የኦማር አልበሽርን ባለቤት ፖሊስ እየመረመራቸው ነው

የፎቶው ባለመብት, AFP
ታትሟል
የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ባለቤት ወ/ሮ ዊዳድ ባቢከር ፖሊስ ለምርመራ እፈልጎታለሁ ብሏቸዋል። ምርመራቸው የመሬት ካርታና የባንክ ሂሳብ ደብተር ጋር የተገናኘ እንደሆነ በአረብኛ የሚታተመው ባጅ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ወ/ሮ ባቢከር ዘለግ ላለ ጊዜ በቁም እስር ላይ ነበሩ። ባለፈው ዓመት በሚያዚያ ባለቤታቸው ኦማር አልበሽር ሥልጣናቸው በሕዝባዊ አመጽ ከተነቃነቀ በኋላ ለምርመራ ሲጠሩ ግን የመጀመርያቸው ነው።
ይህን ዜና የዘገበው ባጂ ዜና አገልግሎት እንደሚገምተው ከሆነ ወይዘሮ ዊዳድ ለአንድ ጊዜ ምርመራ ፖሊስ ቢጠራቸውም እስከወዲያኛው ላይፈቱ ይችላሉ ብሏል።
ሌላኛው አልአይን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ወይዘሮዋ እንዲያውም ከምርመራ በኋላ ወደ ኦምዱርማን እስር ቤት ሳይወሰዱ አልቀሩም።
የቀድሞ ፕሬዚደንቱት ኦማር አልበሽር በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኛን በመደገፍ ወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ይታወቃል።








