ቻይና የማይክሮሶፍት ልውውጥ ላይ ከፍተኛ የመረጃ ምንተፋ አድርጋለች ሲሉ ምዕራባዊያን ከሰሱ

የፎቶው ባለመብት, Reuters
እንግሊዝ ፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት ቻይና በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ፈፅማለች ሲሉ ከሰሱ።
ጥቃቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢያንስ 30, ሺህ ድርጅቶች ላይ ያነጣጠረ እና የማይክሮሶፍት ልውውጥን መሰረት ያደረገ ነበር ተብሏል።
ይህ ጥቃት የቻይናን የሳይበር ጥቃት ባህርይ ከስለላ ተግባራት ወደ ሰብሮ በመግባት መረጀዎችን ወደ መመንተፍ መሸጋገሩን እንደሚያሳይም የምዕራባዊያኑ የፀጥታ ተቋማት ደምድመዋል።
የቻይናው የደህንነት ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትም በተመሳሳይ በሰፊ የስለላ ተግባራት እና ‹‹ግድየለሽነት›› በተሞላበት ባህሪ ተወንጅሏል ።
ቻይና የመረጃ ምንተፋ ክሶች ሲቀርቡባት የመጀመሪያው አይደለም። እነዚህን ክሶች ውድቅ የምታደርገው አገሪቱ ሁሉንም ዓይነት የሳይበር ወንጀል እንደምትቃወም ትገልፃለች።
ነገር ግን ቻይና አሁን በምዕራባዊያኑ የቀረበባት የተባበረ ክስ የጉዳዩን ክብደት ያሳያል። የምዕራባዊው የደህንነት ሹሞች እንደሚሉት የዚህ ክስተት ገጽታዎች ከዚህ በፊት ካጋጠሙ ከየትኛውም ክስተቶች የበለጠ ከባድ ነው።
ይህ ጥቃት የጀመረው ባለፈው ጥር ‹‹ሃፊኒም›› በመባል የሚታወቀው ከቻይና ጋር ተያያዥነት ካለው ቡድን የመጡ የመረጃ መንታፊዎች የማይክሮሶፍት ልውውጥን ደካማ ጎኖች በመመርመር የተጀመረ ነው ተብሏል።
መረጃዎቹን ለመመንተፍ የሚያስችል ደካማ ጎኖችን ካገኙ በኋላ ጥቅም ላይ አውለውታል።
እንግሊዝ ጥቃቱ የግል መረጃዎችን እና የአዕምሯዊ ንብረቶችን ማግኘትን ጨምሮ መጠነ ሰፊ የስለላ ሥራዎች የተከናወኑበት ሳይሆን አይቀርም ብላለች። ይህም ከዚህ ቀደም የሃፊኒም ኢላማ ከነበሩት የመከላከያ ተቋራጭ ተቋማት፣ ቲንክ ታንኮች እና ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ያተኮረ ነበር።
አንድ የደህንነት ምንጭ ለቢቢሲ እንደገለፁትም የማይክሮሶፍት ልውውጥ ደካማ ጎኖች በሰፊው ተጠቃሚ ዘንድ ሳይታወቁ ቀድመው ለመለየት በከፍተኛ ፍጥነት ስራዎችን እያከናወኑ እንደሆነ ተናግረዋል።
በየካቲት ወር አንድ ሌላ ቡድን መጠነ ሰፊ ዘመቻ አካሂዶ እንደነበርም ተሰምቷል። በርካታ በቻይና የተመሰረቱ ቡድኖች ተጋላጭነቱን መጠቀም በጀመሩበት ግዜ ጥቃቱ የጅምላ እንዳደረጉት ተጠቁሟል።
በዓለም ዙሪያ ቁልፍ የሚባሉ ኢንዱስትሪዎች እና መንግሥታት ኢላማ እንዲሆኑ ተደርጓል።
ማይክሮሶፍት መጋቢት ሁለት ቀን ስለ ተጋላጭነቱ በይፋ በመናገር ለመዝጋት ማሰቡን ጠቁሟል። በወቅቱም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የመረጃ መንታፊዎች የጠለፋውን ዋጋ በመረዳት በገፍ ለመጥለፍ ተሰማርተዋል።
በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ ስርዓቶች ለጥቃቱ የተጋለጡ ነበሩ። በተለይም አነስተኛ ወይም መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች እና ድርጅቶች የሆኑ ቢያንስ 30,000 ተቋማት በጥቃቱ ተጎድተዋል ።
የአሜሪካ የፍትህ መምሪያ በበኩሉ በአራት የቻይና የደህንነት ጠላፊዎች ላይ የወንጀል ክሶችን መመስረቱን ይፋ አድርጓል።












