ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የመጀመሪያዋ ናይጄሪያዊት ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪ ህይወቷ አለፈ
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 1 ደቂቃ
በናይጄሪያ የመጀመሪያዋ ሴት ተዋጊ ሄሊኮፕተር አብራሪ መሞቷ ተነግሯል። የናይጄሪያ አየር ኃይል እንዳሳወቀው ፓይለቷ በደረሰባት የመኪና አደጋ ነው ህይወቷ ያለፈው።
ቶሉሎፔ አሮቲሌ ህይወቷ ያለፈው በትናንትናው ዕለት ሲሆን፤ አደጋውም የደረሰባት ካዱና በተባለ ግዛት በሚገኘው የጦር ሰፈር መሆኑም ተገልጿል። አደጋው መቼ እንደደረሰባት ግን የተባለ ነገር የለም።
ቶሎሎፔ የአየር ኃይሉን የተቀላቀለችውም ከሶስት አመት በፊት መሆኑም ተነግሯል።
"ቶሎሎፔ በአየር ኃይሉ አጭር ጊዜ ቆይታዋ በርካታ አስተዋፅኦ አበርክታለች። በተለይም በሰሜናዊ ግዛት የታጠቁ ሽፍታዎችን ለመከላከል እንዲሁም በኒጀር ግዛትም የነበሩ ወንጀሎችን ለመግታት በተካሄደው ዘመቻ አይኪ ከፍተኛ ሚናን የተጫወተች የጦር ሄሊኮፕተር አብራሪ ነበረች" በማለት የናይጄሪያ አየር ኃይል በትዊተር ገፁ አስፍሯል።