ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የጥምቀት በዓል አከባበር በተለያዩ አካባቢዎች
ታትሟል
በየዓመቱ ጥር 11 የሚከበረው የጥምቀት በዓል በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው።
ከጥምቀት በዓል ዕለት ቀደም ብሎ ባለው ቀን በሚከበረው የከተራ በዓል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት በመውጣት የጥምቀት በዓል ወደሚከበርባቸው ቦታ በሕዝብ ታጅበው ይጓዛሉ።
በዚህም መሠረት ጥር 10 ቀን ከፍተኛ ሕዝብ በሚታደምባቸው በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ እና በጎንደር በርካታ ሕዝብ ታድሞባቸዋል።
በዛሬ ዕለት ሐሙስ ጥር 11/2015 ዓ.ም. እየተከበረ ባለው የጥምቀት በዓልም ላይ ሕዝብ ታቦታት ባረፉበት ስፍራ ላይ ተሰብስቦ የጥምቀት በዓል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
ከተወሰኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የከተራ እና የጥምቀት በዓል አከባበርን የሚያሳዩ ፎቶ ግራፎችን አሰባስበናል።