ሩሲያ ከጦርነቱ ወዲህ ከኃይል ሽያጭ 97 ቢሊዮን ዶላር አጋበሰች

ሩሲያ ከጦርነቱ ወዲህ ከኃይል ሽያጭ 97 ቢሊዮን ዶላር አጋበሰች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

ሩሲያ ከዩክሬን ወረራ በኋላ ከነዳጅና ጋዝ የውጭ ገበያ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ አጋበሰች።

ካለፈው መጋቢት ጀምሮ ሃገራት ሩሲያ ያላቸውን ቁጣ መግለፅ ጀምረዋል።

በዚህ ምክንያት የሞስኮው ገቢ እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም መጠኑ ከፍተኛ ነው ተብሏል።

ይህንን የሚለው የኃይል ምርትና ንፁሕ አየር ላይ ምርምር የሚያደርግ አንድ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ እንደሚለው ሃገራት ከሩሲያ የሚያስገቡት ዕቃ ለመመጠን መሞከራቸው አደጋ አለው።

የአውሮፓ ሕብረት፣ ዩናይትድ ስቴትስና ዩናይት ኪንግደም ከሩሲያ ምንም አንገዛም ካሉ መካከል ናቸው።

ምንም እንኳ እኒህ ኃያል የሚባሉ ሃገራት ከሩሲያ ያላቸውን በዩክሬን ወረራ ተቆጥተው ከሩሲያ ቢቆራረጡም የሞስኮው መንግሥት ከየካቲት እስከ ሰኔ ባለፈው ጊዜ 97 ቢሊዮን ዶላር አጋብሳለች።

ከዚህ መካከል 61 በመቶውን አሊያም በገንዘብ ሲሰላ 59 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለሩሲያ ያስገኘው የአውሮፓ ሕብረት ነው።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ሩሲያ በየቀኑ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያክል ታስገባ የነበረ ቢሆንም ይህ መጠን ከመጋቢት ወዲህ ቀንሷል።

ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ተቋም ሩሲያ ገቢዋ ብቻ ሳይሆን ወጪዋም ጨምሯል ይላል።

ተቋሙ እንደሚገምተው ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት 876 ሚሊዮን ዶላር በየቀኑ እያወጣች ነው።

የአውሮፓ ሕብረት ከሩሲያ የሚመጣውን ነዳጅ በ2022 መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማቋረጥ ወስኗል።

ይህ የሩሲያን ገቢ በሁለት ሶስተኛ ሊቀንሰው ይችላል።

ባለፈው መጋቢት ሕብረቱ ከነዳጅ አልፎ ከሩሲያ የሚመጣ ጋዝን መጠን በሁለት ሶስተኛ ለመቀነስ መወሰኑ አይዘነጋም።

ነገር ግን ሕብረቱ እስካሁን ሩሲያ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ከሩሲያ የሚገባ ነዳጅ፣ ጋዝና የድንጋይ ከሰል ሙሉ በመሉ እንዳይገባ ብላለች።

ዩኬ ደግሞ በያዝኩት ዓመት መጨረሻ ከሩሲያ ምንም ነገር ላላስገባ ቃል እገባለሁ ብላለች።

የተቋሙ ጥናት እንደሚለው የአውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ላይ የሚጥለው ዕገዳ ትልቅ አንደምታ አለው።

ድርጅቱ እንደሚለው ሩሲያ ድፍድፍ ነዳጇን በገፍ ለሕንድ እየሸጠች ነው።

ሕንድ ከሩሲያ የምትገዛው ድፍድፍ ነዳጅ መጠን ከጦርነቱ ወዲህ በ17 በመቶ አድጓል።

ጥናቱን የሠራው ተቋም እንደሚለው ሕንድ ይህን ድፍድፍ ነዳጅ እያጣራእ ለአውሮፓ ሃገራትና አሜሪካ እየሸጠች ነው።

ከሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ የሚያመላልሱ ታንከሮች ማዕቀብ ካልተጣለባቸው የሩሲያን ምርት ማገዱ ዋጋ የለውም ይላል ተቋሙ።

ነገር ግን አብዛኛዎቹ ከሩሲያ ምርት የሚያመላልሱ ታንከሮች የአሜሪካና የአውሮፓ ኩባንያዎች ናቸው።

ከሕንድ በተጨማሪ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስና ሳዑዲ አራቢያ የሩሲያ ነዳጅ በገፍ እየገዙ ከሚገኙ ሃገራት መካከል ናቸው።