ዎልቭስ ከ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ብራይተን ከ አርሰናል . . . የሱቶን የፕሪሚር ሊግ ግምቶች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ዛሬ ቅዳሜ ስድስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
ቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች የፈረንጆች አዲስ ዓመት ዕለት እሑድ እንዲከናወኑ መርሐ ግብር ተዘጋጅቶላቸዋል።
የ17ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ግምት የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን እንደሚከተለው ቃኝቷቸዋል።

ቅዳሜ
ዎልቭስ ከ ማንችስተር ዩናይትድ
ዎልቭሶች በባለፈው ጨዋታ ኤቨርተንን አሸንፈው በራስ መተማመናቸውን በማሳደጋቸው ይህ ጨዋታ ለዩናይትድ አስቸጋሪ ይሆናል።
ማንችስተር ዩናይትድ ሊፎካከሩ ቢችሉም የኤሪክ ቴን ሃግ ቡድን እየተሻሻለ በመሆኑ እንደሚቋቋመቸው አስባለሁ።
ኖቲንግሃም ፎረስትን ከማሸነፍ ባለፈ ማንችስተር አሰልጣኙ በሚፈልጉት መልኩ እየተጫወተ ነው።
አሁን የሮናልዶ ጉዳይ ርዕስ አይሆንም። ቡድኑ ፍሰት ያለው ጨዋታ እየተጫወተ ነው።
ግምት፡ 1 - 2

በርንማውዝ ከ ክሪስታል ፓላስ
ክሪስታል ፓላስ በፉልሃም ይሸነፋል ብዬ ባለመገመቴ በእነሱ ላይ ያለኝ እምነት እየተሸረሸረ ነው።
ይህ ጨዋታ ለብርንማውዞችም አስፈላጊ ነው።
ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች አምሰቱን በመሸነፋቸው ላለመውረድ የሚፎካከሩበት ጨዋታ ይሆናል።
ይህን ጨዋታ ያሸነፈ ቡድን መነሳሳቱ እንደሚጨምር ባምንም አቻ ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ።
ግምት፡ 1 - 1

ፉልሃም ከ ሳውዝሃምፕተን
ፉልሃምን በተከታታይ ነጥብ ይጥላል እያልኩ ውጤታማ በመሆናቸው ይቅርታ እጠይቃለሁ። ያሉበት ደረጃ ይገባቸዋል።
ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ ብቻ አይደልም ብዙዎችን ያስደነቁት፤ ጠንካራ የተከላካይ መስመር እና የማጥቃት ፍላጎት ያለው ቡድን ገንብተዋል።
ሳውዝሃምፕተን ደግሞ ችግር ውስጥ ያለ ቡድን በመሆኑ ነው ደረጃ ሰነጠረዡ ግርጌ ላይ የተቀመጠው።
አዲሱ አሰልጣኝ ናታን ጆንስ እንዳመኑትም ቡድኑ ብዙ ሊሠራበት ይገባል።
ግምት፡ 2- 0

ማንቸስተር ሲቲ ከ ኤቨርተን
ካለፉት ዘጠኝ ጨዋታቸው አንዱን ያሸነፉት ኤቨርተኖች ወደ ኢትሃድ የሚያደርጉት ጉዞ ከባድ ነው።
የፍራንክ ላምፓርድ ቡድን ጨዋታውን እንዴት ሊወጣው አስቧል? በተቻላቸው መጠን እየተከላከሉ ለመጫወት የሚመርጡ ቢመስልም በፍጥነት ጎል ከገባባቸው ከባድ ይሆንባቸዋል።
ብቸኛው ጥያቄ ጋርዲዮላ ማንን ነው የሚያሰልፉት የሚለው ነው።
ወጣም ወረደም የተጫዋች ምርጫ ውጤቱን የሚቀይረው አይመስለኝም።
ግምት፡ 5 - 0

ኒውካስል ከ ሊድስ
ሊድስ ከማንቸስትር ሲቲ ጋር ካደረገው ከባድ ጨዋታ በኋላ ድንቅ አቋም ላይ ከሚገኘው ኒውካስል ሌላ ፈተና ይጠብቀዋል።
ሊድስ ያለውን በሙሉ የሚሰጥ ቡድን ነው። ኒውካስል ደግሞ ተከላካይ መስሩ ጠንካራ ከመሆን ባለፈ ጎሎችንም ያስቆጥራል።
ግምት፡ 2 - 0

ብራይተን ከ አርሰናል
አርሰናል ይህን ጨዋታ ካሸነፈ ዋንጫውን ለማንሳት እስከመጨረሻው እንደሚጓዝ የሚያመላክት ይሆናል።
ኤዲ ንኬቲያ ባለፈው ጨዋታ ጎል ቢያስቆጥርም ጋብሬል ጄሱስ ባይጎዳ ለዚህ አይነቱ ጨዋታ ነው የሚያስፈልገው።
ዘንድሮ ብራይተኖች በካራባኦ ካፕ አርሰናል ማሰናበት ከመቻላቸውም ባለፈ በሊጉም አሸንፈዋቸዋል።
አርሰናሎች ዕድል ቢኖራቸውም ይህን ጨዋታ ብራይተኖች እንደሚያሸነፉ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 -1

እሑድ
ቶተንሃም ከ አስቶን ቪላ
ከቶተንሃም ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም። በደረጃ ሰንጠረዡ አራተኛ ላይ ቢቀመጡም አቋማቸው ይዋዥቃል።
ለምንድን ነው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ሁሌም ቡድኔ ደክሟል የሚሉት? ሁሌስ ለምን ቀድሞ ጎል ይገባባቸዋል?
ቪላዎች በሊቨረፑል ተበልጠው ቢሸነፉም በጨዋታው ጥሩ ተንቀሳቅሰዋል።
ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስለኛል።
ግምት፡ 2 - 2

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቼልሲ
ቼልሲዎች ከበርንማውዝ በጣም አስፈላጊ ሦስት ነጥብ አሳክተዋል።
ኖቲንግሃሞች ከዩናይትድ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ዓላማቸውም ምን እንደነበረ ሳይታወቅ ተሸንፈው ወጥተዋል።
ቼልሲዎች የጎል አስቆጣሪ ችግር አለባቸው።
ኖቲንግሃሞች በሊጉ ለመቆየት በሜዳቸው ነጥብ መሰብሰብ አለባቸው። ይህን ጨዋታ ግን ቼልሲዎች በጠባብ ውጤት ያሸንፋሉ።
ግምት፡ 1- 2












