ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የቡድን 20 ሃገራት በአየር ንብረት ዙሪያ እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ቢገቡም ቁርጠኝነቱ አጠያይቋል
የበለጸገ ኢኮኖሚ ያላቸው ሃገራት መሪዎች የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመገደብ "ትርጉም ያለው እና ውጤታማ እርምጃዎችን” እንደሚወስዱ ተስማሙ።
በሮም በተካሄደው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ የተደረሰው ስምምነት ጥቂት ተጨባጭ ቁርጠኝነት የታየበት ሲሉ የአየር ንብረት ተሟጋቾች እንዳልተደሰቱ ጠቅሰዋል።
አስተናጋጇ ጣሊያን በግላስጎው ከሚካሄደው የኮፕ26 ስብሰባ በፊት ጠንካራ ስምምነቶቸ እንደሚቀመጡ ተስፋ አድርጋ ነበር።
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የመሪዎቹ ቃሎች እርምጃ ከሌላቸው “ክፍተት ይፈጥራሉ” ብለዋል።
ጆንሰን "እነዚህ ቁርጠኝነቶች… በፍጥነት በሚሞቅ ውቅያኖስ ውስጥ ጠብታዎች ናቸው" ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቡድን 20ን “ተከታታይ በጣም ውጤታማ ስብሰባዎች” ነበሩ ሲሉ ገልጸዋል። በግላስጎው የአየር ንብረት ጉዳዮች ስብሰባ ላይ “ለውጡን ለመቀጠል በጉጉት እየጠበኩ ነው” ብለዋል።
ከዓለማችን ቀዳሚ የአየር ንብረት በካዮች መካከል የሚጠቀሱት ቻይና እና ሩሲያ በጉዳዩ ላይ "አልተገኙም" ይህም አሳዛኝ" ነበር ሲሉ ጠቅሰዋል።
ከ19 ሀገራትን እና ከአውሮፓ ህብረት የተውጣጡት ጂ20 በሚል ምሕፃር የሚታወቁት 20 ሃገራት 80 በመቶ ዓለምን የሚበክሉ ናቸው ይባላል።
በመሪዎቹ የተለቀቀው ይፋዊ መግለጫ በ2050 ዜሮ የከባቢ ብክለትን ስለማሳካት ምንም አይልም።
ዜሮ የከባቢ ብክለት ማለት አንድ ሀገር ከምታወጣው ከባቢ አየር ውስጥ ተመሳሳይ መጠን ያለው ልቀትን እስክትወስድ ድረስ በተቻለ መጠን የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን መቀነስ ማለት ነው።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ በውይይቱ ማገባደጃ ላይ እንደተናገሩት ሁሉም የቡድን 20 ሀገራት እስከ ምዕተ-ዓመቱ አጋማሽ ድረስ ተቀመጠው ግቡ ላይ ለመድረስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ። ሳይንቲስቶች የአየር ንብረት አደጋን ለማስወገድ ይህን በ 2050 ማሳካት ይገባል የሚሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሃገሮች በዚህ ተስማምተዋል።
የዓለማችን ትልቋ በካይ ቻይና እና ሩሲያ ግቡን ወደ 2060 ገፍተውታል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግም ሆኑ የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ለጉባኤው ሮም ያልሄዱ ሲሆን በቪዲዮ ነበር የተቀላቀት። የእነሱ አለመገኘት ስምምነት ላይ ለመድረስ ቀላል አይሆንም የሚል ስጋት ፈጥሯል።
ፑቲን ዕቅዳቸው "የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን በሚቀጥሉት ሦስት አስርት ዓመታት በሩሲያ ውስጥ ያለው የሙቀት አማቂ ጋዝ መጠን ለምሳሌ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ካሉ ጎረቤቶቻችን እና ወዳጆቻችን ያነሰ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው" ብለዋል።
መግለጫው ከዚህ ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ለአዳዲስ እና ላልተቋረጡ የድንጋይ ከሰል ማምረቻዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የገንዘብ ድጋፍ ለማቆም ቃል ገብቷል።
ይህ እንደ ቻይና፣ ሩሲያ እና ህንድ ላሉ በከሰል ላይ ጥገኛ ለሆኑ ሃገራት ጠንካራ መልእክት አለው። የጂ20 መሪዎች በራሳቸው ሃገር የድንጋይ ከሰል ኃይልን ለማቆም ከመ ስማማት አልደረሱም።
በዓመት 100 ቢሊዮን ዶላር የአየር ንብረት ፋይናንስ ለታዳጊ አገሮች የማቅረብ ግብ ላይ ለመድረስ ተቃርበው እንደነበር ድራጊ ገልጸዋል። ይህ ቁልፍ ቃል ኪዳን እስከ 2023 ድረስ ተገፍቷል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በትዊተር ገጻቸው ሮምን ለቀው የሚሄዱት “ተስፋቸው ሳይሳካ” ቢሆንም ሳይቀበር እንደሆነ አስፍረዋል።
ጆንሰን በበኩላቸው “ምክንያታዊ" ጂ20 ነበር። አንዳንድ መሻሻሎች ታይተዋል። ነገር ግን አሁንም ብዙ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ። "በአሁኑ ጊዜ የፓሪስ ስምምነት እና ከእሱ ጋር የመጣው ተስፋ በወረቀት ላይ ብቻ ነው" ብለዋል።
መሪዎች ሰኞ በኮፕ 26 ከሚያደርጉት ከፍተኛ የአየር ንብረት ስብሰባ በፊት ሮምን ለቀው እሁድ ምሽት ግላስጎው ገብተዋል።
ጆንሰን ከጉባኤው በፊት “ግላስጎው ካልተሳካ ሁሉም ነገር ይከሽፋል” የሚል አሳዛኝ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አክቲቪስቶች በቂ እንዳልሆነ በመግለጽ በመግለጫው ላይ ቅሬታቸውን አስምተው ነበር።
አቫዥ የተሰኘው ቡድን አክቲቪስት የሆነው እንደተናገረው ከቡድኑ የሚመጣ “አነስተኛ የጥድፊያ ስሜት" እንዳለ ተናግሮ "ከዚህ በኋላ ግልጽ ላልሆኑ የምኞት ዝርዝሮች ጊዜ የለንም። ተጨባጭ ቁርጠኝነት እና እርምጃ እንፈልጋለን" ብሏል።
ይሁን እንጂ ሌሎች ወደ 200 የሚጠጉ ሀገራት ልዑካን 200 ከሚጠጉ ሀገራት ተሰባስበው የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ለሚደረገው ኮፕ 26 ስብሰባ ጂ20ን መወጣጫ ደረጃ ለማየተር ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል።
አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የጂ20 ስብሰባ መሪዎች ወደ ግላስጎው ከማቅናታቸው በፊት “ኃይል ለመፍጠር የሚረዳ” ነው ሲሉ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለጆርናል ዱ ዲማንቼ ጋዜጣ እንደተናገሩት “በኮፕ በፊት ምንም አይጻፍም” ብለዋል።