ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ሱቶን ዩናይትድ አቻ ይለያያል፣ ቼልሲ ደግሞ ይሸነፋል አለ
የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን በዚህ ሳምንት በሚደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ በሰጠው ግምት ዩናይትድ አቻ ይለያያል፣ ቼልሲ ደግሞ በሜዳው ሽንፈት ያስተናግዳል ብሏል።
ክሪስ ሱቶን የ31ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ግምቶችን እንደሚከተውል ሰጥቷል።
አስተን ቪላ ከ ኒውካስል
ሁለቱም ክለቦች አስናቂ አቋም ላይ ናቸው። ቪላዎች ከዚህ ቀደም ያደረጓቸውን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል።
ኒውካስል ደግሞ ወደ ቪላ ሜዳ የሚያቀኑት ተከታታይ አምስኛተ ጨዋታዎችን ለማሸነፍ ነው።
ጨዋታው በአቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ይችላል ግን ኒውካስል ባለፈው ሳምንት ከብሬንትፎድ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ ባሳዩት አቋም ተደንቂያለሁ።
ስለዚህ ኒውካስል ያሸንፋል የሚል ግምት አለኝ።
ግምት፡ አስተን ቪላ 1 - 2 ኒውካስል
ቼልሲ ከ ብራይተን
ቼልሲ ባለፉት አራት ጨዋታ ጎል አላስቆጠረም። ላምፓርድ ወደ ቼልሲ ከተመለሰ በአራት ተከላካይ ተጫውቶ በወልቭስ ተሸንፏል።
ላምፓርድ በቼልሲ ቤት ድልን በፍጥነት ማምጣት አለበት ግን የለንደኑ ክለብ የራቀውን ድል ከብራይተን የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው።
ማራኪ የሆነ ጨዋታ የሚያደርጉት ብራይትኖች ባለፈው ሳምንት በስፐርስ በስህተት የተነጠቁትን ሦስት ነጥብ ከቼልሲ ያገኙታል።
ግምት፡ ቼልሲ 0 - 1 ብራይተን
ኤቨርተን ከ ፉልሃም
ፉልሃም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሌላ ክለብ ሆኗል። ተከታታይ 4 ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል። ማርኮ ሲልቭ ከኤቨርተኑ ጨዋታ ነጥብ ለማግኘት መጣራቸው አይቀርም።
ለኤቨርተን ይህ ትልቅ ግጥሚያ ነው። ከሊጉ ላለመውረድ ይህን ጨዋታ ማሸነፋቸው ግድ ነው።
ግምት፡ ኤቨርተን 1 - 0 ፉልሃም
ሳውዝሃምፕተን ከ ክርስታል ፓላስ
ይህን ጨዋታ መገመት ከባድ ነው። በመጨረሻ ደረጃ ያሉት ሳውዝሃምፕተኖች የመጨረሻ የሞት ሽረት የሚያደርጉበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል።
ፓላሶች በበኩላቸው በሮይ ሆድሰን ስር ሆነው ከሁለት ጨዋታ ሁለቱንም አሸንፈዋል። ሊድስ ላይ አምስት ጎል አስቆጥረው ማሸነፈችው ግርምት የሚፈጥር ነው። በአንድ ወር ውስጥ አምስት ሳያስቆጥሩ በአንድ ጨዋታ አምስት ግብ አግብተዋል።
ግን ሴንትስ ለማሸነፍ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም ስለዚህ ይህ ጨዋታ ለፓላስ ቀላል አይሆንም።
ግምት፡ ሳውዝሃምፕተን 1 - 1 ክርስታል ፓላስ
ቶተነሃም ከ ቦርንመዝ
ዓመቱን በሙሉ ለቦርንመዝ የነሰ ግምት ነበረኝ። በሚያስመዘግቡት ውጤት እንዳስደነቁኝ ነው።
ባለፈው ሳምንት ሌስተርን 1 ለ 0 ማሸነፍ ይገባቸው ነበር። ወደ ቶተነሃም ሄደው ግን ያሸንፋሉ የሚል እምነት የለኝም።
