እውቁ አሜሪካዊ ራፐር ኩሊዮ በ59 ዓመቱ ህይወቱ አለፈ

አሜሪካዊው ራፐር ኩሊዮ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

በይበልጥ ‘ጋንጋስታስ ፓራዳይዝ’ በሚለው ሙዚቃው የሚታወቀው የ90ዎቹ ዝነኛ አሜሪካዊው ራፐር ኩሊዮ በ59 ዓመቱ ህይወቱ አልፏል።

የራፐሩ የረጅም ገዜ ስራ አስኪያጅ ጃሬዝ ፖሲ ኩሊዩ ሎስአንጀለስ በሚገኘው የወዳጁ መኖሪያ ቤት መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መሬት ላይ ሞቶ መገኘቱን ለአሜሪካ መገናኛ ብዘሃን ተናግሯል።

ኩሊዮ ሙዚቃ መስራት የጀመረው እንደ አውሮፓውያኑ በ198ዎቹ ቢሆንም ስሙ የገነነው እና በሂፓሆፕ ታሪክ ስሙን የተከለው በ1995 ባወጣው ‘ጋንጋስታስ ፓራዳይዝ’ በተሰኘው ስራው ነው።

ትላንት ረቡዕ ሞቶ የተገኘው ሙዚቃኛው የህልፈቱ ትክክለኛ ምክንያት እስካሁን ይፋ አልሆነም።ሆኖም ስራ አስኪያጁ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጸው የህልፈቱ መንስኤልየልብ ህመም ሊሆን እንደሚችል አስረድቷል።

የመዝገብ ስሙ ሊዎን አይቪ የሆነው እና በመደረክ ስሙ ኩሊዮ የፊልም ማጀቢያ የነበረው ‘ጋንጋስታስ ፓራዳይዝ’ የተሰኘው ሙዚቃ የግራሚ ሽልማትን አግኝቷል።

ሙዚቃው ከወጣ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ቢቆጠርም አሁንም ተደማጭነቱ የቀጠለ ሲሆን በራሱ ድረ ገጽ የወጣ መረጃ ‘ጋንጋስታስ ፓራዳይዝ’ ስፖቲፋይ በተባለው የበይነ መረብ ሙዚቃ ማጫወቻ ከ1 ቢሊዮን ጊዜ በላይ ተደምጧል።

ከአራት አስርት ዓመታት በሙያው የቆየው ኩሊዮ 8 አልበሞች አሉት። በስራውም የአሜሪካን የሙዚቃ ሽልማት ያገኘ ሲሆን ሶስት የሙዚቃ ቪዲዮቹ ደግሞ የኤም ቲቪን ሽልማት አስገኝተውለታል።

ኩሊዩ ‘ጋንጋስታስ ፓራዳይዝ’ በተጨማሪም ሌሎች ተወዳጅ ስራዎቹም ይታወቃል።

ራፐሩ ከህልፈቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ከሌሎች 90ዎቹ ሙዚቀኞች ጋር ወደ ቴክሳስ ተጉዞ የነበረ ሲሆን የሙዚቃ ስራዎቹንም አቅርቧል።