ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ፖሊተከኛው ሊይዙት በመጡ ፖሊሶች ላይ ቦምብ ወረወረ
አሁን በእስር ላይ የሚገኘው ብራዚላዊ ፖለቲከኛ ሪዮ ዲጂኔሮ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በቁጥጥር ስር ሊያውሉት በሄዱ የፖሊስ መኮንኖች ላይ የእጅ ቦምብ መወርወሩ ተሰምቷል።
የቀኝ አክራሪው ፕሬዝዳንት ጄር ቦልሶናሮ አጋር የሆነው እና ሮቤርቶ ጄፈርሰን የተባው ፖለቲከኛ እጅ ከመስጡ በፊት በወረወረው ቦምብ ሀሉት የፓሊስ መኮንኖችን አቁስሏል።
የ69 ዓመቱ ፖለቲከኛ ጄፈርሰን የእጅ ቦምብ ከመወርወር በተጨማሪ በጠመንጃ በተደጋጋሚ ተኩስ ከፍተው የፖሊስ መኪና የፊት መስታወት ሰባብረዋል።
ፖለቲከኛው ቀድም ብሎ የአገሪቱ ዋና ዳኛ ካርመን ሉሲያ በመዝለፉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የእስር ትዕዛዝ አስተላልፎበት ነበር።
ፕሬዝደናት ቦልሴናሮ ፖሊስ ላይ የሚተኩሱ መታሰር አለባቸው ሲሉ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
በቦምብ ጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ የፖሊስ መኮንኖች ሕክምና ድጋፍ ከተደረገላቸው በኋላ ከሆስፒታል ወጥተዋል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አሌክስአንድር ዲ ሞሬስ የቁም እስር ተፈርዶበት የነበረው ፖለቲከኛ የተጣለበት እግድ በመተላለፉ በእስር ቤት እንዲቆይ አዘዋል።
በመጪው እሁድ የሚካሄደውን የቀኝ ዘመሙ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ እና የግራ ዘመም ፖለቲከኛ ሉዚ ሚንክሎ የሚያደርጉትን የድጋሚ ምርጫ ተከትሎ በብራዚል ውጥረት ነግሷል።
በዚህ ወር መግቢያ በተደረገው ምርጫ ከፍተኛ ድምጽ ቢያገኙም አሸናፊ የሚያደርጋቸውን ደምጽ ያላገኙት የግራ ዘመሙ ፖለቲካኛ በድጋሚ ምርጫውም የማሸነፍ ተስፋ አላቸው ተብሏል።