ሩዋንዳ ለጤና ባለሙያዎች የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጠት ጀመረች

ታትሟል

ሩዋንዳ ለጤና ባለሙያዎች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት መስጠት መጀመሯን የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

አንድ የሚኒስቴሩ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በፋይዘር የተመረተው የኮሮናቫይረስ ክትባት በዋና ከተማዋ ኪጋሊ ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ ሆስፒታሎች ይሰጣል።

ክትባቶቹ በተወሰነ መጠን በዓለም አቀፍ እርዳታ እንደተገኙ ሚንስትሩ አስታውቋል።

ክትባት መስጠት ከጀመሩ የአፍሪካ አገሮች መካከላ ግብጽ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሞሪሽየስ እና ሲሸልስ ይገኙበታል።

የሩዋንዳ የጤና ሚንስትር እንዳለው በርካታ ቁጥር ያለው ጠብታ በዚህ ወር ይሰጣል። ይህም በአፍሪካ ሕብረት በኩል በኮቫክስ ጥምረት የሚገኝ ክትባት ነው።

ሩዋንዳ ውስጥ እስካሁን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 17,000 ሌሎች 239 ሞተዋል። አገሪቷ 200,000 ጠብታ አግኝታለች።

በኤር ዚምባብዌ ወደ አገሪቱ የገባው ክትባት በቻይና አምባሳደር አማካይነት ለመንግሥት ተሰጥቷል።

200,000 ጠብታውን የሰጠችው ቻይና ስትሆን ተጨማሪ 600,000 ጠብታ በቀጣዩ ወር ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዘዳንት ኤመርሰን ምናንጋዎ እንዳሉት እገዳ ላይ የተጣለው እገዳ የሚነሳ ይሆናል።

የጤና ሚንስትር እንዳለው እስካሁን ሦስት የካቢኔ አባሎች በቫይረሱ ሳቢያ ሞተዋል።

የዚምባብዌ ጎረቤት በሆነችው ደቡብ አፍሪካ አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው። ክትባቱ አዲሱ ዝርያ ላይ እምብዛም ውጤታማ እንዳልሆነ ጥናት ካሳየ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ክትባቱን አልወስድም ብላለች።