ፕሬዝዳንት ፑቲን በጠቀለሏቸው የዩክሬን ግዛቶች አዲስ የጸጥታ ሕግ አጸደቁ

ፕሬዘዳንት ቭላድሚር  ፑቲን

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ታትሟል

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ በቁጥጥሯ ስር ባደረገቻቸው አራት የዩክሬን ግዛቶችን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ ወታደራዊ ሕግ አጸደቁ።  

በክሬምሊን አዋጅ ሩሲያ ወደ ግዛቱ ጨምሬአቸዋለሁ በምትላቸው ሉሃንስክ፣ ዶኔትስክ፣ ዛፖሪዝዝሂያ እና ኬርሰን ክልሎች ነው አዲሱ ሕግ የወጣው።

ከሕጉ መውጣት ባሻገር ግን ከዩክሬን ጋር የሚያዋስኑ የሩሲያ ክልሎች በከፍተኛ ሁኔታ ድብደባ እየደረሰባቸው ይገኛሉ።

አዲሱ ወታደራዊ ሕግ እስካሁን ድረስ ምን ልዩነት እንደሚያመጣ ግልጽ ባይሆንም የዩክሬን ወታደሮችን ግን መሳሪያቸውን እንዲያስቀምጡ ጫና ያደርጋል ተብሎ ግን አይታመንም። ኪየቭ ይገባኛል የሚለውን ግዛት በሙሉ ከዩክሬን ለማስመለስ ቁርጠኛ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን ሶስት የተለያዩ የደህንነት ደረጃዎችን በማዘጋጀት በመላው ሩሲያ ያለውን ጥበቃ እያጠናከሩ ነው።

ሩሲያን ከዩክሬን የሚያዋስኑ ከተሞች በሆኑት ቤልጎሮድ፣ ብራያንስክ፣ ክራስኖዶር እና ሮስቶቭ ክልሎች እንዲሁም በሩሲያ ቁጥጥር ስር በዋለችው የዩክሬን ግዛት ክራሚያ ውስጥ ‘’መካከለኛ ደረጃ የጸጥታ ምላሽ’’ በሚል አዋጁ ታውጇል።

የጸጥታ እርምጃው የጸጥታ ብሎም በሕዝብ እንቅስቃሴዎች ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ አዋጁ በትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ እና ከእነዚህ ክልሎች መግቢያ እና መውጪያ ላይ ገደቦችን አስቀምጧል።

እንዲሁም ሁለተኛው ደረጃ "ከፍ ያለ ዝግጁነት" በሚል የተመደቡት አካባቢዎች ሲሆን ሞስኮን ጨምሮ በሩሲያ መካከለኛ እና ደቡባዊ ክልሎች አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ።

ፕሬዚዳንቱ በእነዚህ አካባቢዎች እንዲተገበሩ ያወጡት ይህ ድንጋጌ "ተሽከርካሪዎችን መፈተሽ ብሎም የትራፊክ ገደቦች" ብሎም "ጥብቅ ሕዝባዊ ጥበቃን" ያጠቃልላል።

የሞስኮ ከንቲባ የሆኑት ሰርጌይ ሶቢያኒን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የነዋሪዎችን “መደበኛ ሕይወት የሚገድቡ እርምጃዎች አይኖሩም” ሲሉ ተናግረዋል።

አነስተኛ የጸጥታ ዝግጁነት የሚያስፈልገው ተብሎ የታወጀው በቀሪው የሩሲያ ክፍል ሲሆን በተለይም በሰሜናዊ ሩሲያ፣ በሳይቤሪያ እና በሩሲያ ሩቅ ምስራቅ አካባቢዎች የሚተገበር ይሆናል።

የፕሬዚዳንት ፑቲንን ድንጋጌ ለማስፈጸም እንዲያስችል ሁሉም የክልል አስተዳዳሪዎች "የኦፕሬሽን ዋና መሥሪያ ቤት" እንዲያቋቁሙ ታዘዋል።

ይህም የኦፕሬሽን መመሪያ የየክልሉ አስተዳዳሪዎችን፣ የወታደሮች እና የፖሊስ ተወካዮችን ያጠቃለሉ ይሆናሉ።

የየክልሉ አስተዳዳሪዎችም "የሩሲያ ፌዴሬሽን የጦር ኃይሎችን እና ሌሎች ወታደሮችን ፍላጎቶች ሁሉ እንዲያሟሉ" ታዝዘዋል። ይህ ለሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ከፍተኛ ኃይል የሚጨምር የሆናል ተብሎ ይጠበቃል።