ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በፍርስራሽ መካከል ለሁለት ቀናት የቆየውን ታዳጊ ለማትረፍ የተደረገው ጥረት
ታትሟል
ይህ ታዳጊ ሙሐመድ ይባላል፤ እጅግ ከባድ ነው በተባለው ርዕደ መሬት ምክንያት ፍርስራሽ ስር ተቀብሮ ለሁለት ቀናት ያህል ቆይቷል።
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሙሐመድን ከፍርስራሽ ስር ለማውጣት ጥረት በሚያደርጉበት ጊዜ፣ በጠርሙስ ክዳን ውሃ ሲጣጠጡት የሚታይበት ምስል የበርካቶችን ልብ ነክቷል።
ዕድለኛው ሙሐመድ በነፍስ አድን ሠራተኞች ጥረት ከፍርስራሽ ውስጥ በሕይወት ለመትረፍ ችሏል።
ቱርክ እና ሶሪያ የሚዋሰኑባቸውን የድንበር አካባቢዎችን የመታው ተከታታይ ከባድ ርዕደ መሬት ከ11 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ሌሎች በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አደጋው ከደረሰ አራተኛ ቀኑ ቢሆንም የነፍስ አድን ሠራተኞች ከፍርስራሾች ውስጥ በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ነው።