ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በኬፕ ቨርዴ ተረታች

ኬፕ ቨርድ ከኢትዮጵያ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

ብርኪና ፋሶ እና አዘጋጇ ካሜሩን ከዳረጉት የመክፈቻ ጨዋታ በኋላ በኦሌምቤ ስታዲየም በተደረገው ሁለተኛ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

አሰልጣኝ ቡቢስታ ጭምሮ የኬፕ ቨርዴ ዘጠኝ ተጫዋቾች በኮቪድ ምክንያት በስታዲየሙ ያልተገኙ ሲሆን ብሉ ሻርኮች ከዋልያዎቹ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 6 ተጨዋቾችን ብቻ በተጠባባዊ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ተገደው ነበር።

ይሁን እንጂ የኬፕ ቨርዴ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹን በመርታት 3 ነጥብ ይዘው ወጥተዋል።

በጨዋታው ጅማሬ ላይ የዋልያዎቹ ያሬድ ባዬህ በተጋጣሚው ጁሊዮ ታቫሬስ ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ያሬድ መጀመሪያ ላይ በአንጎላዊው ዳኛ ሄልደር ማርቲንስ ዴ ካርቫልሆ ቢጫ ተስጥቶት የነበረው ቢሆንም በረዳት ዳኛው ጥያቄ የማሃል ዳኛው ክስተቱን በቪ ኤ አር ከተመከቱ በኋላ ተጨዋቹ በቀይ ወጥቷል።

ተቀይሮ የገባው ምኞት ደበበ በራሱ ላይ ጎል ለማስቆጠር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የዋልያዎቹ ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ ግብ ከመሆን ታድጎታል።

በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በተጀመረው የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ካሜሮን ቡርኪና ፋሶን 2-1 አሸንፋለች።

በያውንዴ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል አስቆጥረው መምራት ችለው ነበር።

ሆኖም የአስተናጋጇ ካሜሮን አምበል አቡባካር ቡድኑ ያገኘውን የቅጣት ምቶች ዕድል ወደ ጎል በመቀየር ከእረፍት በፊት የውጤትን ብልጫ ወደ አስተናጋጆቹ ዞሯል።

ምድብ ሀ በድል የጀመሩት የማይበገሩት አናብስት ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት ወሳኝ ሙከራዎችን ግብ እንዳይሆኑ አክሽፏል።

ዛሬ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አራት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን የባለፈው የውድድር ዘመን ሁለተኛ የነበረችው ሴኔጋል እና የአራት ጊዜ ሻምፒዮኗ ምሽት ላይ ይጫወታሉ።