በአደጋ ምክንያት ታግደው የነበሩ የቶዮታ አሽከርካሪ አልባ መኪኖች ዳግም ስራ ጀመሩ

አሽከርካሪ አልባ መኪኖች

የፎቶው ባለመብት, Toyota

ታትሟል

በቶኪዮ የፓራኦሎምፒከ ጫዎታዎች መንደር ውስጥ ጥቅም ላይ ውለው የነበሩትና በቶዮታ ከተመረቱት ከነዚህ ያለሽከርካሪ መጓዝ ከሚችሉ መኪናዎች ውስጥ አንዱ ባለፈው ሳምንት አይነ ስውር ተወዳዳሪ ከገጨ በኋላ ተሽከርካሪዎቹ ታግደው ነበር።

ሆኖም አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ተወስኗል።

በተሽከርካሪው የተገጨው ተወዳዳሪ ከባድ ጉዳት ባይደርስበትም አደጋው ባስከተለበት መጠነኛ ጉዳት ምክንያት ውድድሩ ላይ መሳተፍ አልቻለም።

ተሽከርካሪዎቹ ሌሎች ሰዎችን ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ በማለም ተጨማሪ የቁጥጥር ሠራተኞች ተመድቦባቸዋል።

በፓራ ኦሎምፒክ ተሳታፊ የሆነው የጃፓን የጁዶ ቡድን አባል አራሚቱ ኪታዞኖ ባለፈው ሐሙስ ዕለት በእግረኞች መሻገሪያ እያቋረጠ ነበረው በተሽከርካሪው የተገጨው። በዚህም ምክንያት ከሚወዳደርበት የ81 ኪሎ ግራም ውድድር መሳተፍ አልቻለም።

ሰኞ'ለተ ቶዮታ በሰጠው መግለጫ "ተሽከርካሪው ነገሮችን የሚለይበት ክፍል [ሴንሰር]የእግረኛውን መሻገሪያ በመለየት አውቶማቲክ ማቆሚያውን [ፍሬኑን]ቢያንቀሳቅም በተጨማሪም ውስጡ የነበረው ኦፕሬተር የአደጋ ጊዜ ፍሬኑን ቢጫንም ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ ከመቆሙ በፊት እግረኛውን አግኝቶታል» ብሏል።

ኩባንያው እግረኞች ለመጠበቅ ከአንድ በላይ የደህንነት ባለሙያ ተሽከርካሪዎች ላይ የመደበ ሲሆን ተሽከርካሪው የሚጓዝበትን ፍጠነት ኦፕሬተሩ እንዲወስንም ተድርጓል ሲል ገልጿል።

ተሽከርካሪው አዲስ የደህንነት ገጽታያከተተ ሲሆን ይህም ከፍ ባለድምጽ እግረኞችን ማንቃትን ይጨምራል። በፓራሊምፒክ መንደር ውስጥ ጭንቅንቅ በበዛባቸው መሻገሪያዎች ላይ የእግረኞች መመሪያዎች ከስድስት ወደ 20 ያድጋሉ።

ቶዮታ በተጨማሪም መንደሩ አገልግሎቱን እስኪጨርስ ድረስ "በየቀኑ" የደህንነት ማሻሻያዎችን ማድረጉን እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

ተሽከርካሪ አልባው መኪና አደጋ ማድረሱን ተከተሎ የቶዮታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አኪዮ ቶዮዳ በአደባባይ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ቶዮዳ ክስተቱ "አውቶማቲክ ተሽከርካሪዎች ለመደበኛ መንገዶች ገና ብቁ አለመሆናቸውን ያሳያል" ብለዋል።

እነዚህ ሙሉ በሙሉ በኤሌትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በኦሎምፒክና ፓራኦሎምፒክ ተሳታፊዎችን በፍጥነት ለማድረስ በማለም ነው ወደ ስራ የገቡት።