የቻይና ቆሻሻ መጣያ ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ መሙላቱ ተነገረ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የቻይና ቆሻሻ መጣያ ከተያዘለት ጊዜ 25 ዓመት ቀድሞ መሙላቱ ተገለጸ።
ሻኒክስ በተባለችው ግዛት የሚገኘውና የ100 እግር ኳስ ሜዳዎች ያህል ስፋት ያለው ቆሻሻ መጣያ የተሠራው፤ በቀን 2,500 ቶን እንዲይዝ ነበር።
ሆኖም ግን በቀን 10,000 ቶን ቆሻሻ ይጣልበት ነበር። ቻይና እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር የሠራችው ቆሻሻ መጣያ እስከ 2044 አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ነበር።
700,000 ስኩዌር ሜትር ላይ፣ በ15 ሜትር ጥልቀት የተሠራው ቆሻሻ መጣያው፤ ለ8 ሚሊዮን ሰዎች ጥቅም ይሰጣል ተብሏል።
በያዝነው ወር አንድ ተጨማሪ ቆሻሻ መጣያ ተገንብቷል። በ202 ደግሞ አራት ቆሻሻ መጣያዎች ይሠራሉ ተብሏል።
ቻይና ቆሻሻ ማስወገጃ መንገድን ለማሻሻል የወሰደችው እርምጃ ሲሆን፤ ቆሻሻ መጣያዎቹን ከጊዜ በኋላ የኢኮሎጂ (ስመ ምህዳር) መናፈሻ የማድረግ እቅድም አለ።
2017 ላይ ቻይና 215 ሚሊየን ቶን የሚሆን ቆሻሻ ከነዋሪዎች ሰብስባለች። በአጠቃላይ 654 ቆሻሻ መጣያዎች ያሉ ሲሆን፤ 286 መናፈሻዎችም ተገንብተዋል።
ቻይና በ2020፣ ወደ 35 የሚሆነውን ቆሻሻ ዳግመኛ ጥቅም ላይ የማዋል እቅድም ነድፋለች።
አሁን ሻንጋይ ግዛት ውስጥ ውስጥ ቆሻሻን በድጋሚ መጠቀም (ሪሳይክሊንግ) ግዴታ ተደርጓል።
2015 ላይ አንድ የቆሻሻ ክምር ሥፍራ ተደርምሶ 73 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ቻይና ይህ ከተከሰተ ከሁለት ዓመት በኋላ ከ24 አገሮች ወደ ቻይና ይገባ የነበረውን ተረፈ ምርት አግዳለች።
በ2017 አውሮፓ፣ ጃፓን እና አሜሪካ ሰባት ሚሊዮን ቶን የፕላስቲክ ተረፈ ምርት ወደ ቻይና ልከዋል። ተረፈ ምርቱ ማሌዥያ፣ ቱርክ እና ኢንዶኔዥያም ደርሷል።












