛዋሊ ማካሂዚ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎዛ እና የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስትር ዛዋሊ ማካሂዚ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የገዢው ፓርቲ መሪ ሆኖ ለመቀጠል ከዝዌሊ ምኺዜ ብርቱ ፉክክር ነው የገጠማቸው።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ፕሬዝዳንቱ ለገዢው የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፓርቲ መሪነት ጠንካራ ፉክክር የገጠማቸው ከሙስና ጋር በታያያዘ ሥልጣን እንዲልቁ ካስገደዷቸው ከቀድሞው የጤና ሚኒስትራቸው ዝዌሊ ምኺዜ ነው።

የቀድሞ የጤና ሚኒስትር በጆሃንስበግ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት ላይ ከፍተኛ ድጋፍ ለማግኘት ችለው ነበር ተብሏል።

ሁለቱ ዕጩዎች የኤኤንሲ መሪ ለመሆን እንዲችሉ 4 ሺህ 426 ተሳታፊዎች ከታደሙበት የፓርቲው ጉባኤ ድጋፍ ለማግኝት ተፎካክረዋል።

ራማፎሳ በግል የእርሻ ስፍራቸው ላይ ባለ ቤት ውስጥ የተሰረቀ የውጭ አገር ገንዘብ ሶፋ ስር ተገኝቷል መባሉን ለመሸፋፈን ሞክረዋል በሚል ክስ ከፓርቲው ጉባኤ በፊት ከሥልጣን እንዲለቁ ጫና እየተደረገባቸው ነበር።

በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ በኩል የቀረበው ገለልተኛ ሪፖርት ራማፎሳ ሕግ ተላልፈው ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል። ሆኖም ፕሬዝዳንቱ የፈጸምኩት ነገር የለም ብለዋል።

ባለፈው ማክሰኞ የገዢው የኤኤንሲ ፓርቲ የፓርላማ አባላት ራማፎሳን ከሥልጣን ለማስነሳት የሚደረገውን ጥረት ለፕሬዝዳንቱ ድጋፍ በመስጠት እንዲያከሽፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር።

ባለፈው አርብ የተወሰኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች ራማፎሳን ሲቃመው እና ገንዘብ የተሰረቀበትን ፓላፓላ የተባለውን የእርሻ ቦታ ስያሜ በጽሁፍ ይዘው ታይተዋል።

የማካዚህ ደጋፊዎች “ለውጥ” የጠየቁ ሲሆን ራማፎሳ “ተመልሶ አይመጣም” ሲሉ ተደምጠዋል።

የቀድሞ የጤና ሚኒስትር በኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ አንድ የኮሚኒኬሽን ኩባንያ ከቤተሰባቸው ጋር በጥቅም የተሳሰረ ውል ፈጽሟል ከተባለ በኋላ ነበር ከሥልጣን ለመውረድ የተገደዱት።

እሳቸው ግን ይህንን የቀረበባቸውን የሙስና ክስ አይቀበሉትም።