የ56 ዓመቷ ሩሲያዊት በአሳሞች ተበላች

ታትሟል

ነገሩ የሆነው ኡድመርሻ በተሰኘ የሩሲያ ግዛት ካዛን በሚባል ከተማ ውስጥ ነው። የ56 ዓመቷ ሴት አሳማዎቹን ለመመገብ ወደ ነበሩበት በረት ትገባለች። ወዲያው ድንገት ምናልባትም ከሚጥል በሽታ ጋር በተያያዘ ራሷን ስታ ትወድቃለች።

ከሰዓታት በኋላ ባሏ ወደ አሳማዎቹ በረት ሲመጣ ባለቤቱ መሬት ላይ ወድቃና ብዙ ደም ፈሷት ያገኛታል።

ባልየው እዚያው ቤት ውስጥ የነበረ ቢሆንም በጊዜ ተኝቶ እንደነበርና ኋላ ሲነቃ ሚስቱን በዚህ ሁኔታ እንዳገኛታ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በአሁኑ ወቅት በሴትዋ አሟሟት ላይ ምርመራ እየተደረግ እንደሚገኝም ተገልጿል።