ቶተነሃም ባለፈው ሳምንት በብራይተን ይሸነፋሉ ብዬ ገምቼ ነበር። መሸነፍም ነበረባቸው ግን ዕድለኛ ሆነው ከዚያ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ማግኘት ችለዋል።
ቦርንመዞች ከዚህ ጨዋታ የሆነ ነጥብ ሊያገኙ እንደሚችሉ አስባለሁ፣ ነገር ግን ሶን እና ኬንን ሳስብ ቶተነሃም የሚያሸንፍ ይመስለኛል።
ግምት፡ ቶተነሃም 2 - 0 ቦርንመዝ
ዎልቭስ ከ ብሬንትፎርድ
ብሬንትፎድ ድል ካደረጉ አራት ጨዋታዎች አለፈዋል። በአውሮፓ መድረክ የመጫወት ዕድል ያላቸው ብሬንትፎድ እንደ አጀማመራቸው አጨራረሳቸውን ማሳመር እንደሚፈልጉ ጥርጥር የለኝም።
የውድድር ዓመቱ ቀላል ያልሆነላቸው ዎልቭስ ቼልሲን መርታታቸው ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥርላቸዋል። በዚህ ጨዋታም መሸነፍን ያስቀራሉ ብዬ እገምታለሁ።
ግምት፡ ዎልቭስ 1 - 1 ብሬንትፎርድ
ማንቸስተር ሲቲ ከ ሌስተር ሲቲ
የማዝነው ለዲን ስሚዝ ነው። ሌስተርን የተረከበው ጥሩ ጊዜ ላይ አይደለም። ሲቲን በኢትሃድ ጨርሶ ማሸነፍ የማይቻልበት ኃላፊነት ተጥሎበታል።
ሲቲ ቀሪ ጨዋታዎቹን በሙሉ ማሸነፍ የሚችል ከሆነ ሻምፒዮን መሆን እንደሚችል ያረጋግጣል። ስለዚህ ለሲቲ ይህ ጨዋታ የዋንጫ ነው። በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ሌስተር ላለመውረድ የሚያደርገው የሞት ሽረት ነው።
ግምት፡ ማንቸስተር ሲቲ 3 - 0 ሌስተር ሲቲ
እሁድ
ዌስት ሃም ከ አርሰናል
አርሰናል በአንፊልድ በኋላ ወደ ድል የሚመለሱበት ጨዋታ ይሆናል። 2 ለ 0 ሲመራ ለቆየ ቡድን አቻ መለያየት እንደ ሽንፈት ቢታይም፣ መድፈኞቹ ከሊቨርፑል ያገኙት አንድ ነጥብ ውድ እንደሆነች መታየት አለበት።
ከዌስት ሃም ወሳኝ ሦስት ነጥቦችን በመወሰድ ከሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት አስጠብቀው ይቀጥላሉ ብዬ አምናለሁ።
ዌስት ሃም ባለፈው ሳምንት ፉልሃምን ቢያሸንፍም በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ሌላ ሽንፈት ያስተናግዳል ብዬ አስባለሁ።
ግምት፡ ዌስት ሃም 0 - 2 አርሰናል
ኖቲንግሃም ፎረስ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ
ይህ ጨዋታ ለፎረስት ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ፎረስት ዘጠኝ ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ አልቻሉም።
የካሰሚሮ ከቅጣት መመለስ ለኤሪክ ቴን ሃግ ቡድን ብርታት የሚፈጥር ቢሆንም፣ በዚህ ጨዋታ ዩናይትድ የሚያሸንፍ አይመስለኝም።
በሜዳቸው ጥሩ የሆኑት ፎረስቶች ከዩናይትድ አቻ ይለያያሉ ብዬ ገምታለሁ።
ግምት፡ ፎረስ 1 - 1 ዩናይትድ
ሰኞ
ሊድስ ከ ሊቨርፑል
ከሊቨርፑል ምን አይነት አጨዋወት መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም።
ከአርሰናል ጋር የተጫወተው ሊቨርፑል ሌላ ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ ደካማ የነበረው ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ ጥሩ ተጫውቶ ነጥብ ተጋርቷል።
ይህን ሊቨርፑል ግን ከሊድስ በሚኖረው ጨዋታ የምንመለከተው አይመስለኝም።
ግምት፡ ሊድስ 1 - 1 ሊቨርፑል