የትዊተር ፎቶ ማቀናበሪያ ቀመር በዘር እንደሚያዳላ ተደረሰበት

ካሜራ እያየች ያለች ጥቁር ሴት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

የትዊተር 'አውቶማቲክ' የፎቶን መጠንን የማስተካከያ ስርዓት ነጭ ቀለም ላላቸው ሰዎችና ሴቶች እንደሚያዳላ መታውቁን ኩባንያው ገልጿል።

የማህበራዊ ገጹ ተጠቃሚዎች በመጠን ትልቅ የሆኑ ፎቶዎችን ለማሳነስ በሚሞክሩበት ጊዜ ይህንን ስራ የሚሰራው የቲውተር ቀመር ላይ ያጋጠማቸውን ችግሮች ከገለጹ ከወር በኃላ ነው ኩባንያው ይህን ያለው።

ትዊተር ተከታታይ ፍተሻ ከደረገ በኃላ ነው ችግሩ መኖሩን ያረጋገጠው።

ኩባንያው ይህ ችግር ያለበት ስርዓት አሁን ከአገልግሎት ውጪ እየተደረገ መሆኑን ገልጾ በተሻሻለው የዕጅ ስልኩ መተግበሪያ ላይ ያለ አድሎ ትክክለኛ የተጠቃሚዎች ምስልን እንደሚያሳይ አስታውቋል።

የትዊተር የዘር መድሎ

ባለፈው ዓመት መስከርም ላይ አንድ ጥቁር የዩኒቨርሲቲ ሰራኛ የራሱንና የሌላ ነጭ የስራ ባልደረባውን ፎቶ ትዊተር ላይ ለመለጠፍ ሲሞክር ቀድሞ የነጩም ይሁን የጥቁሩ ፎቶ ይያያዝ የቅድመ እይታው ቀመር ግን እየደጋገመ የሚያሳየው የነጩን ፎቶ ብቻ ነበር።

ሌሎች ተጠቃሚዎች ደግሞ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባርክ ኦባማና ሴናተር ሚች ማኮኔል ያለበትን ፎቶ ወይም ሌላ ነጭና ጥቁር ሰዎች በጋራ ያሉበትን ፎቶ በመውሰድ ቀመሩ ያለበትን ችግር ደርሰውበታል።

ፎቶዎቹን ወስደው በትዊተር የፎቶ መጠን ማስተከካያ ላይ ሲያስቀምጥ ቅደመ እይታው ጥቁር ቀለም ያለውን ሰው በመከለል ነጩን ሰው ብቻ ያጎላል። በፎቶው ያለው ጥቁር ሰው ለማየት የምስሉ የመጀመሪያ ሙሉ መጠን መሆን ይጠበቅበታል።

ለጉዳዩ በፍጥነት ምላሽ የሰጠው ትዊተር የቀመር ማሽኑ ፍተሻ ማድረጉን ገልጾ ማስተካከያ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

እናም ኩባንያው በቀመሩ ምህንድስና ላይ ያሉ ችግሮችን አስመልከቶ ማብራሪያ አውጥቷል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 የተዘጋጀው ቀመሩ የፎቶ መጠንን የሚያስተካክለው ቀመር በምስሉ ላይ ያለን ሰው አይን ተከትሎ እንዲሰራ መዘጋጀቱን ያስረዳው ኩባንያው ይህን ግን በርካታ የተወሳሰቡ ውጤቶችን ማስከተሉን ገልጿል።

በሙከራው ውጤትም ቀመሩ 80 በመቶ ለሴቶች፣ 4 በመቶ ለነጮች፣ 7 በመቶ ለነጭ ሴቶችና 2 በመቶ ደግሞ ለነጭ ወንዶች እንደሚያደላ ታውቋል።