የዝውውር ጭምጭምታዎች፡ ማጓየር ወደ ዌስት ሃም? ዲ ዮንግ ወደ ማንቸስተር ሲቲ?

ታትሟል

ዌስት ሃም እንግሊዛዊውን የመሐል ተከላካይ ከማንቸስተር ዩናይትድ በውሰት ማስመጣት ይፈልጋሉ።

የ30 ዓመቱ ሃሪ ማጓየር በዩናይትድ ቤት ያለው ተቀባይነት መቀዝቀዙን ተከትሎ ዝውውሩ ሊሳካ ይችላል ይላል የቴሌግራፍ ዘገባ።

ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ያቀናል ተብሎ ብዙ ሲባልለት የነበረው ኔዘርላንዳዊው ተጫዋች ወደ ሲቲ ሊያቀና ይችላል።

እንደ ሚረር ዘገባ ከሆነ ባርሴሎና የ28 ዓመቱን በርናንዶ ሲልቫ ይፈልጋሉ። ለዚህ ደግሞ የ26 ዓመቱ ፍራንኪ ዲ ዮንግን ለሲቲ አሳልፈው ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።

የባየርን ሙኒክ አለቃ ኡሊ ሆነስ እንግሊዛዊው አጥቂ በያዝነው የክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ጀመርን እንደሚመጣ ያምናሉ ሲሉ የጀርመኑ ኪከር ጋዜጣ አስነብቧል።

የ29 ዓመቱ የቶተንሃም ሆትስፐር የፊት መስመር ተጫዋች ሃሪ ኬን ወደ ሙኒክ ሊያቀና ይችላል የሚለው ዜና በተደጋጋሚ ተሰምቷል።

የኬን መጨረሻ ያላስተማመነው ቶተንሃም ተተኪ አጥቂ ለማስፈረም ደፋ ቀና እያለ ነው።

በቶተንሃም ዓይን ውስጥ ከገቡ አጥቂዎች መካከል የ22 ዓመቱ ሰርቢያዊ የጁቬንቱስ አጥቂ ዱሳን ቭላሆቪች ይጠቀሳል።

የማንቸስተር ዩናይትድ ባለቤት የሆነው የግሌዘር ቤተሰብ የአትላንታውን ዴንማርካዊ አጥቂ ለማስፈረም ይገደዳል ሲል ኤክስፐርስ ኦንላይን ዘግቧል።

ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ዩናይትድ ዘጠኝ ቁጥር አጥቂ ካላስፈረመ የገበያ ዋጋው ሊወርድ ይችላል መባሉ ነው።

የጣሊያኑ ኮሪየሬ ዴሎ ስፖርት እንደዘገበው ኒውካስል ዩናይትድ የናፖሊውን አጥቂ ለማስፈረም 82 ሚሊዮን ፓውንድ አቅርቧል።

ጆርጂያዊው የ22 ዓመት የክንፍ መስመር ተጫዋች ክቪቻ ክቫርትስኬሊያ በተናቀቀው የውድድር ዘመን ድንቅ ብቃቱን ካሳዩ ተጫዋቾች መካከል ነው።

የሊቨርፑሉ አምበል ጆርዳን ሄንደርሰን ከሳዑዲው ክለብ አል-ኤቲፋቅ ጋር ስምምነት ቢደርስም ሁለቱ ክለቦች ግን ገና ከስምምነት እንዳልደረሱ ፋብሪዚዮ ሮማኖ ገልጧል።

የቼልሲው ጋቦናዊ አጥቂ በያዝነው ክረምት ወደ ማርሴ ያቀናል ሲል የፈረንሳዩ ጎል ፅፏል።

የ34 ዓመቱ የቀድሞ የአርሰናል አጥቂ ኦባሚያንግ ዝውውሩ እንዲሳካ ደመወዙን ለመቀነስ እንደተስማማ ተሰምቷል።

የሳዑዲው አረቢያው አል-ሂላል የ32 ዓመቱን የማንቸስተር ሲቲ የክንፍ ተጫዋች ሪያድ ማሃሬዝ ለማስፈረም እንደሚሻ ፋብሪዚዮ ሮማኖ አሳውቋል።

ሌላው በሳዑዲ ክለቦች የሚፈለገው ቤልጂየማዊው ሮሜሉ ሉካኩ ነው። የቼልሲው አጥቂ በውሰት ባቀናበት ኢንተር ይቆያል ቢባልም ይህ የሚሳካ አይመስልም።

ኢንተር ሚላን በሉካኩ ፈንታ የአርሰናሉን ወጣት የ22 ዓመት አጥቂ ፍሎሪያን ባሎገን ማስፈረም እንደሚሻ ስካይ ስፖርትስ ዘግቧል።